April 7, 2019t

Gindeberet churches plea

*** ቤተ ክርስቲያን፣ በኦሮሚያ ክልል ያለችበትን አጠቃላይ ኹኔታ በተመለከተ ለማዕከል የሚቀርቡ ሪፖርቶች፣ ምርቅና ፍትፍት ናቸው፡፡ በክልሉ ከሚገኙ 15 አህጉረ ስብከት የሚበዙቱ፣ በመንፈሳዊና የአስተዳደር ዘርፎች፣ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መጠናከሩንና መስፋፋቱን የሚያሳዩ በርካታ ተግባራት እንዳከናወኑ የገለጹባቸው አስደሳችና ተስፋ ሰጪ ዘገባዎች፣ ፈጣን የጋራ ምላሽን የሚጠይቁ አሳሳቢ ስጋቶችና ተግዳሮቶች መኖራቸውንም የሚጠቁሙ ናቸው፡፡ በስኬት ረገድ፣ በጥቅምቱ የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 37ኛ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ የተሰሙት የአህጉረ ስብከቱ ሪፖርቶችና ተጓዳኝ መረጃዎች ካሰፈሯቸው ክንውኖች መካከል፡-

በውስጣዊ ችግሮችና ድክመቶች እንዲሁም በውጫዊ ተጽዕኖዎችና ተግዳሮቶች ረገድ፣ ሪፖርቶቹና መረጃዎቹ ከጠቆሟቸው መካከል የሚከተሉት ዐበይት ነጥቦች ይገኙባቸዋል፡-

‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡‡ በማዕከል ደረጃ፣ የአህጉረ ስብከቱን ስኬቶች ለማጠናከርና ዘላቂ ለማድረግ፣ ችግሮቹን ለመቅረፍና ተግዳሮቶቹን ለመቋቋም እንደሚያስችሉ የታመነባቸው ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ በሰባክያንና በካህናት ሥልጠና እና ስምሪት፣ ቅዳሴያትን ጨምሮ የሥርዓት መጻሕፍት ትርጉሞች እንዲሁም የመዝሙራት ዝግጅቶች ተጠቃሾቹ ናቸው፡፡ማኅበረ ቅዱሳን፣ ሥርዓተ ትምህርት በመቅረፅና መምህራንን በማሠልጠን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያትና በመደበኛ ጉባኤያት የሚያበረክተው ክፍተት የመሙላት አገልግሎት በቀላሉ የሚታይ አይደለም፤ የተግባር ምላሽ እየሰጡ የሚገኙ ሌሎችም ተቆርቋሪዎች ያሉ ሲኾን፣ በአካባቢ ደረጃ፣ በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት የግንደ በረት እና አቡና ግንደ በረት አብያተ ክርስቲያን የአገልግሎት ማኅበር አንዱ ነው፡፡ የሀገረ ስብከቱ መንበረ ጵጵስና በኾነው አምቦ፣ አዳማ፣ አዲስ አበባ፣ ሰበታና ሌሎችም ከተሞች በሚኖሩ የግንደ በረት እና የአቡና ግንደ በረት ተወላጅ ምእመናንና በጎ አድራጊዎች፣ ከዐሥር ዓመት በፊት የተቋቋመው ማኅበሩ፣ በመጪው ሳምንት እሑድ፣ ሚያዝያ 6 ቀን 2011 ዓ.ም.፣ ከ7፡00 ጀምሮ “የግንደ በረት አብያተ ክርስቲያናትን እንታደግ” በሚል መሪ ቃል፣ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ የገቢ ማሰባሰቢያና የምምክር መርሐ ግብር ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ ባለፉት 27 ዓመታት የተሰበከው የጎሠኝነት ፖሊቲካ የፈጠረው ጥላቻ፣ በቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ተልእኮ አፈጻጸም ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተጽዕኖ በቁጭት ያነሣሣው ማኅበሩ፣ አገልግሎቷ የተሟላና ዘላቂ ይኾን ዘንድ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ ቆይቷል፡፡ “የሰሜኖች/የምኒልክ እንጂ የአንተ አይደለችም” የሚለውን ከፋፋይ ተረክ ስሑትነት በማስጨበጥ፣ አንዲት፣ ቅድስት፣ ሐዋርያዊትና ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እንደኾነች የሚገልጽ ኹለንተናዊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡

Gindeberet churches plea0

ከወረዳው 41 አብያተ ክርስቲያን ውስጥ ከ15 በላይ የኾኑት፣ ምንም አገልጋይ እንደሌላቸውና በመንፈቅ አልያም በዓመት አንዴ፣ ከሌሎች አድባራት ተለምነው፣ አውሬውንና ተናዳፊውን ታግሠው በሚመጡ ካህናት እንደሚከፈቱ የማኅበሩ አመራሮች ተናግረዋል፡፡ ከመቶ ያላነሱ የፕሮቴስታንት አብያተ እምነት በአጭር ጊዜ በተስፋፉበት የግንደ በረት ወረዳ ከተማ/ካቺሲ/ ኦርቶዶክሳውያን ያላቸው፣ አንድ የመድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ብቻ መኾኑ፣ “የፖሊቲካውን ተጽዕኖ ያሳያል” ይላሉ፡፡ ማኅበሩ፣ መንፈሳዊ ጉባኤያትን በማዘጋጀት፣ በየዓመቱ ጥቅምት 27 ቀን በሚከበረው የካቺሲ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በዓለ ንግሥ ጉዞ በማድረግ፣ ያረጁ ሕንፃ አብያተ ክርስቲያንን በማደስ ችግሩን ለመቀነስ ከስምንት ዓመት በፊት የጀመረውን ጥረት አሁንም ቢቀጥልም፣ ዋነኛው መንሥኤ፣ ቤተ ክርስቲያን በልጆቿ ላይ አለመሥራቷ መኾኑን የአመራር አባላቱ አስገንዝበዋል፡፡ መንፈሳዊውን ትምህርት ከዘመናዊው ያጣጣሙ ኹለገብ ተተኪ አገልጋዮችን ለማፍራት በማሰብ፣ ከስምንት ዓመት በፊት የአንደኛ ደረጃ ዘመናዊ ት/ቤት በወረዳ ከተማው መክፈታቸውንና በቅርቡም ተመጋጋቢ የኾነ የአብነት ትምህርት ቤት ለማቋቋም ማቀዳቸውን ተናግረዋል፡፡ የካቺሲ መድኀኔዓለም መንፈሳዊ ት/ቤት የተሰኘውና በደብሩ ቅጽር ለመገንባት የታቀደው የአብነት ት/ቤቱ፦ የመማሪያ ክፍሎች፣ የተማሪዎች ማደሪያ፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የኮምፒዩተር ማእከልና የእንግዶች ማረፊያ እንደሚኖሩት አመራሮቹ ገልጸዋል፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ፣ ከወረዳው 41 አብያተ ክርስቲያን የተውጣጡ 50 ተማሪዎችን በመያዝ ሥራውን እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡ በቀኑ መርሐ ግብር፣ ቀደም ሲል በተቋቋመው የካቺሲ መድኀኔዓለም ት/ቤት፣ ዘመናዊ ትምህርታቸውን እንደሚከታተሉና በአዳሪ መርሐ ግብር ደግሞ በአብነት ት/ቤቱ መንፈሳዊውን እንደሚገበዩ ገልጸዋል፡፡ “ተማሪዎቹ በወረዳው እስካሉና በሚሔዱባቸው ቦታዎች ኹሉ ብቁ አገልጋዮች ኾነው እንዲወጡ የሚያደርግ ሥርዓት እንከተላለን፤” ያሉት አመራሮቹ፣ በወረዳውም ኾነ በክልሉ የካህናትንና የዲያቆናትን እጥረት ለማቃለል አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተስፋቸውን ገልጸዋል፡፡ ማኅበሩ፣ የተመረጡትን ተማሪዎች አልባሳትና የምግብ ወጪ እንደሚችልና ትምህርት ቤቱን በመገንባትና በማደራጀት ረገድ፣ ምእመናንና በጎ አድራጊ አካላት፣ የገንዘብ፣ የሞያና የቁሳቁስ እገዛ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል፡፡ ከቤተ ክርስቲያኑ ኹለት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ የደብሩ የከተማ ይዞታ ላይ የተገነባው ዘመናዊው የመድኀኔዓለም አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ከዐጸደ ሕፃናት እስከ ስድስተኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ እያስተማረ ይገኛል፡፡ ከአቻ ት/ቤቶች ጋራ በተደረገ የተማሪዎች ውድድር ቀዳሚና የሌላ እምነት ተከታይ የኾኑ ነዋሪዎችም ለልጆቻቸው መማሪያ የሚመርጡት እንደኾነ ተገልጿል፡፡ በአንድ ብሎክ የጀመረውን የመማር ማስተማር ሥራ እያስፋፋ አራት ማድረሱንና ግንባታውን ሲያስፋፋ ደረጃውን እስከ 8ኛ ክፍል ማሳደግ እንደሚችል በወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ፈቃድ ተሰጥቶታል፡፡ ኾኖም ተጨማሪ ቦታ ጠይቆ በመከልከሉ፣ ያለውን 4ሺሕ ካሬ ያህል ይዞታ በማመጣጠን ዘመናዊ ቤተ መጻሕፍትንና ቤተ ሙከራን ያካተቱ አራት ተጨማሪ ብሎኮችን ለመገንባት ዐቅዷል፡፡ ተማሪውንና ኅብረተሰቡን በማገልገል ቋሚ ገቢ የሚያስገኙ ዳቦ ቤት፣ ወፍጮ ቤትና የእንስሳት ማድለቢያ ግንባታም እንደሚከናወን የማኅበሩ ዕቅድ ይጠቁማል፡፡ በመኾኑም፣ የአዳሪ አብነት ት/ቤቱን በመገንባትና ዘመናዊውን ት/ቤት በማጠናከርና በማስፋፋት ረገድ፣ ምእመናንና በጎ አድራጊዎች፣ በመጪው እሑድ ሚያዝያ 6 ቀን፣ ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ፣ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚካሔደው የገቢ ማሰባሰቢያና የምክክር መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ኹለንተናዊ