April 11, 2019

አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ውስጥ ከመቼውም የከፋ አደጋ እያመጣ ይመስለኛል፡፡ እጅግ የከፋ ዘረኝነትና ጥላቻ የገነባው የኦሮሞ ፖለቲካ ነውር የሚውቅ አደለም፡፡ ወያኔ የመንግስቱን መዋቅር ሁሉ በትግሬ ሞላው ብሎ ሁሉም አውግዟል፡፡ ዛሬ አብይ ወደ ሥልጣን ከመጣ በአንድ አመት ውስጥ ወሳኝ የተባሉ የአገሪቱ ተቋማት በኦሮሞ እየተሞሉ እንደሆነ ምን ያህል ሕዝብ እንደሚያውቅ አላውቅም፡፡ እኔ በብቃትና ከሌሎች ተሽሎ ተገኝቶ በአጋጣሚ አንድ ተቋም በርከት ያሉ የአንድ ብሔር ተወላጆች ሊኖሩት ይችላሉ፡፡ ይሄ ሊያጋጥም ይችላል፡፡ አሁን የምንነጋገረው ግን በብቃት ሳይሆን በቀጥታ በአብይ እየተሾሙ ዋና ዋና ተቋማትን እየተቆጣጠሩ ያሉ የኦሮሞ ተወላጆች ነው፡፡ አዝናለሁ! እንዲህ ባልናገር ደስ ባለኝ ነበር፡፡ እኔ ከማንም ጋር በማንነቱ ምክነያት ጉዳይ የለኝም በአመለካከት ግን ከብዙዎች ኦሮሞ ከሆኑ ጓደኞቼ ጭምር ልንስማማ አልቻልንም፡፡ ባለመስማማቴ ደስተኛ ነኝ የመረጡትን መምረጥ አይቻለኝምና፡፡ እጅግ የከፋ የዘረኝነትና ጥላቻ መንፈስ ተሞልቶ ጓደኛዬ ቢሆን ለእኔ እንደማይጠቅመኝ አውቀዋለሁ፡፡ በብዙ ተግባራዊ እውነታዎችም አይቼዋለሁ፡፡ እኔ ግን ቢቸግረው ትቼው አላልፍም፡፡ እንደሚባለው ሰው ስለሆነ ብቻ አደለም፡፡ የምጋራቸው ከደም ጨምሮ ብዙ እሴቶች አሉኝ፡፡ ሰው ስለሆነ ከዚያ በኋላ ሊመጣ የሚችል ነው፡፡

የኦሮሞ ፖለቲካን እጅግ አምርሬ የምኮንነው ዝም ብዬ ከሜዳ ተነስቼ ወይም ሲሉ ስለሰማው አደለም፡፡ በራሴ የአየሁትን እውነት መካድ ስለማልችል እንጂ፡፡ ውስጥ ለውስጥ እርስ በእርስ ትልቅ ችግር አለ፡፡ ለሌላው ያለው የጥላቻ ጥግ ደግሞ እጅግ የከፋ ነው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ አቃፊ ነው የሚለው ሊተረጎምላቸው የሚችሉ በኦሮሞ ብሔረሰብነት ያሉ የተወሰኑ ቦታዎች አሉ፡፡ አሁን ግን ይበልጠው በሚባል ሁኔታ ይሄ አባባል በብዙ ቦታዎች እውነት አደለም፡፡ በተለይ ደግሞ በኦሮሞ የተማረው በሚባለው ማህበረሰብ የለየለት ዘረኝነትና ጥላቻ ሰፍኗል፡፡ እንግዲህ የአገርን ተቋማት ሙሉ ለሙሉ እየተቆጣጠረ ያለው ይሄ በዘረኝነትና ጥላቻ የመረቀዘ አእምሮ ያለው ነው፡፡ ታስታውሳላችሁ በቀለ ገርባ በእስር ቤት በአለ ጊዜ ብዙዎቻችን ስለእሱ እንደጮኽን፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ማንነቱን አላዋቅንም፡፡ እንግዲህ በቀለ የተሻለ ኤክዝፖዠር ያለው ምን አልባትም ከሌሎች ሕዝቦች ጋር የኖረ ነው፡፡ ውስጡ የታመቀውን የጥላቻውን ልክ ግን መቆጣጠር ስላልቻለ ፈነዳበት፡፡ በቀለ በውስጡ የያዘውን ይዞ (ዘረኝነቱን) እንዳሰብንው የጎንደር አስተዳዳሪ ቢሆን ዘረኝነቱን ላናውቅ እንችል ነበር፡፡ ይሄን ሁሉ ጥላቻ የታጨቀ ሰው ግን በአገኘው አጋጣሚ ሌሎችን ለማጥቃት እንደሚያሴር አጠያያቂ አደለም፡፡ ብዙ ሰላማዊ የመሰሉን የኦሮሞ ሊሕቃን የሆነ ቦታ ማንነታቸው ሲፈነዳ አይተናል፡፡ ጓደኛዬ ብለህ የምታምነው እስክታጣ ድረስ አስደንጋጭ ይሆኑብሀል፡፡ ምንም አይነት አመክንዮ የለም፡፡

በተቋም ደረጃ በግልጽ ይሄን ትመለከታለህ፡፡ በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ ያጠቁሀል፡፡ ይሄን የሚናገረው በሕይወቱ ያለፈበትን እውነት እንጂ ከሰው የሰማው አደለም፡፡ ይሄን ለማከም ብዙ ሞክሬያለሁ፡፡ እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ዛሬ ስንተኛው ዋና ሰው እንደሆነ ባላውቅም ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሊያውም  ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አንድ ተጨማሪ ኦሮሞ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት አብይ መድቧል፡፡ ሊያውም ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ያልኩት በምክነያት ነው፡፡ ዛሬ እናገረዋለሁ፡፡ ይሄ ባንክ አደገኛ የሆነ የዘረኝነትና ጥላቻ ሴራ የሚሰራበት ባንክ ነው፡፡ ይሄ የደረሰው በራሴ በራሴ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ላለመናገር ብዙ ጊዜ ወስኜ ነበር፡፡ ግን አሁን የአገር ጉዳይ በመሆኑ መናገሩ ይጠቅመኛል፡፡ ከአንደ ጓደኛዬ ጋር ይሄ ባንክ ሲመሠረት አክሲዮን ለመግዛት በወቅቱ ቦሌ መንገድ ይመዘገብበት በነበረው አሁን የባንኩ መሥሪያቤት ወደሆነው ሕንጻ ሄደን በልጽ አስደንጋጩን የዘረኝነት እውነት ገጠመኝ፡፡ ለመመዝገብ መታወቂያ ተጠየቅን፡፡ የጓደኛዬ ሥም የሚፈልጉት ስለነበር በቀጥታ መዘገቡት የእኔ ሥም ግን እነሱ የሚፈልጉት አደለም፡፡ ሁለታችንም ፓስፖርት ነበር የያዝንው፡፡ እኔን የቀበሌ መታወቂያ ጠየቁኝ፡፡ በእርግጥም የቀበሌ መታወቂያ አልነበረኝም፡፡ ምክነያታቸው ብሔር በቀበሌ መታወቂያ ላይ ስላለ ነበር፡፡ የሚዘገንነው ነገር አስተናጋጇ ስሜን ስታይ ያለችው “ይሄማ በጣም የቀበሌ መታወቂያ ያስፈልገዋል”፡፡ ድርጊቱ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ መሠረት ወንጀል እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ለማን ይናገሩታል ይሄን የመሠለ አስነዋሪ ድርጊት፡፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ሆኖ የተሾማን ግለሰብ ከዚህ ዘረኛ ተቋም እንደሆነ ሳይ ይሄን መናገር ግድ እንደሚልና አገርንም የመታደግ ጉዳይ ሆኖ ስለተሰማኝ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ገልጬ ለጓደኞቼም አላወራሁትም ነበር፡፡ በቅርብ ጊዜ ነው ለሁለት ጓደኞቼ ይሄ ነገር ገጥሞኛል ብዬ የተናገርኩት፡፡ ጉዳዩ የአስተናጋጇ ችግር እንዳይመስላችሁ፡፡ በኋላ ጓደኛዬም ሲደብረው ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ሲላት እኔ የታዘዝኩትን ነው የምሰራው ነው ያለችን፡፡ ገባኝ ከዛ በፊት በሥራ ምክነያት ሥሜን ብቻ በማየት ተመሳሳይ ገጠመኝ ነበረኝ፡፡ እኔን ብዙም አልደነቀኝም፡፡ ይሄን እውነት ጓደኛዬ ስለሕሊናው ፍርድ ቤት በቀርብ ይናገረዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ እሱንም በመጨረሻ ኦሮሞነት(ዘረኝነት) ካልበላው፡፡ ለሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ በዚህ አጋጣሚ እናገራለሁ፡፡ ከምንም የከፋ አደገኛ በሽታ ነው፡፡ እባካችሁ ራሳችሁን ከዘረኝነት ታደጉ፡፡ ዛሬ ዘረኛውን ተቋም መናገር ያስፈለገኝ አደገኛ የሆነ ሁኔታ በአገር ላይ እየተፈጠረ እንደሆነ ስላሰጋኝ ነው፡፡

አብይ ምን እየሰራ እንደሆነ ፍርድ ለሕሊና፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤክስኪውቲቭ ማኔጅመንት አባላት

  1. ዋና ሥራ አስኪያጅ፡- ባጫ ጊና
  2. ም/ ዋና ሥራ አስኪያጅ፡- ኑሪ ሁሴን (ዛሬ የተሾመው ከላይ የጠቀስኩትን ባንክ ሲመራ የነበረ)
  3. የሰው ኃይል ኃላፊ፡- አሊ አህመድ (መቼም ነውር የለም ወንድሙ እንዳሆን)
  4. የፋይናንስ ኃላፊ፡- መሊካ በድሪ
  5. የሕግ ኃላፊ፡- ሱራ ሰቀታ
  6. የቢዝነስ ኃላፊ፡- ፍቅረሥላሴ ዘውዱ
  7. ሪስክ ማኔጅመንት ኃላፊ፡- ጥሩብርሀን ኃይሉ
  8. የውስጥ ኦዲት ኃላፊ፡- ኪዳኔ መንገሻ

ከስምንቱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኤክስኪውቲቭ ኃላፊዎች ቢያንስ አምስቱን እዩ፡፡ ሌሎቹ በሥም ስለማይታወቁ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄን የሚፈጽም  ሰው በምን ሞራል ስለ ኢትዮጵያዊነት እንደሚያወራ አይገባኝም፡፡  እነዚህ የገንዘብ ተቋማት ከንብረትነት በላይ የደህንነት አደጋም ናቸው፡፡ ዛሬ ሕዝብን እየጨፈጨፈ ያለው ኦነግ የገንዝብ ምንጭ የኢትየጵያ ንግድ ባንክ ላለመሆኑ መተማመኛ የለም፡፡ በእርግጥም በዘረፋ ሥም ከዚሁ ባንክ ባለፈው ገንዘብ ተላልፎለታል፡፡ ከዛ ይሄን ዘረፋ የፈጸመና ሕዝብን እየጨረሰ ያለ ቡድን ለመደምሰስ የመከላከያ ሠራዊት ወደ ቦታው ሲያቀና በሽምግልና ሥም የመከላከያ ሠራዊት ጥቃት እንዳያደርስበት ታድገውታል፡፡

በሌላው ዋና የአገሪቱ የገንዘብ ምንጭ ተቋም ያለውን ሌላ ጉድ በእነዚህ ሊንኮች አድምጡ፡፡

https://www.facebook.com/AbbayMedia/?__tn__=kC-R&eid=ARAlv1xkcQ6OF98swhDzOAxP4l07gntEsQgOovea8pexzxIeklwwTPt3ExxQZQSDp0JQhJoO04JCFTW1&hc_ref=ARR376CN-0392WiBlrJD3UPqo89-ISsGAIbdlQqH6RmA-7_UAJgKUUgJ_0YzWkTuUak&fref=nf
https://www.youtube.com/watch?v=E-BbhBpgKSA&fbclid=IwAR1hHcTGIQZF2Iwph_RHc_U8_yUXxQ_VQZMEiGOmIqCqu_P_r8gbb7xu8bA

በአዲስ አበባ መስተዳደርም የሆነው ተመሳሳይ ችግር ነው፡፡ በመከላከያውም ምን እንዳለ አናውቅም፡፡ ብዙ የማናውቀው ጉድ አለ፡፡ ይሄን ጉዳይ ኦሮሞ ስለሆነክ የሚያስደስትህ ሌላ ስለሆንህ የሚያበሳጭህ አደለም፡፡ ሕሊና የሚባል ነገር አለ፡፡ እንግዲህ የሄን የሚያደርግን ሰው ነው ስለኢትዮጵያዊነትና ሕዝብ ለመናገር ምን ሞራል ሊኖረው ይችላል፡፡ ኦሮሞን እንደሕዝብ ካሰብን ይሄ በመጀመሪያ ደረጃ አደጋው ለኦሮሞ ሕዝብ ነው፡፡ ለኦሮሞ ሕዝብ ቤቱ ከሚባላት ቁራሽ ምግቡ የዘለለ ምንም እንደማይደርሰው እናውቃለን፡፡ ይሄው ነበር በወያኔ ቡድን 27 ዓመት ሙሉ በትግሬነት የትግራይን ሕዝብ አንዳች የተለየ ጥቅም ሳይኖረው እንደሕዝብ እንዲጠላ ያደረጉት፡፡ የወያኔ ትግሬ ቡድን አለ አሁን እሱ ሲለቅ የኦሮሞ ኦዴፓ/ኦነግ ቡድን ተተካ፡፡ ቀጥሎ አገር እንደ አገር ከቆየች እንዲሁ ሊቀጥል ነው፡፡ ግን ትልቅ አደጋ ይዙ መጥቷል፡፡ ዘሬ በኦሮሞነትህ ይሄን ትክክል ነው ብለህ ከአመንህ ትላንት ወያኔ ያደረገው ነውር ነበር ለማለት የሞራል ብቃቱ አለመኖር ብቻ ሳይሆን እርግማን ነው፡፡ በአይንህ ያየህውን የዘረኝነት አደጋ የእኔ ወገን ከሆነ እያልክ የምትዘፍንለት ከሆነ በእውነት አይቀርልህም፡፡  አዝናለሁ! አብይ ይሄን የሚያሴር ሰው ነው የሚል እምነት አልነበረንም፡፡ ለማም አዝናለሁ ቃልህ እውነት ለመሆኑ ማረጋገጫ የለውም፡፡ ይልቅ ዘረኝነትህን ጠቋሚ እውነቶችን እያየን ነው፡፡ እንግዲህ ሕዝብ በየቦታው እያለቀ ያለው በእነዚህ ሰንሰለቶች በሚታገዝ ውንብድና አለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም!

ቴድሮስ ጸጋዬ የተናገረው አንድም ውሸት የሆነ ነገር የለም፡፡ የራሱ የሆነ አጀንዳ ሊኖረው ይችላል፡፡ ግን የሚናገረው በተጨባጭ ማስረጃ ነው፡፡ ቴድሮስን የምታውግዙ መጀመሪያ እየሆነ ያለውን ገሀዳዊ ነውር አውግዙ፡፡ አሁን እነ አብይ በብዛት የፌስቡክ አርበኛ እንዳሰማሩ እናያለን፡፡ ይሄን ደግሞ ከየት አመጣህው አትበሉኝ፡፡ ቆይታችሁ ሁሉም ነገር ይገለጽላችኋል፡፡ በወያኔ እየተሳበበ ፌስቡክ ላይ በኦሮሞ ሥም ይለቀቃል የሚባለውን መጠነኛ ጥናት ለማድረግ ሞክሬ ነበር፡፡ እውነታው ከዚህ ውጭ ነው፡፡ በትክክልም እኔ እንደደረስኩበት በኦሮሞ ሥም ሆነው ፌስቡክ ላይ መርዝ የሚረጩት በትክክልም ኦሮሞ ናቸው፡፡ ጥቂት ሌሎች አሉ፡፡ ግን ይሄ ነው የሚባል አደለም፡፡  አሁን ላይ እየተሞከረ ያለው ደግሞ አደገኛ የሆነ ሐይማኖትን የሚነቅፍ ሴራ ነው፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔርን ለማወቅ በአልፈለጉት መጠን የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው የሚለው የፈላስፈው አባባል እንዲህ በተግባር እየተተረጎመ ነው!

ለሁሉም ይሄን መልዕክት ከልብ እናገራለሁ! አመሰግናለሁ!

ልዑል አምላክ እግኢአብሔር አገራችንን ይታደግ! አሜን!