April 9, 2019
ምንጭ – ኢትዮ ሚዲያ ፎረም

ከጥቂት ቀናት በፊት በኢሳት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ላይ ከወደ ዋሺንግቶን በቀጥታ የሚተላለፈውን ስለ ጊዴኦ ተፈናቃዮች ወቅታዊ ችግር ስርጭት አይቼ በጥሞና መከታተል ጀመርኩ። ለችግር ለተዳረጉት ትዮጵያውያን ወገኖቹ ዕርዳታ በማሰባሰብ የታወቀው ወንድማችን ታማኝ ጥቁር ልብስ ለብሶ በመሃሪ ደገፋው የሃዘን ሙዚቃ ታጅቦ ከበስተኋላው የሰቆቃን ህይወት በማሳለፍ ላይ ያሉትን ህዝቦች ፎቶግራፍ ሰቅሎ ካንጀቱ “ለወገኖቻችን እንድረስ” እያለ ዕንባ ቀረሽ ንግግር እያደረገ በመላው ዓለም ያሉትን ወገኖቻችንን አነሳስቶ ወደ ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ መዋጮ ማሰባሰቡን አይቼ ተደሰትኩ። በችግር ላይ ላለ ወገን መድረስ ማለት ከዚህ የተለየ ትርጉም የለውምና! በግሌ ዕድሜዬን ሙሉ የሰራሁት በተለያዩ አገራት በተለያየ ምክንያት ከቄያቸው ከሚፈናቀሉት ህዝቦች ጋር ስለነበር፣ ማፈናቀልንም ሆነ መፈናቀል የሚያስከትላቸውን ችግሮች ጠንቅቄ ስለማውቅ፣ የጌዴኦ ተፈናቃዮችን ወቅታዊ ችግር ግምት ውስጥ ለመክተት ጊዜም አልፈጀብኝም። ሙሉውን በ PDF ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ …. የጌዴኦ ተፈናቃዮች ጉዳይ…
