f

April 9, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/107771


የኦሮሞ ጽንፈኞች፣ ኦነጎች፣ የጃዋር ቄሮዎችና በኦዴፓ/ኦህዴድ ውስጥ ያሉ ያልተደመሩ፣ ለነ ዶ/ር አብይና አቶ ለማ ራስ ምታት የሆኑ ዘረኛ አመራሮችና አባላት፣  በኦሮሚያ ክልልና በአማራ ክልል ከሚሴ ዞን ውስጥ በሚኖሩ፣ ኦሮሞ ባልሆኑ ማህበረሰባት ላይ፣ እንደዚሁም እነዚህን አካባቢዎች በሚያዋስኑ የሌሎች ክልሎችና ዞኖች ወረዳዎች በሚኖሩ ዜጎች ላይ የሽብር ተግባራት እየፈጸሙ እንደሆነ በገሃድ እያየን ነው።
በተለይም ዶ/ር አብይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስተር ከሆኑና ኦህዴድ/ኦዴፓ በፌዴራል መንግስቱ የበላይነቱን ከያዘ በኋላ ፣ ጽንፈኞቹ በሕወሃት ጊዜ የማይታሰብ ድርጊቶችን ነው እየፈጸሙ ነው ያሉት። አንዳድን ዜጎች ህወሃት ይሻል ነበር እስከማለትም እየደረሱ ነው። በጌዴኦ ዶ/ር አብይ ተፈናቃዮችን ለማነጋገር ሄደው በነበረ ጊዜ ፣ አንድ የጌዴኦ እናት እንደተናገሩት፣ ምን አልባትም እነዚህ ሰዎች  “የኛ ሰው ስልጣን ይዟል፣ ማንም አይነካንም”  ከሚል አስተሳሰብ ይሆናል እኩል ዘር ተኮር ተግባራት ላይ የተጠመዱት።
ለምሳሌ የሚከተሉትን በግልጽ የሚታወቁትን መጥቀስ እንችላለን። ከእነዚህ ጽንፈኞች የተነሳ

በኦሮሞ ክልል የቦረናና ጉጂ ዞኖችን በሚያዋስኑ አካባቢዎች የሚኖሩ በአስር ሺሆች የሚቆጠሩ ሶማሌዎች በግፍ ተፈናቅለዋል፤፡ ብዙዎች ተገድለዋል።
በጉጂ ዞን ውስጥ የሚኖሩ በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ የጌዴዎና የቡርጂና ወገኖች በግፍ ተፈናቅለዋል።የሞቱም አሉ።
ምእራብ ወለጋን በሚያዋስኑ የቤኔሻንጉል ክልል ወረዳዎች በሚኖሩ ጉሞዞች ላይ ኦነጎች በከፈቱት ጥቃት ምክንያት በተነሳው ግጭት፣ ከመቶ ሺህ በላይ ዜጎች ፣ አብዛኞቹ ኦሮሞዎች፣ ተፈናቅለዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል።
በሃረር ዙሪያ ያሉ ጽንፈኛ ቄሮዎች የሃረርን ከተማ የዉህ መስመሮች ለወራት ዘግተው በከተማዋ ላይ ትልቅ ሽብር ፈጽመዋል።
በአዲስ አበባ ዙሪያ በቡራዩ በአስር ሺሆች የሚቆጠሩ