ምንጭ – እኢትዮ ዳዪጀስት (ethiodigest)

April 9, 2019

        አናንያ ሶሪ

~ “በብሔሩ ሳቢያ የተጨቆነ ነበር” ካልን ፤ ሁሉን በኢትዮጵያ ምድር የሚኖር ሰው ሁሉ ባለመብትና ግዴታ ነፃ ዜጋ አድርገን ፤ መበላለጡን ማስቀረትና እኩልነት ማስፈን በተቻለን ነበር!

~ ነገር ግን የመለስ እና ሌንጮ የአእምሮ-ፈጠራ ውላጅ /brainchild/ የሆነው ‘ሕገ-መንግስት’ ፤ በዜግነት ኢትዮጵያዊ – በመብትና ግዴታ እኩል ነፃ ሰዎች መሆን የሚገባቸውን ኢትዮጵያውያንን…..

በቋንቋ ሸንሽኖ እና በታሪክ ባላንጣ እንደሆኑ አድርጎ በማስላት ፤ “በልዩነት ቅራኔ ላይ የተመሰረተውን የ”ብሔር ፌደራሊዝምን” ቀመረ!

~ በዚህም የተነሳ “እኩል የኢትዮጵያ ዜጋ” ሆነው በመላው ኢትዮጵያ ባለቤትነት ተሰምቷቸው በነፃነት የሚንቀሳቀሱና የሚኖሩ ዜጎች ከመሆን ይልቅ ፤

“ክልል” ተብሎ በተመተረላቸው አጥር ተሸብበው በዚያ ውስጥ ቤተኛ፤ በሌላው ክልል ውስጥ “እንግዳ” መሆን የጀመሩ ኢትዮጵያውያን የልዩነትና ጥርጣሬ ኑሮን በግጭትና እርስ-በርስ ግድያ ጀመሩት!

~ ከሩቁም ከቅርቡም ታሪክ ውስጥ እሾህና አሜኬላው እየተመረጠ የተነዛለት ሰፊው ምስኪን ህዝብም ፤ ወደተወጠነለት የግጭት-ወጥመድ ሰተት ብሎ መትመም ጀመረ!

/ ወተር፣ በደኖ፣ አርባጉጉ፣ ሐረር፣ አርሲ፣ ….. በደም አበላ ታጠቡ!/

~ በዚህ እኩይ-‘ህገ-መንግስታዊ’ ቀመር የተነሳም፤ ከ”ዜጋነት” በአንድ ጊዜ ወደ”አናሳ፣ መጤ፣ ሰፋሪ ብሔርነት” ደረጃ የተሽቀነጠሩ አያሌ ኢትዮጵያውያን መሳደድ፣ መፈናቀል፣ እና በየተገኙበት መገደል ዕጣ-ፈንታቸው ሆነ!

~ ይኸውም አደራረግ እና ዳፋ ጊዜውን ጠብቆ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የቋንቋ ቤተሰቦች ላይ አንድ ባንድ ደረሰ…. አሁንም አላባራ! ዜጎች በከንቱ ደማቸው እየፈሰሰ ይገኛል….

* * * የዚህ ሁሉ ሰንኮፍ ‘ህገ-መንግስት’ ተብዬው፤ የእኩይ-ቂመኛ ልሂቃን የከፋፍለህ-ግዛ ማስፈፀሚያ ማኑዋል መቼ ከጥቅም ውጪ ይደረጋል?! * * *

* ሰንኮፉ ሳይነቀል ፤ ስርየት የለም! *

ዝግጅት ክፍሉ:- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እንገልፃለን!