April 12, 2019
በጀርመን የኢትዮጵያውያን የውይይትና የትብብር መድረክ… በአሁኑ ጊዜ በአጠቃላይ በአገራችን እየተካሄደ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት፤
ሀ/ ለውጡ፤ የገጠመውና እየታዩ ያሉት መሬት ላይ ያሉ ችግሮች ምንድናቸዉ? በቲቪ እስክሪን (መስኮት) በለውጥ አራማጁ አካል የሚነገረውና እየሆነ ያለው ሆድና ጀርባ የመሆን ችግር ለምን ይታዩበታል?
ለ/ ማናቸውም ዓይነት ችግር ያጋጥም፤ ወቅቱ ሌላ አማራጭ እንደሌለም ስለሚያሳይ፤ ችግሩን ተቋቁሞ ለውጡ የታሰበለትን ዓላማ ግብ እንዲመታ የእኛ ድርሻ ምን መሆን አለበት? በሚሉትና በአጠቃላይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ አሕመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄዱ ባሉት የለውጥ እርምጃዎች ዙሪያ ተወያይቶና በለውጥ ሂደትም ያጋጠሙ ችግሮችን ገምግሞ ከዚህ የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል። ከመግለጫዉ ባሻገርም ለውጡ የታለመለትን ግብ እንዲመታ መድረካችን የበኩሉን አገራዊ ግዴታ ከመወጣት ወደኋላ ላለማለትም እንደገና ቃል በመግባት ጭምር ነዉ።
… የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ…
