April 23, 2019

የዛሬውን የአሩሲ ሰልፍ በፎቶ ይመልከቱ ሀሳብዎን ይስጡ ሼር ያድርጉ

የቡርቃ ዝምታ በመርዝ የተለወሰ ልብ ወለድ በህወሓት ላቦራቶሪ ሆን ተብሎ የተቀመመ ዓላማው የአማራ ሕዝብን ከኦሮሞ ወንድሙ ጋር ላይገናኝ በማራራቅ ከአንድ ወገን ነኝ ብሎ የሚያስበውን ሕወሓት እድሜ ልክ ስልጣን ላይ ማቆየት ነው። ብቅል ያባውን እንዲሉ ጌታቸው ረዳ ሲጨንቀው ግልፍ ሲለው ያወጣው የእሳት እና ጭድ ታሪክ መሰረቱም ይሄው ነው።

የአኖሌ ሐውልት ቆሞ በዚህም የአንድን ሕዝብ ተጠያቂ ለማድረግ ሲሞከር ግቡ ምንድን ነው? በእርግጥ ለኦሮሞ ታስቦ ነው? በዚህ የሐውልቱ ዓላማ የታሪክ ማስረጃ ባይቀርብበትም በእርግጥ ዓላማው ተፈጸመ የተባለ ታሪክን መዘከር ነው? ብዙ ጥያቄዎችን ማንሳት ይቻላል ቁም ነገሩ በጥላቻ ያበዱና ከዚህም የፖለቲካ ትርፍ ለማጋበስ የቋመጡ እንደ አቶ አዲሱ አረጋ ጉዳዩን መርምረው ሐቁን መቀበል አይፈልጉም።ይልቅ አጋጣሚውን አጣብቂኝ ውስጥ ለገባ የፖለቲካ ስልጣን መንጠላጠያ ለማዋል የሚሯሯጡ ሞልተዋል።

የአኖሌ የጥላቻ ታሪክ ደራሲዎቹ ወያኔዎችና አለቆቻቸው ያንኑ ታሪክ መሰረት አድርጎ 1980 ዓመተ ምህረት በአሶሳ በትግል ላይ ሳሉ በሕዝብ ትምህርት ቤት አማሮች ብለው በዘር የለዩዋቸውን ሰብስበው ህጻናት እና ሴቶች ሳይቀር በመትረየስ አቃጥለዋል። የዚህ ጥቃት ሀላፊነቱን በወቅቱ ኦነግ እና ሻዕብያ መውሰዳቸውና ድርጊቱንም ትልቅ ወታደራዊ ድል ብለውት ነበር ።ይህን የዘር ጭፍጨፋ ማድረግ ለምን አስፈለገ?

የክብር ሬድዮ ይህን የአሶሳ ጭፍጨፋ አስመልክቶ እነ ዶክተር አብይ ወደ ስልጣን ሳይወጡ የጊዜው የኦነግ ሊቀመንበር የነበሩትን አቶ ሌንጮ ለታ ጠይቀናቸው በሰጡት ምላሽ ድርጊቱ መፈጸሙን ነገር ግን ኦነግ ሳይሆን ሌሌች በቦታው የነበሩ ፈጽመውታል ብለዋል።ማንነታቸውን ለመግለጽ ግን አልፈለጉም።የዚህ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ፊልም ካላጠፉት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ላይብረሪ ውስጥ ነበር።ለመሆኑ ይህ የዘር ማጥፋት ለምን ተፈጸመ?

በ1983 ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በሁዋላ እነ አቶ ስዬ መከላከያ ሚኒስትር ሆነው በአሩሲ ፣በአረካ፣በአርባ ጉጉ ፣በወተር፣በበደኖ እና ሌሎችም ቦታዎች የጥላቻው ታሪክ ባለ እዳ የተደረጉ የአማራ ብሄር ተወላጆች ከእነ ቤታቸው ተቃጥለዋል፣አይናቸው እያየ ገደል ተጥለዋል፣በግፍ እና በከባድ ጭካኔ በማንነታቸው ሳቢያ ተጨፍጭፈዋል።

በጊዜው ኦነግና ወያኔ በጋራ እያስተዳደሩ ስለነበር ጭፍጨፋውን ወያኔ ኦነግ ነው ኦነግ ወያኔ ነው ብለዋል።ኦነግ ተገፍቶ ከወጣ በሁዋላ ከጭፍጨፋው የተረፉትን በቴሌቪዥን እያቀረቡ ወያኔዎች ዶክመንተሪ ሰርተዋል።ነገር ግን ያንን ጭፍጨፋ ተቃውመው አማራው ራሱን ማደራጀት አለበት ያሉትን ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በግፍ አስረው አሰቃይተው ለሞት ዳርገዋል። በዚያ ወንጀል ሳቢያ ኦሮሞን ሁሉ ተጠያቂ የሚያደርግ አለ? ለዚህ ሐውልት መች ነው የሚቆመው? ተጠያቂዎቹ ለፍርድ ቀርበዋል? አቶ ሌንጮ እንዳሉት ይህ ጉዳይ በገለልተኛ ወገን ተጣርቶ መቼ ነው የዘር ማጥፋቱን ያቀዱና ያስፈጸሙ ለህግ የሚቀርቡት?

የአኖሌው የጥላቻ ታሪክ መሰረቱ በዚያ ብቻ አላበቃም።በቅርቡ በሰሜን ሸዋ የተፈጸመው የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተድበስብሶ እንዲቀር የተፈለገው ለምንድነው? 27 ንጹሃን ያልታጠቁ ሰላማዊ ሰዎችን ያስጨፈጨፉና የጨፈጨፉ በኦሮሚያ ክልል ሲመሽጉ ለምን ወጥተው ለህግ አልቀረቡም?

የአኖሌን የጥላቻ ሐውልት በማሞካሸት አንገት ለማስደፋትና ወያኔ ሲያደርግ የነበረውን ሕዝብን በጅምላ ለማሸማቀቅ እና ስልጣንን እናጠናክራለን እያስፈራራን እየገደል እያድበሰበስን እንቀጥላለን የሚል እብሪት ያለባቸው ጽንፈኞች የቡርቃን ዝምታ የሚፈልጉት ለታሪክ ነጋሪነት ሳይሆን ለተጨማሪ ሽብር፣ ዘር ማጥፋት በቻሉት ጊዜ ለመፈጸም ከዚያ በሚፈጠር የእርስ በእርስ ግጭት ለመፍጠርና ለማዳከም ነው ይህን ማለት ልመና አይደለም።የኤርትራ ሰላይ የጻፈውን ልብ ወለድ አክብረህ ስለ ኦሮማራ ስታወራ ብትውል የሚሰማህ ማነው? ይህ የዕብደት መንገድ የት ያደርሳል?

አሁን ጉዳዩ ግልጽ ሆኗል ዛሬም ከጥላቻ ማትረፍ የሚፈልገው ሀይል ቦታ እያገኘ እየገነነ መድህን የዛሬው የሻዕብያውን ሰላይ አግንነው የቡርቃ ዝምታ አማራና ኦሮሞን ለማጣላት ገንዘብ በጀት ተመድቦ ከተሰሩ የወያኔ ፕሮጀክቶች አንዱ መሆኑን ያጋለጡትን እውነቱን በአደባባይ የመሰከሩትን አቶ አዲሱ አረጋን ለማውረድ በጫና ቃላቸውን እንዲል ውጡ ዘመቻ የከፈቱ ወገኖች ምንድነው ፍላጎታቸው? ሌላ ዙር ጭፍጨፋ ማካሄድ? ይህን ድርጊት ለሰው ልጅ መብት የሚቆሙ ሁሉ ሊያወግዙት ይገባል ትግሉ ተጀመረ እንጂ ገና አላለቀም ።