ምንጭ – ፋና

On Apr 11, 2019

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሶዳን ጦር የሀገሪቱን ብሄራዊ ራዲዮ ጣቢያ መያዙ ተሰምቷል።

ጦሩ በብሄራዊ ራዲዮ ጣቢያው በሀገሪቱ ሁኔታ ላይ ወሳኝ መግለጫ ይሰጣል ተብሎም እየተጠበቀ ነው ።

ከዚህ በተጨማሪም የካርቱም ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዝግ መደረጉ ተነግሯል።

የሀገሪቱ ብሄራዉ የቴሌቪዥን ጣቢያም የሀገሪቱ ጦር በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወሳኝ የሆነ መግለጫ ይሰጣል ሲል አስታውቋል።

በርካታ የሱዳን ጦር ተሽከርካሪዎችም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የሚገኙበት ቤተ መንግስት ከበው መቆማቸውን ምንጮች የገለፁት።

ለወራት ፕሬዚዳንት አልበሽር ስልጣን አንዲለቁ በርካታ ሱዳናውያን የሀገሪቱ ጦር እየወሰደ ያለውን እርምጃ ተከትሎም አደባባይ ላይ በመውጣት ደስታቸውን እየገለፁ መሆኑ ነው የተነገረው።

የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተደረገባቸው እንደሆነ ይታወሳል። ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርእንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1989 ጀምሮ ላለፉት 30 ዓመታት ሀገሪቱን በመምራት ላይ ይገኛሉ።