Image may contain: 3 people, people standing, suit and outdoor

ምንድነው ይሄ ጉድ… ?

እንደዚህ ታጥቆ ግለሰቦችን የሚያጅበው የግለሰብ ጥበቃ ቡድን ነው? ወይስ የመንግስት ጥበቃ ነው? መቼም የመንግስት ታጣቂ አይሆንም በሚል እንደሚከተለው አስተያየቴን እሰጣለሁ…

መንግስት የጦር መሳሪያ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር አድርጎ ከመንግስት አካል ውጪ ማንም ሰው በተለይ የዚህ አይነት የጦር መሳሪያዎች እንዳይያዙ ካላደረገ በራሱ ላይ ሌላ መንግስት እያደራጀ እንደሆነ ሊያውቀው ይገባል።

ጃዋር መሃመድ የአንድ ሚዲያ ባለቤት ነው… አለቀ። እንዴት ነው በእንዲህ ያለ የጦር መሳሪያ አጀብ የሚደረግለት… መንግስት ሆይ ዛሬ ይሄንን ዝም ካልክ…ይቺን ልምድ ይዘው ነገ ደግሞ ሎሎችም የሚዲያ ባለቤቶችም ራሳቸውን በጦር መሳሪያ እያጀቡ ሲሄዱ ሃይ ብሎ መከልከሉ ይቸግራል።

ለምሳሌ የአውራምባ ታይምስ ባለቤት DawitKebede ተነስቶ በኡዚ ታጅቦ ቢሄድ፣ የፍትህ ጋዜጣ ባለቤት ተሜ ደግሞ በዲሞፍተር ታጅቦ መሄድ ቢጀምር፣ የሆርን አፌርስ ባለቤት ዳንኤል በበኩሉ በዙ 23 ካልታጀብኩ አልንቀሳቀስም ማለት ቢጀምሩ መንግስት ምን ብሎ ሊከለክላቸው ነው…? ስማቸው “ጃዋር መሃመድ ለተባሉ የሚዲያ ባለቤቶች ብቻ ነው በመሳሪያ የመታጀብ ፍቃድ የተሰጠው…” የሚል አዋጅ ሊያወጣ ነው?😁 ወይስ ሁሉም በየፊናው በጦር መሳሪያ እየታጀበ ሃገሪቷ የማፊያ ሃገር ልትሆን ነው?

ኧረ ግዴየለም ይሄንን ነገር በልክ አድርጉት!

አቶ ጃዋርስ ብትሆን ይሆንን አይነት የመሳሪያ እጀባ እስክንድር ነጋ አድርጎት ብታይ ምን ትል ነበር? እርግጠኛ ነኝ ዝም አትልም… (እኔም ዝም አልልም) እና ስለፈጠረህ ስለ አላህ ብለህ… በእንዲህ ያለ ማናለብኝነት መንግስትንም አታሳጣ ለራስህም ቢሆን በዚህ ደረጃ ኩፍፍፍ ማለት መልካም አይደለም እና ተንፍስ ጃዋር!

ወይ ጣጣችን!