April 19, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/110562

Image may contain: sky

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቻይና ሰራሹን ሲ919 (C919) አውሮፕላን የመግዛት ውጥን እንዳለው ዋና ሥራ አስፈፃሚው ተወልደ ገብረማርያም መናገራቸውን የቻይና ጋዜጦች ፅፈዋል። ዋና ሥራ አስፈፃሚው እንዳሉት የኢትዮጵያ የበረራ መኃንዲሶች ከአምራቹ (Commercial Aircraft Corporation of China) ባለሙያዎች ጋር የአውሮፕላኑን ተስማሚነት ለመመዘን በስራ ላይ ናቸው።

ቻይና ሰራሹ ሲ919 የመጀመሪያ የሙከራ በረራውን ያደረገው ከሁለት አመታት በፊት ነበር። በዚህ ዓመት ሌሎች ሶስት ሲ919 የመንገደኞች አውሮፕላኖች የሙከራ በረራ ያደርጋሉ።

ይኸ ቻይና ሰራሽ አውሮፕላን የቦይንግ 737 እና የኤየር ባስ ኤ320 ተወዳዳሪ እንዲሆን የታቀደ ነው።
የቻይና መንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንዳሉት አምራቹ የቻይና የንግድ አውሮፕላን ኮርፖሬሽን ከ28 ዓለም አቀፍ ደንበኞች 815 ትዕዛዞች ተቀብሏል።
ቻይና በሚቀጥሉት አምስት አመታት በዓለም ከሚበሩ አውሮፕላኖች 20% ቻይና ሰራሽ እንዲሆኑ አቅዳለች። የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ አብዛኞቹ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶች የቦይንግ ሥሪት የሆኑ አውሮፕላኖች በብዛት ይጠቀማሉ።
ንብረትነቱ የፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ስፔን የሆነው ኤየርባስ የሚያመርታቸው A320 እና A330 ከቦይንግ ሥሪቶቹ ቀጥሎ ግልጋሎት ላይ የዋሉ ናቸው።
Via Eshet Bekele – #EthioNewsflash News Monitoring