April 6, 2019

source: https://mereja.com/amharic/v2/107120


አቶ ታከለ ኡማ በጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ ከሚመራው የባለአደራ ምክር ቤት ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ መያዙን ሰምቻለሁ። ይሄ መልካም ዜና ነው። መሰረታዊ የአዲስ አበባ ሕዝብ ጥያቄ ይዘው ከተነሱ ጋር የአዲሳ አበባ ከተማ አመራር ነን የሚሉ ማዳመጥና መስማት ከስራ ዘርፋቸው አንዱ ነው። እግርጠኛ ነኝ አቶ ታከለ ኡማ እነ እስክንድር ባቀረቡት ጥያቄዎች ላይ ይስማማሉ የሚል እምነት አለኝ።
ይሄን ብዬ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ስለሰጡት አንድ ንግግር ልውሰዳችሁ። ንግግሩን በጣም ሃሪፍ ንግግር ሆኖ አግኝቼዋለሁ። “ብሄረተኝነት ለኦሮሞ አይጠቅምም፣ ለማንም አይጠቅም” ይላሉ ኢንጂነር ታከለ።

ኢንጂነር ታከለ ሲሾም የተሾሙበት አካሄድ በጣም መስመር የለቀቀና ከአዲስ አበበ አስተዳደር አሰራር ውጭ በኦዴፓ/ኦህዴድ የተሰጠ ሹመት በመሆኑ ከፍተኛ ተቃዉሞ ማቅረቤ ይታወቃል።
“ለምን ታከለ ኡማ መነሳት እንዳለበት” በሚል ርእስ ከሰባት ወራት በፊት ሶስት ምክንቶችን በማቅረብ ነበር ኢንጂነሩ እንዲነሱ ጥያቂር አቅርቤ የነበረው። አንደኛው አሿሿማቸው ትክክል ስላልነበ፣ ሁለተኛው ከመሾማቸው በፊት የነበራቸው አቋም ለአ.አ ጥቅም እንዲቆሙ አያደርጋቸው ብዬ በማሰቤና ሶስተኛ የጣይቱ ሃዉልት እንዲሰራ ከፈቀዱ በኋላ እንዳይሰራ በማድረጋቸው ነበር።
ከሶስት ሳምንታት በፊት “ሶስት ነጥቦች ስለታከለ ኡማ” በሚል ርእስ ስለ ም/ከንቲባው አዎንታዊ አስተያየት ሰጥቻለሁ።
አንደኛው አቶ ታከለ ምንም እንኳን የእቴጌ ጣይቱ ሃዉልት እንዲሰራ ከፈቀዱ በኋላ እንዳይሰራ ማድረጋቸው በወቅቱ ተቃዉሞ እንዳቀርብ ካደረግኝ አንዱ ምክንያት የነበረ ቢሆንም፣ ከመከልከላቸው በፊት መፍቀዳቸው ግን ፣ አይምሯቸው እንደተበላሸ የኦሮሞ ብሄረተኞ አንዱ አለመሆናቸውን የሚያሳይ ነው። እንደዚያ ቢሆኑ ኖሮ በመጀመሪያዉኑ አይፈቅዱም ነበር። ሆኖም ከሌሎች፣ የኦሮሞ ብሄረተኞችና በዉሸትFiled in:Amharic