April 11, 2019
Source: https://mereja.com

የማለዳ ወግ … ድምበር ተሻጋሪው አድልኦ !
============================
* ኦኤም ኤን በጅዳ ኮሚኒቲ እርዳታ ሊሰበስብ ነው
* የጅዳ ቆንስል የእርዳታውን ፈቃድ አጽድቆታል
በሀገር ቤት የተለያዩ ተቋማትና በአደባባይ የዘር መድልኦ ተደረገ ሲባል ነገር ላለማክረር ዝምታ የመረጥን ብዙዎች ነን ። መድልኦና ተጽዕኖው ድንበር ተሻግሮ ተመልክተንም ቢሆን ሆደ ሰፊ ሆነን ባሳለፍነው ቁጥር ነገሮች መደራረብ ይዘዋል። ለውጡን ተከትሎ ብዙ የመድልኦ መረጃዎች ተመልክተናል። በእርግጥም ያፈጠጡ ጭብጥ መረጃዎች በሀገሬ ምድር ተመልከተናል። ያም ሆኖ የሚታይ የሚሰማው የኦሮሚያ ፖለቲከኞች ተጽዕኖ ጅዳ ደርሶ ተመልክቻለሁና ሀቁን እንናገረው ዘንድ ግድ ነው ።
የጅዳና የሪያድ ኮሚኒቲ አዳራሾች ለእናት ሀገር ጥሪ ፣ ለአባይ የህዳሴ ግድብ ፣ የተፈጥሮ አደጋ ሲደርስና ዜጎች በአደጋ ሲፈናቀሉ እርዳታ ይሰበሰብባቸዋል። ይህ የሚሆነው የተለያዩ ማህበራትና ድርጅቶች ጥያቄ ቀርቦ ቢሆንም ላንዱ ፈቃድ ሲሰጥ ላንዱ ሲነፈግ ታዝበናል። ይህም ይሁን ብለን አይተን እንዳላየን ዝም ጭጭ ያልንባቸው ጊዜያቶች በርካታ ናቸው።
አድልኦ ደንበር ሲሻገር ያስባለኝ የኦቦ ጁሃር የኦሮሚያ ኔትወርክ ቴሌቪዠን በጅዳ ኮሚኒቲ አዳራሽ እርዳታ ሊሰበስብ ፍቃድ እንደተሰጠው መረጃ ደርሶኛልና ነው። የግል ተቋም የሆነው የቄሮው ዘዋሪ የኦቦ ጁሃር ቴሌቪዥን ጣቢያ በመንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚሲዮን መ/ቤቶች ተጽዕኖ ማሳረፉ ስንሰማ ግን ለምን ? እንዴትስ የቀደመውን የአንድ ዘር የበላይነት የማግዘፍ ስራ በንጉሱ ዶር አቢይ ዘመን ድንበር ተሻግሮ ቀጠለ ? ማለቴ አልቀረም።
የጅዳ ቆንስል መ/ቤት መንገድ በሳተ ሁኔታ ለኦቦ ጁሃር መሐመድ ድጋፍ ሲያደርግ የመጀመሪያው አይደለም። ቆንስል መስሪያ ቤቱ ከውጭ
