April 8, 2019
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ወረዳ እና በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭት ከተፈጠረ በኋላ ከመተሐራ ከተማ የተፈናቀሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በችግር ላይ እንደሚገኙ ለDW ገልጸዋል። በአዋሽ ከተማ ተጠልለው የሚገኙት እነዚሁ ነዋሪዎች መንግስት ችግራቸውን ተመልክቶ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ወደ አካባቢው የተጓዘው ዘጋቢያችን ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር የተወሰኑትን ተፈናቃዮች አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ በምሽቱ የሬድዮ ስርጭታችን ይጠብቁ። ከታች የተያያዘውን ቪዲዮም ይመልከቱ።
(ቪዲዮ፦ ዮሃንስ ገብረእግዚያብሔር )
