ሐራ ዘተዋሕዶ
April 19, 2019 L

- ለመኖሪያና ለንግድ የተከራዩ ኹለት ባለ12 ፎቅና ኹለት መለስተኛ ሕንፃዎች ናቸው፤
- በመኖሪያነት የሚጠቀሙበትም ኾነ በንግድ የተሠማሩት ተከራዮች ባሉበት ይቀጥላሉ፤
- በልዩ ፖሊቲካዊ ውሳኔ እንዲመለሱላት መወሰኑን፣ የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፤
- እንዲመለሱላት፣ ያለፉትና ያሉት ቅዱሳን ፓትርያርኮች በተደጋጋሚ ሲጻጻፉ ኖረዋል፤
- በአቡነ ቴዎፍሎስ አመራር፣ እስከ 10ኛ ፎቅ ከገነባች በኋላ ነበር በደርግ የተነጠቀችው፤
- የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 10ሺሕ ቤቶች አንዱ ኾኖ ቆይቷል፤

- ከተወረሱባት ቤቶችና ሕንፃዎች ውስጥ ከ830 በላይ አስመልሳ እያስተዳደረች ትገኛለች፤
- በቀደሙት አባቶች የተሠሩት ሕንጻዎች ኪራይ፣ ከዋነኛ የገቢ ምንጮችዋ አንዱ ነው፤
- በ2010 ታክስን ጨምሮ 81.6 ሚ. ብር ገቢ ሰብስባለች፤ በ2011 85 ሚ.ብር ዐቅዳለች፤
- በአሮጌው ቄራው እቴጌ መስክ፣ 2 ባለ9 ፎቅ ሕንፃዎችን በ50 ሚ.ብር እያስገነባች ነው፤
- “ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቤተ ክርስቲያኗ ባላቸው አክብሮት በቃላቸው መሠረት ያስፈጸሙት ነው፤”
- “የቤተ ክርስቲያንን ገቢ በማጎልበት የልማት ራእይዋን በራስዋ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዙ ናቸው፤” /ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ/
