April 24, 2019

ከስር ያለው ፎቶ ዛሬ ኦሮሚያ ውስጥ የተደረገውን ሰልፍ ከሚያሳዩት መካከል አንዱ ነው። ባነሩ በርካታ የሀሰት ትርክቶችን ይዟል። አንደኛው የአኖሌ ጉዳይ ነው። ሰልፍ የወጡበትም ምክንያት አቶ አዲሱ አረጋ በእነ ተስፋዬ ገብረ አብ የተደረሰው አኖሌ የተሰኘ የሀሰት ታሪክ የፈጠራ፣ ታሪክ ነው በማለቱ ነው። አቶ አዲሱ አረጋ የፈጠራ ታሪክን አጋለጠ ተብሎ የተጠራበት የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ታዲያ ሌሎች አዳዲስና ገረሚ የሀሰት ታሪኮች ተጨምረውበታል። ለአብነት ያህል በቀይ የተከበበውን ፎቶ መጥቀስ ይቻላል።

በዚህ ፎቶ ላይ የሚታዩት ሱዳን ውስጥ በደል የደረሰባቸው ናቸው። የኦሮሞ ፅንፈኞች የኢትዮጵያ ሕዝብ አምስት ሚሊዮን ባልሞላበት ዘመን ከ10 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተጨፍጭፎብናል ብለዋል። ማጣቀሻዎቻቸው ደግሞ የሀሰት ተራኪዎች ናቸው። ይህ የተስፋዬ ገብረአብ አድናቂና አምላኪ ትውልድ ታዲያ ሱዳን ውስጥ እምዬ ምኒልክ ከሞቱ ከ100 አመት በኋላ የተፈፀመውንም ምኒልክ የፈፀመው አድርገው በፎቶ ይዘውት ወጥተዋል።

እምዬ ምኒልክ ኢትዮጵያ ውስጥ እንኳን ያልነበረ 10 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ጨፈጨፈ ተባለ። ከሞተ ከመቶ አመት በኋላም ሱዳን ውስጥ የተጎዱትን ለእምዬ ምኒልክ ሰጧቸው! በቀጣዩ ሰልፍ በቀጣይ ጊዜ ለሚሞቱትንም እምዬ ምኒልክን ባለ እዳ አድርገው ያቀርቧቸዋል። ይህ የሀሰት ትርክት ከቀጠለ የማንሰማው፣ የማናየው ጉድ አይኖርም መቼም። ሉሲም የገራገሩ አፋር ሕዝብ መኖርያ ቦታ ተገኘች እንጅ አፅሟ የተገኘው ሌላ ቦታ ቢሆን ኖሮ አጤ ምኒልክ ስማቸው መነሳቱ ባልቀረ ነበር። ተመስገን! አፅሟ አፋር ላይ ተገኘልን!

የሀሰት ትርክት ሱስ ሲሆን እንዲህ ነው! ገና ገና ብዙ እንሰማለን፣ እናያለን!