April 25, 2019
እምዬ በብዙ ፍቅርና በትንሽ ልምጭ አንድ ያደረጓትን አገር አፈርሳለሁ ማለት አላዋቂነት ነው!!! ቬሮኒካ መላኩ ሃገረ መንግስት ምስረታ (State formation) የራሱ ትልቅ ሂደት አለው ። ይሄን ታላቅ ሂደት እንደ ተስፋዬ ገብርአብ ያለ ጦጣም ሆነ እንደ ህዝቅኤል ገቢሳ ያለ ግመሬ ሊረዳው አይችልም ። ይሄን ሂደት ለመረዳት Enlightened ( አብራሄ ህሊና ) ያስፈልጋል። የአለም ታሪክ የጦርነት ታሪክ ከመሆኑ የተነሳ የፖለቲካ ልሂቃን “Peace country has no history.” ይላሉ። አብርሃም ሊንከን ታላቋ አሜሪካን በጦርነት ጋግሯል ። በትልቅ ድስት አንተክትኮ አዋህዷል ። አሜሪካኖቹ Melting Pot ነን እያሉ ያንቆለጳጵሱታል ። ። ኦቶቫን ቢስማርክ ጀርመንን ጅእንደ ብረት ቀጥቅጦ እንደ ሰም አቅልጦ አዋህዶ ፈጥሯል። እምዬ ምኒልክ ደሞ በብዙ ፍቅርና በትንሽ ልምጭ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓል። አብርሃም ሊንከን በአንድነት ጠበቃ ደግፎ ባቆያት አሜሪካን አገር ሚኒሶታ ግዛት አልያም ቢስማርክ በተዋደቀላት ጀርመን፤ በርሊን ውስጥ ሆት ዶግ እየላፉ የካልዲስን ቡና እንደ ወረደ እያጣጣሙ ምኒልክ በነፍጥና በመስዋዕትነት ያቆማትን አገር ” ኬኛ ብቻ” እያሉና ለመገንጠል እየታገሉ በመሀይም መንጋቸው “ምኒልክ ጨፍጫፊ ነው” ቢሉ አንድም ርባና ቢስ የትውልድ ፖለቲካዊ ርግማን ነው፤ ሌላም አላዋቂነትን በአደባባይ መግለጥ ነው፡፡ ፓስካል ..“የክሌዖፓትራ አፍንጫ አንድ ኢንች ቢረዝም ወይም ቢያጥር ኖሮ፣ የዓለም ታሪክ የተለየ ይሆን ነበር” (If Cleaopatra’s nose, had been an inch longer or shorter world’s histoy would have been changed) በማለት ጽፏል፡፡ ይሄን ድንቅ ፖለቲካዊ አባባል ወደ እኛ አገር ስናመጣው ” የአፄ ምኒልክ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች በአንድ ሰአት ቢዘገዩ ኖሮ ኢትዮጵያም ዳግም አትመሰረትም ነበር ፣ አፍሪካም የነጮች አህጉር ትሆን ነበር።” በማለት አፋችንን ሞልተን መናገር እንችላለን። “የአፄ ምኒልክ ጥፋት የደንቆሮ ህዝብ ንጉስ መሆኑ ብቻ ነው ። የደንቆሮ ህዝብ ንጉስ መሆን ሃሜት ያመጣል ። የቸሩ ምኒልክን ባህሪ የያዘ ሰው ያፋቅራል እንጅ አያጣላም ። ” ይሄን የፃፈው የ19ኛው ክዘ ምሁር ነጋድራስ ገብረህይወት ባይከዳኝ ነው። . የኦሮሞ ልሂቃንና መንጋቸው አሁንም ኢትዮጵያ እየመራ ያለው ታላቁ ምኒልክ ይመስላቸዋል ። ጧት ላይ ከው ከው ሲሉ ላደናቀፋቸው ድንጋይ ሁሉ ምኒልክን ተጠያቂ ያደርጋሉ። ሰሞኑን በቡርቃ ዝምታ ስም የዚህን ታላቅ ንጉስ ስም በሰልፍ ሲያነሱልን ከረሙ። መቼም በመላው አፍሪካ ከተፈጠሩ የመሪዎች ሁሉ እንደ አፄ ምኒልክ የታደለ ንጉስ ተፈጥሮ አያውቅም ። የእምዬ ምኒልክ እናት ወ/ሮ እጂግአየሁ ምኒልክን ሲፀንሱ ” ዛሬ በህልሜ ከመሀፀኔ ውስጥ አለምን የምታበራው ፀሀይ ስትወጣ ተመለከትኩ ” ብለው ከተናገሩ ጀምሮ እስከ ዛሬዋ እለት ድረስ እምዬ ምኒልክ እንደ ፀሃይ እያበራ ነው ። እንደ ፀሃይ ለአለም የሚያበራው የምኒልክ አምላክ በሰላም ያውላችሁ ። Filed in:Amharic