April 23, 2019
በኦሮሞ ሕዝብና ወጣት ላይ ያካሄደው የሞራል ስብራት፣ የታረክ ማዛባት፣ የትምህርት ውድቀት፣ የኢኮኖሚ ብዝበዛ፣ የፓለቲካ ጭቆና… ወዘተ ታሪክምንጊዜም አይዘነጋውም፡፡

“ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል” የተባለው በኦሮሞ ሕዝብ በውኑ ደረሰ፡፡ ወያኔ የአገራችን ሀብት በሙሉ ተቆጣጥሮ ሕዝባችንን ለማኝ አደረገ፡፡
የፈጠራ ታሪክ አሸከመን፡፡ ሕዝብን ከሕዝብ በሰይጣናዊ ዜዴው በማናከስ የሥልጣን እድሜው አራዘመ፡፡
በሕዝብ ትግል ወደ ወጣበት ዋሻው ቢገባም፤ ጥሎብን የሄደው የታሪክ ኪሳራ፣የኢኮኖሚ ቀውስ የፓለቲካ አለመስከን…ዛሬ ወጥረው የያዙን የታሪክ ፈተናዎች ናቸው፡፡
ይህን ሁሉ ደባ ለማክሸፍ ገና ብዙ ትግል ይቀረናል፡፡ ፕ/ር መረራ ገና ከጠዋቱ የወያኔን ደባ ከተረዱት በጣት ከሚቆጠሩት ምሁራን ውስጥ አንዱ ናቸው፡፡ ዛሬም የወያኔን ተንኮል ለሕዝባችን ከማሳወቅ አልተቆጠቡም፡፡
ፕ/ር መረራ በጣሙን እናመሰግናለን፡፡
