April 9, 2019

በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ታህሳስ 12 1938 ዓ.ም 5 (C–47) አውሮፕላኖችን በመያዝ ተመሰረተ፡፡
አየር መንገዱ መጋቢት 30 1938 ዓ.ም የመጀመሪያውን በረራ ወደ ካይሮ አደረገ።
73 የስኬት አመታትን ያሳለፈው አየር መንገዱ የአፍሪካዊነትን መንፈስ በማበልፀግ ግንባር ቀደም መሆኑ ይነገራል፡፡
የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በማንገብ የሚንቀሳቀሰው አየር መንገዱ በአሁኑ ጊዜ 108 አይሮፕላኖችን ይዞ እየሰራ ይገኛል፡፡
አየር መንገዱ በቅርቡ ወደ ኢስታንቡል ቱርክ አዲስ የበረራ መስመር ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
የቱርክ ኢስታምቡል የበረራ መስመር ለአየር መንገዱ 120ኛው አለም አቀፍ መዳረሻ ነው፡፡
EBC
