April 11, 2019

Source: https://fanabc.com

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ነቀምቴ ከተማ ገብተዋል።

በነቀምቴ ከተማ በሚኖራቸው ቆይታም የወለጋ ስታዲየምን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መርቀው እንደሚከፍቱ ይጠበቃል።

በዛሬው እለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሚደረገው በነቀምቴ ከተማ የሚገኘው የወለጋ ስታዲየም ግንባታ በመንግስት እና በህብረተሰቡ ድጋፍ የተከናወነ ነው።

ለግንባታው እስካሁን 196 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን፥ ከዚህም ውስጥ 181 ነጥብ 7 ሚሊየን ብሩ በመንግስት የተሸፈነ መሆኑ ተነግሯል።

ከ30 ሺህ በላይ ተመልካች የመያዝ አቅም ያለው ስታዲየሙ፥ በዙሪያው ለቢሮና ለንግድ የሚያገለግሉ ሱቆችም አሉት።

ስታዲየሙ በፊፋ መመዘኛ መሰረት ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እየተሰራ ሲሆን፥ የእግር ኳስ፣ የቦሊቦልና የቅርጫት ኳስ ሜዳዎች፣ የመሮጫ መምና ሌሎች የመወዳደሪያ ሥፍራዎችን ያካተተ ነው።

በሙለታ መንገሻ