Source: https://fanabc.com

የኢህአዴግ ምክር ቤት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ መደበኛ  ስብሰባውን ያካሂዳል

On Apr 11, 2019446

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል።

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት ከፊታችን ሰኞ ማለትም ሚያዝያ 7ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ስብሰባውን የሚካሂድ መሆኑን ምክር ቤቱ አስታውቋል ።

ምክር ቤቱ በመደበኛ  ስበሰባውም በተለያዩ አጀንዳዎች  ዙሪያ የሚመክር መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

በዚህ መሰረትም ምክር ቤቱ ያለፉት ወራት የድርጅት ስራዎች አፈጻጸም እንዲሁም በሌሎች ሀገራዊና ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ውይይትና ግምገማ በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል ።