ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
ሳምሶን መኮንን ሃብተ ወልድ ማን ነው??

በደርግ ለተሰዉ ሰማእታት መታሰብያ መጽሃፍ የተወሰደ፤…..
ሳምሶን መኮንን ሃብተ ወልድ ህዳር 7/1948 ዓ.ም ተወለደ። የመጀመርያ ከዚያም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በ 1966 ዓ.ም አጠናቆ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል ላይ ሳለ፤ ከቅጥር ግቢ ውስጥ በደርግ ካድሬዎች ተይዞ ለእስራት ተዳርጓል። ለጥቂት ጊዜ ከታሰረም በኋላ በሽተኛ መሆኑ በሃኪን ስለተረጋገጠ መለቀቁ ይታወቃል።
በ 1969ዓ.ም ዘመድ ጥየቃ አሰብ ሄዶ ሳለ ፤ በኢሕአፓነት በመጠርጠር እዛ እንደደረሰ ለሁለተኛ ግዜ ለእስር ከተዳረገ በኋላ በግፍ ተገድሏል።
ይሄንን አረመኔ ፋሺስት ደርግ ነው ያሁኖቹ የድል አጥቢያ አርበኞችና የወያኔ አጋፋሪዎች አገርወዳድ የሚሉን!!
ሳምሶን መኮንን ሃብተ ወልድ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!
ነፍስ ይማር ለጀግኖቻችን!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!
