April 10, 2019

አብይ ወደ ውጭ ሲሄድ የሆነ የሴራ የቤት ሥራ ሰጥቶ ነው የሚለው አስተሳሰብ እየመጣ ነው፡፡ ግን እኔ የሚከተሉትን ጥያቄቆች እንዲመልስልኝ እፈልጋለሁ፡፡ ጉዳዩም እሱ ከሚያውቀው ውጭ ነው የሚል እምነት የለኝምና ነው፡፡ ሆኖም የነገሬ መነሻ በአጠቃላይ ሸዋን ለምን የፈሩታል ነው? በቅርቡ በዶ/ር አለሙ ሥሜ ላይ የተከፈተውን ዘመቻ አይቼ ነገሮችን ይበልጥ እንዳሰላስል አድርጎኛል፡፡ አሁን ደግሞ በሰሜን ሸዋ በየቦታው እየተቀሰቀሰ ካለው ግጭት ጀርባ ማን አለ? ይሄ ለሁሉም የሚቀርብ ጥያቄ ነው፡፡ እኔ የራሴን ግንዛቤ ከታች አስቀምጫለሁ፡፡ ከዛ በፊት ግን ለአብይ ያለኩትን ጥያቄ እንሆ፡-

ሕዝብ እየጨፈጨፈና ባንክ እየዘረፈ ያለውን ኦነግ የመከላከያ ሠራዊት እንዳይደመስሰው በሽምግልና ሥም የታደገው ማን ነው?

ለከሚሴው የወሎ ኦነግ የባሌ ሮቤው ትዕይንት እና ፎከራ በምን ተሳስረው ነው? ኦሮሞነት? በዛው ቦታ ሊያውም በፍርድ ቤት ፊት ለፊት ቆንጨራ ይዞ ሲፎክር የነበረው እውነቱን ለምናውቅ ምን ማለት እንደሆነ ይገባሃል? ደርግ አከርካሪውን ሰብሮት የነበረ ከጁኔዲን ሳዶ ጀምሮ ጉልበት እያገኘ የመጣ ቡድን በኦፒዲኦ ተሸፍኖ የሚንቀሳቀሰውን አላውቅም ልትል ትችላለህ?

ለመሆኑ ኢትዮጵያና ሕዝቧን እያመሰ ያለው ማን ነው? ወያኔ? እውነቱን እንነጋገር የኦሮሞ ሊሂቃን አንተን ጨምሮ ምን እየሰራችሁ ነው? የአረመኔውን ኦነግ ሰንሰለት እያጠናከራችሁ አደልም? አሁን አገሪቱ ውስጥ ላለው ችግር ከኦነግና ኦዴፓ ውጭ ማን ነው? በየቦታው ጸረ-ኢትዮጵያና ሕዝብ እንዲደራጁ የሚያደርገው ማን ነው?

በየመንግስት መዋቅሩ የእስላማዊ ኦሮሞ ጽንፈኛ አራማጆችን ሰንሰለት እያጠናከረ ያለ ማን ነው?

ከሸዋ ሰው ጠፍቶ ነው ከአርሲና ባሌ ለሱሉልታና ለገጣፎ ከንቲባ የመደባችሁት? ለመሆኑ እንዲህ ያለው አይን ያወጣ ድርጊት ለማድረግ የደፈራችሁት የሴራውን ሰንሰለት ለማሳለጥ አደለም?  ሸዋን ለምን ፈራችሁት? ኢትዮጵያዊ ስለሆነና ከሌሎችም ጋር ስለተጋበረ ለኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት ፖለቲካ ስለማይመቻችሁ አልፎም አደጋ ስለሚሆብባችሁ አደለም? የሸዋ ኦሮሞ የጎበና ዳጬ ዘር ራሱን የማስተዳደር ብቃት የለውምና ነው? ወይስ የእስላማዊው ኦሮሞ ቡድን ለማጎልበት? ሁሉም እንዲረዳኝ የምፈለገው የእስላማዊ ኦሮሞ አክራሪ ቡድን ማለት የኦነግ ክፍል ሆኖ ግን የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ኦሮሞዎችን በማደራጀት በተደጋጋሚ ችግር የፈጠረ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ከዚያደባሬ ወራሪ ጋር በመሆን ይንቀሳቀስ የነበረና ደርግ ከፍኛ መትቶት አድፍጦ የተቀመጠ ነበር፡፡ እስከ ዛሬም ድረስ በሀረር፣ አርሲና ባሌ ሕዝብ በንቃት አካሄዱን የሚከታተለው አደገኛ የሆነ ቡድን ነው፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ግልጽ መሆን አለብን፡፡  በተደጋጋሚ እነ ብርሀነመስቀል አበበ ሰኚና ገረሱ የሚባሉ እውነቱን ያውቁታል ግን በኦሮሞነት ተጋርደው ለቤተሰቦቻቸው ሳይቀር አደጋ የሆነን ቡድን እድል የሚያገኝበትን ፖለቲካ ሲያራምዱ ነበር፡፡  ስለዚህ ጉዳይ እኔ ከምናገረው የምታውቁ ሌሎች ኦሮሞ የሆናችሁ ተናገሩት፡፡ እውነቱን ብትሸፋፍኑት አደጋው ከማንም በላይ ለኦሮሞ ነው፡፡ ይሄ ቡድን አሁን በመንግሰት መዋቅር ትልቅ ሰንሰለት ፈጥሮ ይሄው በምታዩት ሆኔታ ለሸዋዎቹ ሱሉልታና ለገጣፎ ከንቲባ ሆነው ተቀምጠዋል፡፡ የአኖሌን ሀውልት ያሰራው ይሄው ቡድን ነው፡፡ መለስ ዜናዊ ይሄን ሴራ አሳምሮ ያውቀው ነበር፡፡  ከዚህ በፊት የዝቋላ ገዳምን ኢሬቻ እናከብርበታለን ብለው በይፋ በመንግስት መዋቅር ማስታወቂያ እንዳወጡ አስታውሱ፡፡ ኢሬቻ ለእነሱ እምነታቸው ባይሆንም ግን ያን ማድረግ ለዓላማቸው ግን ይጠቅማቸዋል፡፡ አስተውሉ ይሄም የሆነው አሁንም ከሸዋዎቹ ከተማ በቢሾፍቱ በአስተዳዳሪነት ተቀምጠው ነው፡፡ አገርን አንድ ያደረገው ሸዋ ራሱን መምራት ስለማይችል ሌሎች ያስተዳድሩታል፡፡

ሌላው ሁንም ከሸዋ ጋር በተያያዘ የሴራውን ሰንሰለት ሊያፈርስ የተነሳ አካል እንዳለ የሚያሳይ ፊንጭ አለ፡፡ እንሚመስለኝም ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ ላይ ከየቦታው ዘመቻ የተከፈተው ከዚሁ ጋር የተያያዘ ይመስላል፡፡ አሁን በቅርቡ ተመሳሳይ ግጭት በሰሜን ሸዋና ከረዩ ኦሮሞ ተከስቶ አሁንም ያልተፈታ ችግር አለ፡፡ አሁንም በአጣዬ ተጀመረ፡፡ ለዚህ በመንግስት መዋቅር የሉት ዋና ተዋናይ እንደሆኑ ነው የሚገባኝ፡፡  ወያኔም እጅግ ከምትፈራው ሕዝብ ሸዋ ነው፡፡ የሸዋ ኦሮሞ በጉባና ዘርነት አማራው በሚኒሊክ ዘርነት ስም ተሰጥቶት ወደ የወሳኝነት ስልጣን እንዳይመጣ በጥንቃቄ ነው የሚያዩት፡፡ ሰሞኑን በዶ/ር አለሙ ስሜ ላይ ዘመቻ የተከፈተው ያለምክነያት አልነበረም፡፡ በተለይ ከላይ ያነሳሁት የአይኤፍኤልኦ ቡድን ሸዋ እድል ከአገኘ እንኳን ለገጣፎና ሱሉልታ አርሲም እድል እንደማይኖረው ያውቃል፡፡ በአማራው ሸዋ እስከ ቀበሌ ድረስ ወያኔ ከትግራይ በመጡ ነበር ስታስተዳደር የነበረችው፡፡ የዛሬው የአጣዬና አካባቢው ችግር ከወያኔ ነው ቢባል ቢሆን እንኳን ጎንጭ አልፋ ቀልድ ነው፡፡ ጉዳዩ ግን እንዲህ ነው፡፡  ሸዋ አሁን ያለውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ሸዋ ሊያንሰራራ እንደሚችል ስጋት እየሆነ የመጣ ይመስላል፡፡ አገጣሚው ከተሳካለትን ከተነሳ ደግሞ እንደተባለው ኢትዮጵያዊነት ሊመለስ ነው፡፡ ይሄ ለብዙ አሁን ስልጣን ላይ ላሉትም ሆነ በአሸባሪነት ለተሰማሩት ትልቅ አደጋ ነው፡፡  ከተወሰነ ጊዜ በኋላ በሰሜን  ሸዋ ዞን አስተዳደር በኩል የሸዋን ሕዝብ ማደራጀት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይመስላል፡፡ ችግሩ ደግሞ በአማራው ሰሜን ሸዋ የተገደበ ሳይሆን ሸዋን በአጠቃላይ ወደነበረበት ትስስሩ የሚመልስ ነው፡፡ ለዚህም የሸዋ ጀግኖችንና ድንቅ የታሪክ ባለድርሻዎችን የሚዘክር ሲምፖዚየም በሚቀጥለው ሰኔ ይሁን ነሀሴ በደብረብርሀን ታስቦ ነበር፡፡ ይሳካ አይሳካ እናያለን፡፡ በዚህ ሲምፖዚየም የሚዘከሩት ጀግኖች በዋናነት ኢትዮጵያን የመሠረቱትና ታላላቅ ገድላትን ፈጽመው ለዛሬ የክብር ታሪክ ያቆዩት ሚኒሊክና ጎበና ጨምሮ የታላላቆቹ አባቶችና እናቶችን ነው፡፡ ይሄ አደጋ የሚሆንባቸው ዛሬ ሰሜን ሸዋን በየአቅጣጫው የተነሱበት ይመስላል፡፡ ቢያንስ እንዲህ ያለውን ድርጊት እንዳያስብ አስተዳደሩን ወከባ ለመፍጠር፡፡  በዚህ ሲምፖዚየም ከመላው ሸዋ የሚገናኙበትና የሚመክሩበት ሊሆንም ስለሚችል ትልቁ ስጋት ነው፡፡ በዚህ የተጀመረው በቀጣይ አመቦ ላይ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ ኦሮማራ በሚል ሳይሆን ኢትዮጵያ በሚል ነው፡፡ ኦሮሞውና አማራው ብቻ ሳይሆኑ ጉራጌውም፣ ከምባታውም ሌሎችም የሸዋ ግዛት ነዋሪዎች ይሰበሰባሉና፡፡ ይሄን ሀሳብ የጀመሩት እንቅስቃሴያቸው ያልተመቻቸው ቢኖሩ አይገርምም፡፡ አሁን በሰሜን ሸዋ በየቦታው የችግሮች መፈጠር ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደሆነ መገበመት ስህተት አደለም፡፡ ይሄን እቅድ በቴሌቪዥን ማስተዋወቅ ተጀምሮ ነበር፡፡