No photo description available.

ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

ነስሩ ሢራጅ ዓሊ፤ አሕመዲን ሢራጅ ዓሊ፤ ተቅየ ሢራጅ ዓሊ እነማን ናቸው???…….“ባረመኔው ደርግ የተገደሉት ሶስቱ ወንድሞቼ”

አሁንም በፅናት እየታገለ ባለው ወንድማቸው ካሚል ሢራጅ አሊ እንደተነገረው፤……

“ሶስቱ ወንድሞቼ ባረመኔው ደርግ ተገደሉ”

እኔና ወንድሞቼ በአዲስ አበባ ውስጥ ቤኒን (ሱማሌ ተራ) ተወለድን። የአባታችን ስም አህመድ ኡስበቶ ሲሆን የእናታችን ደግሞ ዘምዘም መሃመድ ባብሴራ በመባል ይታወቃል።

“ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ በኢሕአወሊ በአዲስ አበባ ከተማ ቤኒን ሰፈር(ሱማሌ ተራ)ወጣቱ በኢሕአፓ ዙሪያ እንዲሰባሰብና ሠፈራችን የላብ አደሩ ሠፈር እንደመሆኑ መጠን በኢላአማ ሥር እንዲሰባሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጌአለሁ።

በመጨረሻም በ1970ዓ/ም በከፍተኛ 2ቀበሌ 14ተይዤ ከ3ወር በኃላ ወደ ከፍተኛው ማዕከል እስር ቤት ከፍተኛ 2ቀበሌ 16(ሊሴ ገ/ስላሴ ት/ቤ ጀርባ)ታስሬአለሁ። በአሁኑ ሰዓት ለ33ዓመት በስደት ላይ ብሆንም ዛሬም በፅናት በአካባቢዬ በኢሕአፓ ስር ተሰባስቤ በመታገል እገኛለሁ።

በቀይ ሽብር የተገደሉት ወንድሞቼ፤…

1. ነስሩ ሢራጅ ዓሊ (ሐቢብ ሙስጠፋ)በ1945ዓ/ም ተወለደ። በትምህርት ደረጃው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበረ ሲሆን በኢሕአፓ ውስጥ በማደራራጀትና በቅስቀሳ ስራ ላይ ተሰማርቶ ይታገል ነበር።በ1968ላይ ተይዞ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ለከፍተኛ ስዬል በመዳረጉ የተነሳ ለህክምና ጳውሎስ ሆስፒታል ተልኮ እየታከመ እያለ በኢሕአፓ እስኳዶች እንዲያመልጥና እንዲያገግም ተደርጎ ነበር። በዚያንም ግዜ አንድ ጊዜ ብቻ አግኝቼው ነበር። ከዚያ በኃላ ስለሱ ሐረር ታይቶ ነበር ከሚል ወሬ በስተቀር የደረሰበትን ሳናውቅ ቀርተናል። አሁን በቅርብ የደም ዘመን ቁጥር 2 ላይ በደርግ እንደተገደለ የሚገልፅ ከማንበቤ በስተቀር ይሙት ይኑር አናውቅም።

2. አሕመዲን ሢራጅ ዓሊ በ1947 ተወለደ። በኢልባቦር ክፍለ ሐገር በሥራ ይኖር ላይ በነበረበት ጊዜ በኢሕአፓ ስር ይንቀሳቀስ እንደነበረ እንጂ ብዙ ስለሱ ብዙም የምናውቀው አልነበረም። በመጨረሻም በቀይ ሽብር መገደሉን በሚያቁት ልጆች ስንሰማ ፤ ማልቀስ እንኳን በተከለከለበት ጊዜ ፈልገን ምንም ሳናገኘው ቀርተናል።

3. ተቅየ ሢራጅ ዓሊ አሕመድ በ1951ዓ/ም ተወለደ። በሰፈራችን በማደራጀትና በስኳድነት ይታወቅ ነበር። በመጨረሻም ቸርቸል ጎዳና አካባቢ ተገድሏል።”

ነስሩ ሢራጅ ዓሊ፤ አሕመዲን ሢራጅ ዓሊ፤ ተቅየ ሢራጅ ዓሊ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ናቸው። በጣም እንኮራባቸዋለን!!!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!