ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
ሳምሶን ወርቃለማሁ ተ/ሃይማኖት ማን ነው??

በቤተሰቦቹ እንደተነገረው፤…..
“ስለ ሳምሶን ወርቃለማሁ ተ/ሃይማኖት መረጃ ያላችሁ የዚህ አምድ ተከታታይና አንባቢዎች፤ የምትሰጡኝ ተጨማሪ መረጃ ለታሪኩ መሟላትና ለቤሰቡም የህሊና እረፍት የሚሰጥ ስለሆነ በቅድምያ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።”…………
ሳምሶን ወርቃለማሁ ተ/ሃይማኖት ከአባቱ ሌትናንት ኮሎኔል ወርቃለማሁ ተ/ሃይማኖት እና ከእናቱ ወ/ሮ ወይንሸት ይመር በየካቲት 23/1946 በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደ። እድሜው ለትምህርት ሲደርስ ከ 1-6 ኛ ክፍል የተማረው በአስመራ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አንደኛ ደረጃ ት/ ቤት ሲሆን፤ 7ኛ ክፍልና 8ኛ ክፍልን በጎንደር አጼ ፋሲል ት/ቤት ፤ ከ9 እስከ 12 ያለውን ደግሞ በጄነራል ዊንጌት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተምሯል።
ሳምሶን ወርቃለማሁ የመጀመሪያ ዓመት ትምህርቱን በ1961 ሓረር በሚገኘው አለም ማያ ኮሌጅ የተከታተለ ሲሆን ከዚየም አዲስ አበባ ይገኝ በነበረው ቀዳማዊ ኅ/ስላሴ ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት (university law school) ገብቶ፤ በየከቲት 66 የፈነዳውን የህዝቡን ትግል ለመቀላቀል ትምህርቱን እስካቆመበት (withdraw) ድረስ እስከ 3 ኛ ዓመት ተምሯል።
ሳምሶን ወርቃለማሁ ከዮኒቨርሲቲ ትምህርቱን ካቆመ(withdraw) በኋላ በ አዲስ አበባ ጊዮርጊሰ አካባቢ የሚገኘው ፍ/ቤት ለአንድ አመት ያህል ሰርቷል።። በ ኢሕአፓነት ተጠርጥሮ በደርግ ነፍሰ ገዳዮች ክትትል ላይ ስለነበር፤ ተደብቆ ከሚኖርበት የድሮ ፖስታ ከሚገኘው ታላቅ እህቱ ቤት አካባቢ ማታ ማታ እየወጣ ይመለስ ነበረ። አንድ ቀን በ 1970 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ማታ እንደወጣ አልተመለሰም።
ቤተሰቦቹ ከሌላ ሰው ባገኙት መረጃ መሰረት፤ ሳምሶን ወርቃለማሁ በጎንደር የኢሕአፓ ተዋጊ ክንፍ የነበረው የኢሕአሠ ተጋዳይ አባል ሆኖ መታገሉን፣ የትግል ስሙም “ይመር” ይባል እንደ ነበረ እንደሰሙ ይናገራሉ።
ሳምሶን ወርቃለማሁ ተ/ሃይማኖት በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!
