
የታጠቁ ቡድኖች በደቡብ ክልል አማሮ ወረዳ በሚገኙ የኮሬ ማኅበረሰብ አባላት ላይ ግድያ እየፈጸሙ እንደሚገኙ የማኅበረሰቡ አባላት አስታወቁ።የማኅበረሰቡ አባላት ትናንት በጉዳዩ ላይ በሀዋሳ ከተማ ባካሄዱት ውይይት ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች በማኅበረስቡ አባላት ላይ የግድያ እና መፈናቀል ጥቃት እየፈጸሙ ይገኛሉ ብለዋል። መንግሥት በአካባቢው የሚንቅሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎቸን ትጥቅ እንዲያስፍታ ፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀድሞ ቦታቸው እንዲመልስ እና የሕይወት መጥፋትና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎችም ካሣ እንዲከፍል ጠይቀዋል።
DW Audio Player00:0000:00
