ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!


ንጉሴ ዘነበ ማን ነው??

Image may contain: 1 person, closeup


ንጉሴ ዘነበ በድሬ ደዋ አዲስ ከተማ ነዋሪ የነበረ ሲሆን፤ በደግነቱ፤ በሰው አክባሪነቱና በተግባቢነቱም በአካባቢውና በጓደኞቹ በጣም የሚወደድ፤ ለቤተሰቦቹም አለኝታ የነበረ ወጣት ነበር። በትምህርት ደረጃውም ምጡቅ ከሚባሉት የወቅቱ ተማሪዎች አንዱ ነበር። በአለማያ ኮሌጅ የ 2ኛ አመት ተማሪ የነበረው ንጉሴ ዘነበ ለሓገሩና ለህዝቡ በነበረው ፍቅርና መፍትሄው የስርአት ለውጥ እንደሆነ ባለው ፅኑ እምነት፤ በጋራሙለታ ውስጥ ከነበረበት የእድገት በህብረት ዘመቻ ወደ ድሬ ደዋ በመመለስ፤ በኢሕአፓ ስር ተደራጅቶ በፋሺስቶቹ በግፍ እስከተገደለበት ቀን ድረስ በአቋሙ ፀንቶ ቆሟል።

ንጉሴ ዘነበ ላመነበት አላማ፤ ህዝባችን ከአንባገነኑና ፋሺስቱ ወታደራዊ ስርአት ተላቆ ዲሞክራሲና ህዝባዊ መንግስት እንዲሰፍን የበኩሉን በቆራትነት ታግሎ አስመስክሯል። ባድርባይ ምሁራንና በቦዘኔ ካድሬዎች ድጋፍ የትግሉ ሃይል ሚዛን እየተቀየረ ሲመጣ፤ የኢሕአፓ መዋቅር እየተጋለጠና እየተመታ በመምጣቱ፤ ወጣቱ ለእስራት ግድያና ስደት ተዳረገ። ንጉሴ ዘነበም ለአደጋው ተጋልጦ መፈለግ ሲጀምር ከድሬ ደዋ አምልጦ በገጠር አካባቢ እራሱን በመቀየር መኖር ጀምሮ ነበር።

የንጉሴ ዘነበ ማምለጥና መሰወር የቆጫቸው ቅጥረኛ ካድሬዎች፤ ቤተሰቡን በማግባባትና ተመልሶ መጥቶ እጁን ከሰጠ ምህረት እንደሚደረግለት የተለመደ ፋሺስታዊ ውሸታቸውን ዋሽተው፤ በቤተሰቡ አማካኝነት እጁን እንዲሰጥ ካደረጉት በኋላ፤ ቀይ ሽብር በማለት በግፍ ተገድሎ እንዲጣል ተደርጓል።

ንጉሴ ዘነበ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። ነፍስ ይማር!! በጣም እንኮራበታለን!!!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!