April 10, 2019

https://youtu.be/6mo07Ml0Hf8

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ ከኃላፊነታቸው ተነሱ። ኮሚሽኑንን ከዘጠኝ ወራት በላይ በሃላፊነት ሲመሩ የቆዩት ሜጀር ጄኔራል ደግፌ በዲ መነሳታቸው ተገልጿል፡፡

ኮሚሽነሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ሰኔ 19 ቀን 2010 ዓ.ም. ነበር። የኮሚሽኑን የቀድሞ ሃላፊ አቶ ይህደጎ ሥዩምን ተክተው የተሾሙት።

ሜጀር ጄኔራል ደግፌ፣ ከኃላፊነታቸው በድንገት የተነሱበት ዝርዝር ምክንያት ለጊዜው ባይታወቅም፣ ማክሰኞ ሚያዝያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. የደረሳቸው የስንብት ደብዳቤ ግን ‹‹በጡረታ›› የሚል መሆኑ ታውቋል፡፡

ላለፉት ዘጠኝ ወራት ኮሚሽኑን ሲመሩ ቆይተው፣ ከሚያዝያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

Source: Reporter