2019-04-19

አቶ ለማ መገርሳ ዛሬ ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳርነት መነሳታቸውን ተክትሎ በክልሉ የፓርቲና የመንግሥት የሥራ ኃላፊነቶች ሽግሽግ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህም አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከኦሮሞ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ፅህፈት ቤት ኃላፊነታቸው ተሰናብተዋል፡፡
በምትካቸው የፓርቲው የገጠር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ አዲሱ አረጋ መሾማቸውን ከፅህፈት ቤቱ የወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በምን አዲስ ኃላፊነት ላይ እንደተመደቡ ወይም ለመመደብ እንደታሰበ መረጃው አላካተተም፡፡
የኦሮሞነት አቀንቃኙ አቶ ጃዋር መሐመድ የዶክተሩን ስም ሰሞኑን በአሉታዊነት ሲጠቅሱ መሰንበታቸው እና በዶክተሩ ላይ የድብደባ ሙከራ መደረጉ ይታወሳል፡፡
