April 11, 2019

‹ወርቅ መፍትሄ ኖሮህ አቅሙ ከሌለህ ተግባራዊ ማድረግ አትችልም››

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ
(ለግዮን መፅሄት)

ያለፈውን አንድ አመት ሙሉ በሙሉ ለመገምገም አልችልም። ምክንያቱም ከተፈታሁ አመት አልሞላኝም። ከዛ
በፊት የነበረውን ለማወቅም የመረጃ አፈና ነበረብኝ። ያም ሆኖ ባለፈው አመት ውስጥ የነበሩትን አብዛኛዎቹን ወራት
በተመለከተ ጥቂት ማለት እችላለሁ።

በእነዚህ ወራት ብዙ ጥሩም መጥፎም ነገሮች በሃገራችን ተከስተዋል። እነዚህን መዘርዘር ትርጉም አለው ብዬ አላምንም። ጥሩዎቹ ተስፋን አመላካች መጥፎዎቹ ተሰፋን አጨላሚ አድርገን ከወሰድናቸው ይበቃል። ትልቁ ቁም ነገር ለውጡ ሲጀመርና ከተጀመረ ጥቂት ወራት በኋላ የነበረው ሃገራዊ ሁኔታ ብዙም ለውጥ ሳይታበት በዛው እንደቀጠለ ነው። ለውጡ ሲጀመር ተስፋ በአንድ በኩል፤ ስጋት በሌላ በኩል ተፋጠው ነበር። አሁንም ይህ ፍጥጫ በተስፋ አሸናፊነት አልተጠቃለለም። በየወቅቱ ስጋት እየጨመረ መሆኑ እየታየ ነው። የዚህ ምክንያት ግን አዲስ ስጋቶች ስለተወልዱ ሳይሆን መጀመሪያውኑ 27 አመታት በሙሉ በወያኔ የተዘረጋው ሁለንተናዊ ስርአት ሃገሪቱን ምን አይነት አደገኛ ሁኔታ ላይ ጥሏት እንዳለፈ ለማየት በለውጡ የመጀመሪያዎቹ ወራት የተስፋ ጉልበት ወይም ስካር አይናችንን አሳውሮት ስለነበር ነው። ለውጡ ወለደው አመጣው የምለው ወያኔ ያልተከለው አንድም አዲስ ችግር አይታየኝም።

በሁሉም መልኩ የ27 አመት የወያኔ አገዛዝ ሃገሪቱን ስር የሰደደ መዋቅራዊ ችግሮች ውስጥ ጥሏታል። ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮቻችን መዋቅራዊ ችግሮች ናቸው። አንዳቸውንም ችግሮች በዋዛ ፈዛዛ፣ በወለም ዘለም ልንፈታቸው አንችልም። የአንድ ሴክተር የአንድ አካባቢ ችግር ከሌሎች ችግሮች ጋር የተሳሰሩ ናቸው። የአንድ ዘርፍ ችግር አንስተህ ለብቻው መፍትሄ እሰጣለሁ ብለህ ብትሞክር ያው ችግር በሌላ ቦታ መፈንዳቱ አይቀርም። ስራህ እሳት በየቦታው ማጥፋት እንጂ እሳት የሚቀሰቅሰውን ምክንያት ማጥፋት አትችልም።

የዚህ አይነቱ አካሄድ አንድ ቀን በየቦታው የሚፈነዳው እሳት ይበዛና የማጥፋት አቅምህ ያንስና የፈራኽው ሁሉንም አወዳሚ እሳት በሃገር ላይ ማንደድ ነው። ይህ እንዳይሆን ከፈለግህ ፖለቲካን ከምር መውሰድ አለብህ። የሁሉም ችግሮች መፍቻ ቁልፍ ከፖለቲካ ችግሮች ጋር በጣም የተቆራኘ በመሆኑ። የምር ፖለቲካ የለበጣ፣ የምኞት የዘፈቃድ ስራ አይደለም። ሀገራችን ያለችበትን ጥቅልና ውሰብስብ አስቸጋሪ ሁኔታ በአግባቡ መረዳት ይጠይቃል።

የሃገሪቱ መሰረታዊ ችግሮች ምንድን ናቸው የሚል ጥያቄ አንስቶ በዝርዝር መልስ መስጠት ይጠይቃል። ይህ ደግሞ ጥናት ዲስፕሊንና ከእውነታ ጋር በድፍረት መፋጠጥን ይጠይቃል። ችግሮችን ማወቅ በራሱ ብቻ በቂ አይደለም። የችግሮቹን መፈትሄ መፈለግ ችግሮቹን ከማወቅ በላይ ትልቁ ፈተና ነው። ይህን ማድረግ ብትችልም ሌላው ከዚህ በላይ፣ በተለይ ከሀገራችን ሁኔታ ስትነሳ አንጥረህ ያስቀመጣካቸውን ችግሮችና መፍትሄዎች ምን ያህሉ በማህበረሰቡ የሚገኝ ተጽእኖ አድራጊ አካላት ይጋሩታል የሚል ጥያቄ ማንሳት አለብህ ።

በኛ ሃገር የተወሰነ የጋራ መግባባት ከሌለ ወደ መፍትሄ ለመሄድ ይቸግራል። የጋራ መግባባት ብቻውን በቂ አይደለም። ሃገሪቱ በሰው ሃይል፣ በመዋእለ ነዋይና በጊዜ እነዚህን ችግሮች ለመፈታት ምን ያህል አሴት አላት? ሌላው ጥያቄ ነው። ወርቅ መፍትሄ ኖሮህ አቅሙ ከሌለህ ተግባራዊ ማድረግ አትችልም። ይህን አቅም ግምት ውስጥ ያስገባ የተግባር ስትራተጂ መንደፍ መቻል አለብህ። በቅድሚያ ሊፈቱ የሚገባቸውና ተራቸውን ጠብቀው መፈታት የሚችሉ ጉዳዮች የትኞቹ ናቸው የሚል ጥያቄ ማንሳት ይኖርብሃል።

ያለፈው አመት የኔ ግምገማ በዋንኛነት የተመለከተው፣ ከላይ ባስቀመጥኩት መነጽር ያለንበትን ሁኔታ ቃኝቶ ከችግር መውጫ የሚሆን ስትራቴጂ የሚነድፍ ሃይል በሃገሪቱ አለመታየቱ ነው። ይህ ሃይል ሁሉንም በሃገሪቱ ያሉ የፖለቲካና ፖለቲካዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ አካዳሚውናን፣ የጥናትና የምርምር ተቋማትን በተለያዩ ጉዳዮች አስተያየት ሰጪ ሆነው ብቅ
የሚሉ የሃገራችንን ምሁራንን በአጠቃላይ ሁላችንንም ይመለከታል። ይህ ያስፈራል። ያሳስባል። የተስፋና የስጋት ፍጥጫ በተስፋ አሸናፊነት እንዲዘጋ በዘዴ በብልሃት በጥናት በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ውሉ ወደለየለት መዳረሻ ለመድረስ እለታዊ እርምጃችንን መቃኘት ይጠበቅብናል። ከዚህ ውጭ ሁላችንም የምንሰራው የየግላችንን ጊዚያዊ እርካታ ከማስገኘት አልፎ ሃገርን ከጥፋት ገደል አፋፍ የሚመልስ አይሆንም።