April 9, 2019

የከሚሴ ዞን ልክ እንደ መተማ ወታደራዊ ስልጠና እየተሰጠበት እንደሆነ ከ10 ወራት በፊት (ሰኔ/2010)  በብአዴን አሁን ያለበት ሁኔታና ተግዳሮቶቹ በሚል ለከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ባዘጋጀው ሰነድ ላይ አቅርቦት ነበር።

ይህ የሰነድ ማጠቃለያና የመፍትሄ ሀሳብ (የመተማውን ሶስት ቀበሌዎች ጨምሮ) ለፌደራል መንግስቱ ከማስፈፀሚያ እቅድ ጋር ተልኮለት ነበር።

ይህም ማለት ፌደራል መንግስት በፖለቲካ አመራሩና በደህንነት መዋቅሩ የደረሰውን ሰነድ መተግበር ቢችል በምዕራብ ጎንደር ያ ሁሉ ቀውስ ከመድረሱ በፊት መቆጣጠር ይቻል ነበር።

በተመሳሳይ ሰሞኑን በከሚሴና ሰ/ሸዋ (አጣየ ሜጀቴ) የደረሰውን ጭፍጨፋም ቀድሞ መቆጣጠር ይቻል ነበር።

ይህ ሁሉ ሲሆን የፌደራል መንግስት ሆን ብሎ ጉዳዩ ጭፍጨፋ እና መፈናቀል እንዲያስከትል ችላ ብሎት እንደቆየ ይጠቁማል።

የክልሉ መንግስትም የፌደራል መንግስቱ የመፍትሄ እርምጃ ባለመውሰዱ ዝም ብሎ እጁን አጣጥፎ ተቀምጦ አስከሬን ቆጣሪ ከመሆን የሚከፈለው ዋጋ ተከፍሎ የመተማውንም ችግር ይሁን የከሚሴውን መቀነስ ይቻል ነበር።

የምዕራብ ጎንደር (መተማ) የደረሰብን ስብራት እስካሁን ክልሉ ሌላ ነገር እንዳያስብ/እንዳይሰራ አድርጎታል።

የክልሉ መንግስት የከሚሴውን ጉዳይ አደጋው ሳይከፋ በመጨረሻው ሰዓትም ቢሆን እንኳን ልዩ ሀይሉም ወደ ከሚሴ ማስጠጋቱ የሚያስመሰግነው ነበር።

ይሁንና

•ለወራት ከፍተኛ ስልጠና ሲያደርጉ የቆዩት ቀድመው ጥቃት በመፈፀማቸውና ህዝቡም ከለላ ለመስጠት መሞከሩ፣

•በተለይም እንደ ግንቦት ሰባት ያሉ ጋጠወጥ ደጋፊ አፈቀላጤዎች በማያውቁት መንገድ ጉዳዩን በማራገብ ሌላ ፅንፍ እንዲይዝ በማድረጋቸው፣

• የዞኑ አመራሮች የዚሁ የጭፍጨፋ አካል ደጋፊ ሆነው መገኘት እና

•የኦሮሞ መብት ተሟጋቾች የተዛባ ቅስቀሳ ማድረጋቸው ክልሉን አጣብቂኝ ውስጥ ከቶ የሟቾችና ቁስለኞችን ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል።

የክልሉ መንግስት በተለይም እንቅልፉን ተኝቶ በኖረ ፌደራል መንግስት ትዕዛዝ መከላከያ ገብቶ ከማረጋጋት ይልቅ ከለላ መስጠቱ የዚሁ የቀውሱ አካል ነው።

አንዳንዶች ይህንን ሰሞን ቀውስ ፈጣሪውን ኦነግን ለመከላከል ሲሉ ሲያሻቸው አብንን ሲያሻቸው አዴፓን በማያገባቸው መውቀስ ሲያዘወትሩ ለአማራ ያላቸውን ጥላቻም እየነገሩን እንጅ ለችግሩ ተቆርቁረው አይደለም።

ስለሆነም በሰሞኑ ችግር የፌደራል መንግስት፣የከሚሴ ዞን አመራሮች እና አንዳንድ የኦዴፓ አመራሮች ካልተጠየቁ የዚህ አይነት ችግር ወደፊትም ስጋት ሆኖ ይቀጥላል።መተማመንም አይኖርም።

በተለይ በተለይ የአዴፓ አመራሮች ችግር ከመፍታት ይልቅ በመግለጫ የፌደራሉን መንግስት ችግር መሸፈኛ እየሆኑ ስለሆነ ይህም ሊታረም ይገባል።

ሰሞኑን መከላከያ በሰራው ስህተት ምክትሉ (አዴፓ) ምንም በማያውቀው ገብቶ ሲዘባርቅ ተስተውሏል።በደህንነቱ ጉዳይም ብዙ ጥያቄ እየተነሳ እያለ የማያገባው ተመስገን ጥሩነህ መግለጫ ሲሰጥ ነበር።

በተመሳሳይ ንጉሱ ጥላሁንም እንደለመደው የተዛባ መግለጫ ሰጭና የመንግስት ገመና ሸፋኝነቱን ቀጥሏል።ችግሩን የፈጠረው መሪው ኦዴፓ ሆኖ እያለ ፕረስ መግለጫው ላይ ግን ብቅ እያሉ የሚቀደዱት የብአዴን ካድሬዎች ናቸው።ዶ/ር አብይ ይህንን የሚያደርገው በተጠና መልኩ ነው።ችግሩን በራሱ ሰዎች ይፈጥራና መግለጫውን በብአዴን ሰዎች ያሰጣል።
ይህ የብልጣብልጥ አካሄድ አሳፋሪ ነው።