April 13, 2019

Posted by: ዘ-ሐበሻ

ያንብቡት ብር ያድርጉት

ታላቅ ቅሬታ በፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ላይ . . . .

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰትንም ተመልክቷል። በፌደራል ደረጃ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንደሌለ እና ከክልሎችም የደረሳቸው ሪፖርት እንደሌለ አስታውቀው ወደፊት እናጣራለን ብለዋል አቶ ብርሃኑ ፀጋየ።

* ምናለ በቁስላችን ላይ እንጨት ባትጨምሩ? ምናለ ከጅምላ ክህደት ይልቅ እንደ መንግስት ሃዘኔታ sympathy እንኳን ቢታይችሁ?!? በራያ ህዝብ ላይ የደረሰ የሰብአዊ መብት ጥሰት አልተፈፀመም ካሉ……

= ሦስት የራያ ወጣቶች በሃምሌ 2/2010 በዋጃ ጥሙጋ ፤ አንድ የራያ ወጣት በወፍላ ኮረም ፣ እንዲሁም ዘጠኝ የራያ ወጣቶች ጥቅምት 11/2011 ዓ.ም በአላማጣ ከተማ ላይ በአጠቃላይ 14 የራያ ተወላጆች በትግራይ ልዩ ሃይል በግፍ አልተረሸኑም ወይ?! ይሄን ጉዳይስ ባለፈው በፌደሬሽን ምክር ቤት በኩል ተዋቅሮ ወደ አካባቢው የተላከው ጊዜያዊ አጣሪ ኮሚቴ ሪፖርት ውስጥ ተካትቶ የለም እንዴ??

= በመቶዎች የሚቆጠሩ የራያ ገበሬዎች ፣ መምህራን እና ወጣቶች ከቀያቸው ፣ ከስራ እና ከቤተሰባቸው ተፈናቅለው በስደት ካምፕ ውስጥ እየተሰቃዩ አይደለም ወይ??

= በዚህ ሰዓት ከአንድ ሺ ዘጠኝ መቶ (1900) በላይ የራያ ሽማግሌዎች ፣ ባለሃብቶች ፣ መምህራንና ወጣቶች በግፍ ታፍነው በትግራይ እስርቤቶች #ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመባቸዉ እንደሆነ አልሰሙም ይሆን??

ክቡር የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ….

= አንዲት የራያ ወጣት በወፍላ ኮረም ከተማ በስድስት የትህነግ ልዩ ሃይሎች ተደፍራ የአእምሮ በሽተኛ እንደሆነች ሰምተው ይሆን?!?

= አራት የራያ ባላ ህፃናት እና ታዳጊዎች ወረቀት አነበባችሁ በሚል ብቻ በጨካኙ ትህነግ ታስረው የስነ ልቦና ችግር እንደገጠማቸውስ ያውቁ ይሆን?!?

= በራያ አላማጣ የወራባያ ገበሬና የሃይማኖት አባት በትህነግ ታፍነው እስር ቤት ውስጥ በደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ ጭንቅላታቸው ውስጥ ደም ፈሶ እዛው እስር ቤት ህይወታቸው ማለፉን እና ልጆቻቸው የአባታቸውን አስከሬን ማስመርመር እንኳን እንደተከለከሉ አልሰሙ ይሆን?!?

= አሁንስ በአላማጣ ፣ በኮረም ፣ በዋጃ ጥሙጋ ፣ በመሆኒ በኩኩፍቶ ወጣቱ እየተደበደበ ፣ ቤት ለቤት እየታፈነና ወላጆች ጭምር እየተሸማቀቁ እንደሚኖሩ ያውቃሉ?!?

= በራያ ወረዳዎች 27 ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ህፃናት በቋንቋቸው የመማር ህገመንግሥታዊ እና ሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመባቸዉ መሆኑን ያውቃሉ?? ኧረ ስንቱ?? በራያ ተወላጆች ላይ የተፈፀሙ እና እየተፈፀሙ ያሉ ግፍ እና የመብቶች ጥሰቶች ስንቱ ተዘርዝሮ ያልቃል??

የፌደራል መንግስትም ሆነ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ስለ ራያ ህዝብ ካልሰማችሁ መረጃዎቹን እነሆ። ለማወጣቸው መረጃዎችም ተጠያቂ ለመሆን ዝግጁ ነኝ!!! አንዳች ሃሰት የለበትም!!! የኔ ጥያቄ ግን እውነት መረጃ ስለሌላችሁ ነው ወይስ አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት. … ሆኖባችሁ ነው??

….. ነው ወይስ የእርስዎ የቤተሰብ አባል ወይም ከእርስዎ ብሄር ሰው ካልሞተ ፣ ካልታሰረ ፣ ብልቱ ላይ የፕላስቲክ ዉሃ ካልተንጠለጠለ፣ አካላዊና ስነልቦናዊ ጥቃት ካልተፈፀመበት ወይም በግዳጅ ከቀየው ካልተፈናቀለ ….ወዘተ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተፈፅሟል አይባልም?!?

….. ነው ወይስ የራያ ህዝብ ኢትዮጵያዊ አይደለም ተብሎ ታስቦ ነው?!? ከሆነም በግልፅ ይነገር!

….. ነው ወይስ የፌደራሉ መንግስት በራያ ህዝብ ጉዳይ ከትህነግ ጋር የገባው ስምምነት ይኖር ይሆን?? ነው ወይስ የራያ ህዝብ የፌደራሉ መንግስት የጦስ ዶሮ ይሆን??

…… ለዛ ይሆን “ጋዜጠኞች” የራያን ህዝብ አንገብጋቢ ጉዳይ ተሳስተው እንኳን የማያነሱት?!? ሊሆን ይችላል!

ዳሩ ግን. . . . . .

የትግራይ ክልል የጠቅላይ አቃቤ ህግን አይሰማም ብቻ ሳይሆን የፌደራሉን መንግስት ለይስሙላ ካልሆነ በቀር እንደ መንግስት አይቀበለውም!!! ይሄው ጌታቸው አሰፋን ይዛችሁ አቅርቡ ብሎ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ትዕዛዝ ካስተላለፈ ወራቶች ቢቆጠሩም ክልሉ ግን አንዳች ምላሽ አልሰጠም። ጭራሽ ወንጀለኞችን አሳልፌ አልሰጥም ብሏል። ጠቅላይ አቃቤ ህግም በዚህ አፍሮ ደብቁኝ ያለ ይመስላል። ጋዜጠኛ ተብየዎቹም አንስተውት ባያውቁም አለያም “ውሾን ያነሳ ውሾ” ተብለው ሊሆን ቢችልም…. ይሄ ጉዳይ ግን የፌደራሉ መንግስት ያለውን የስልጣን የበላይነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ እና ለብዙ ሃገራዊ ቀውሶች መንስዔ መሆኑም ይታመናል።

ሃቅ እንነጋገር ከተባለ በዚህ ሰዓት በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ክልል መካከል functional የሆነ ግንኙነት አለ ማለት አይቻልም!!! አለ ከተባለም የበዛ #እሽሩሩ ብቻ ነው ያለው!!! ለዚያውም ብዙ የማይጠቅም appeasement!!!

ታዲያ እኔም በሃገሬ እና በመንግስት ተስፋ ስለማልቆርጥ እንጅ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቀርቶ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ሆነ የፌደራል ፖሊስ ወደ ትግራይ ክልል ዝር ማለት እንደማይችሉ ሳላውቅ ቀርቼ ሳይሆን የጊዜው ባለስልጣናት ቢያንስ በቁስላችን ላይ እንጨት ባይጨምሩ ለማለት ነው!!!

የዚያን ምስኪን የራያን ገበሬ እንባ እና የራያ ወጣት ጉዳትን የምጮኸውም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ አምላክ ይፍረድ!!!!

ደጀኔ አሰፋ