ከቴዎድሮስ ዎልደ አበዛ ፌስ ቡክ የተወሰደ

Image may contain: 2 people, people smiling, text



ዶ/ር መረራ ጉዲና <<እኔ ስለ አኖሌ ታሪክ ወያኔ ሃውልት ሰርቶ ሲያስመርቅ እንጂ በኦሮሞ ታሪክ ሰምቸው አላውቅም።>> ኦሮሞ ከዛሬ 50 እና 40 አመታት በፊት ምሁር የለውም (ዘገምተኛ እና ጨለምተኛ) ነው ብል ስህተት አይደለም።

ይህ ባይሆን ኑሮማ ትግሬዎች እንደፈለጉ እና እንደ አመቻቸው የኦሮሞን ህዝብ በፈጠራ እና በውሸት ታሪክ ውስጥ ዘፍቀው አዕምሮውን ባላጦዙት ነበር። ምክናየቱም የኦሮሞን የአመት 100 ታሪክ ያውም የውሸት ታሪክ ፅፈው የሰጡትና የሚተርኩለት በደማቸው ኤርትራዊ የሆኑ ባንዳዎችና ወያኔዎች ናቸው።

ይህንን ልል የቻልኩት ኦሮሞ ምሁር የለውም ለማለት ሳይሆን ከእራሱ ከኦሮሞ አብራክ የፈለቁ የእውነተኛ ልጆቹን እውነተኛ ታሪክ ከማድመጥ ተቆጥቦ በትግሬ እና እንዲሁም ኤርትራዊ ደም ባላቸው ባንዳዎች የተፃፈ የሐሰት ታሪክ ተሸክሞ የሙጥኝ ማለቱ ነው። እውነት እናውራ ከተባለ የወያኔዎች አላማ እና ምኞት አማራን እና ኦረሞን በአገኙት አጋጣሚ እርስ በእርስ ማጫረስ ነው።

አንድ ኦሮሞ ስለ ትግሬ ታሪክ አውቅልሃለሁ ስማኝ ቢለው ፈፅሞ አይቀበለውም። ትግሬ ከትግሬዎች በቀር የማንንም ታሪክ አይቀበልም። አይደለም የፈጠራ ታሪክ ሊቀበሉ ቀርቶ እውነትንም እየሸመጠጡ ነው።
source mariamwit page.

**************************////////*********************
የተሰጡ አስተያየቶች:-
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህር አቶ አበባው አያሌው፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሴት ልጅ በጦርነት ጊዜ የተለየ ጥበቃ እንደሚደረግላት ጠቅሰው፤ በአኖሌ ጡት ተቆርጧል ለሚለው ማረጋገጫ የሚሆን የታሪክ ሰነድ የለም ብለዋል፡፡ አፈታሪኩ ከብሔርተኝነት ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ነው ያሉት አቶ አበባው፤ አፈታሪክን መነሻ አድርጐ ሃውልት መገንባት አይገባም፤ ከዚህ በተጨማሪ ሃውልቱ ጥላቻና ቂም በቀልን ከማንፀባረቅ የዘለለ ፋይዳ የለውም ብለዋል፡፡

የታሪክ ምሁሩና ፖለቲከኛው ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በበኩላቸው፤ የሃውልቱን መገንባት እንደማይቃወሙ ገልፀው፤ ከአፈ ታሪክ የዘለለ ማረጋገጫ ሰነድ አልተገኘለትም፤ ነገር ግን ከታሪክ የመረጃ ምንጮች መካከል አንዱ አፈ ታሪክ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ ጥናት ማድረግ ያስፈልጋል ግን ሰነድ የለውም ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የሃውልቱ መገንባት ጥላቻና ቂም በቀልን ለቀጣይ ትውልድ ያስተላልፋል የሚለውን አመለካከት እንደማይቀበሉት የገለፁት አቶ ቡልቻ ደመቅሳ፤ የታሪኩን እርግጠኛነት ከዩኒቨርስቲ መምህራን መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡ ሃውልቱም በትክክል ድርጊቱን ከማንፀባረቅና ለመማሪያ ከመሆን ባለፈ ጥላቻና ቂም በቀልን አያስተላልፍም ባይ ናቸው፤ አቶ ቡልቻ፡፡

“ሀውልቱ የኦሮሞን ህዝብ 100 ዓመት ወደ ኋላ የጎተተ ነው”
አቶ አበባው መሃሪ (የመኢአድ ሊቀመንበር)

የሃውልቱን መገንባት አጥብቄ እቃወማለሁ፡፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ብዙ ጀግንነት የሰሩ የኦሮሞ ልጆች አሉ፡፡ የሚኒልክ አማካሪ ከነበሩት መካከል ወደ 80 በመቶ የሚሆኑ ኦሮሞዎች ነበሩ፡፡ ጣሊያን በተሸነፈበት ጦርነትም የኦሮሞ ልጆች ገድል ቀላል አይደለም። እነዚህን ታሪኮች ወደ ጎን ገፍቶ አኖሌ ላይ ብሄሮችን ሊያቃቅር የሚችል ሃውልት ከመገንባት ይልቅ የእነዚህን ጀግኖች ሃውልት አቁመው ቢሆን ኖሮ፣ ኢትዮጵያዊነት ይበልጥ ይፀና ነበር፡፡ የታሪክም መገለጫ ይሆን ነበር፡፡ እንደኔ እይታ የአኖሌ ሃውልት የኦሮሞን ህዝብ ወደ ኋላ 100 ዓመት የጎተተ እንጂ ወደፊት ያራመደ አይመስለኝም።

በሌላ በኩል እኔ ይሄ ሃውልት የኦሮሞዎች ፍላጎት ያለበት ነው ብዬ አላምንም፡፡ የፖለቲካ ድርጅቶች ያሰሩት ነው የሚል እምነት አለኝ፡፡ በአጠቃላይ ግን ሃውልቱ ሁለቱ ትላልቅ ብሄር ብሄረሰቦች- አማራና ኦሮሞው እርስ በእርሳቸው ተጋጭተው ትልቅ የነበሩት ትንሽ እንዲሆኑ ታልሞ የተደረገ ሴራ እንጂ የኦሮሞን ህዝብ ለመጥቀም የተደረገ ስራ አይደለም፡፡ ሃውልቱ ለኦሮሞ ህዝብ ጥቅም ሳይሆን ጉዳት ነው የሚያመጣው፡፡ ከሌላው ብሄር ጋር ቅራኔ ውስጥ ይከተዋል፡፡ ከፍተኛ ጉዳትም ያስከትላል፡፡

“ዛሬ የኦሮሞን ህዝብ እየበደሉ ያሉት እነሱ ናቸው”
ዶ/ር ሞጋ ፍሪሣ (የኦፌኮ አመራር፤ ፖለቲከኛ)

ወደ ኋላ ሄዶ ታሪክ ጎልጉሎ ማውጣት ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ምኒልክ ግዛት ለማሰባሰብ ጦርነት አካሂደዋል፣ ይሄ የሚታወቅ ታሪክ ነው፡፡ ዛሬ ላይ ይሄ ተደረገ ብለው ታሪክ ለመንገር የሚሞክሩት እነሱ እነማን ናቸው? ዛሬ የኦሮሞን ህዝብ አንድነት በማናጋት ላይ ያሉ ሰዎች ናቸው እኮ እነሡ! ታሪክን ለመንገር ብቁ አይደሉም፡፡ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል የአኖሌ ታሪክን ማውጣቱ ትርጉሙ ምንድን ነው? ይሄን ለማድረግስ ምን የሞራል ብቃት አላቸው? ለወደፊት በሚገባ የኢትዮጵያ ታሪክ በሚፃፍበት ጊዜ ለሃገራቸው ጥሩ የሰሩ ሰዎች ታሪክ ይወጣል፡፡ እነሱም ዛሬ ወንድሞቻቸውን እየገደሉ እኮ ነው? ታሪክ ለመፃፍ ብቁ አይደሉም፡፡ አሁን ታሪክ ብለው የሚያወሩ ሽማግሌዎችም እውነተኛ ኦሮሞ አይደሉም፡፡ በገንዘብና በጥቅም ተደልለው ነው፣ ታሪኩን ይሄ ነው ብለው የሚያወሩት፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እኮ በጣም ደግ ህዝብ ነው፡፡ በነሱ አካሄድ ቢሄድ ኖሮ፣ ኦሮሞና አማራው ተፋጅቶ ነበር፡፡ በአንድ በኩል ህዝቡን እያፋጀ፣ በሌላ በኩል ደርሰው ታሪክ ነጋሪ ነን ማለት አይገባቸውም፡፡ መጀመሪያ ራሳቸውን ከኢህአዴግ ምርኮ ነፃ ማውጣት አለባቸው፡፡
ታሪኩን አልተመራመርኩም ነገር ግን በጦርነት ጊዜ ብዙ ነገር ይፈፀማል፡፡ ለምሳሌ ድሬደዋ ላይ ብቻ የተፈፀሙ የድሮ ታሪኮችን ጎልጉለን ብናወጣ ብዙ ነገር እናገኛለን፡፡ ያሸነፈው አካል እንዲህ ያለ ነገር መፈፀሙ የተለመደ ነው፣ እነሱ አሁን የሚሰሩትን ጥፋትና ተንኮል ለመሸፈን ሲሉ ነው ይሄን ያመጡት፡፡ ሰዎች እርስ በእርሳቸው በሚናከሱበት ጊዜ ላይ፣ ይሄን ሃውልት መገንባቱ በእሳት ላይ ቤንዚን መጨመር ነው፡፡
ዛሬ መነገር ያለበት አንድነታችንን ስለምንጠብቅበት ሁኔታ ነው፡፡ ዛሬ ከወገኖቻችን ጋር ተስማምተን የሃገራችን የአንድ ኢትዮጵያን ጥቅም የምናስከብርበት ጊዜ መሆን አለበት እንጂ ወደ ኋላ ሄዶ ታሪክ እየመዘዙ እንዲህ ያለውን ነገር መፈፀሙ ተገቢ አይመስለኝም፡፡ ዛሬ እኮ የኦሮሞን ህዝብ እየበደሉ ያሉት እነሱ ናቸው፡፡
************************/******************
ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ