April 13,2019
Source – Fana

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 05 ፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ መርጠዋል።
ፓርቲዎቹ ዛሬም ቀጥሎ በዋለው የድርድር እና የውይይት ቅድመ ውይይት የአፋር ህዝብ ፓርቲ ሊቀ መንበር የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አድርገው መርጠዋል.
አቶ አደም የምክር ቤቱ ሰብሳቢ ሆነው የተመረጡት 44 የድምፅ በማግኘት ነው።
የኦነግ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ቀጀላ መርዳስ እና የኦም ለህዝቦች ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ግርማ በቀለ ከአቶ አደም ጋር በእጩነት ለውድድር ቀርበው ነበር።
የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት 107 ፓርቲዎች የሚገዙብትን የጋራ እና ተናጥል እንቅስቃሴ መግዣ የቃል ኪዳን ስነድን አተገባበርን ከመከታተል ጀምሮ በፓርቲዎች መካከል የሚፈጠር አለመግባባትን የመፋታት ሃላፊነት አለበት።
በዳዊት መስፍን
