ሚያዚያ 16, 2019

የሃዋሳ ከተማ ዕጣ ፈንታ በአብሮነት ላይ የተመሠረተ ስለሆነ በወቅታዊ ፖሊቲካ ጉዳዮች ለነዋሪዎች ሥጋት ሊሆን እንደማይገባ የደቡብ ክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ተናገሩ፡፡ ሀዋሳ — 

ለአንዱ የተሻለ ዕድል ተሰጥቶ የተቀረውን ወገን መከልከል ታሪካዊ ስህተት መፈፀም ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ሃዋሳን ለሁሉም የምትመች ከተማ ለማድረግ ተደጋግፎ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የከተማዋ አስተዳደር በወቅታዊ የከተማ ፖሊቲካ እንቅስቃሴና በገቢ አሰባሰብ ዙርያ ከከተማው ባለኃብቶች ጋር መክሯል፡፡

ማኅበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የጥላቻና የግጭት መንስዔ የሚሆኑ አስተሳሰቦች በሃዋሳ ከተማ በስፋት እንደሚንፀባረቁና መንግሥት ህግ ተላልፈው በተገኙበት ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወስድም ገልፀዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የሃዋሳ ከተማ ዕጣ ፈንታ

by ቪኦኤk

ዮናታን ዘብዴዎስ

16x9 Image