አለፈ

April 26, 2019

Source: https://fanabc.com

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከጎንደር ዙሪያ ወረዳ ወደ ምዕራብ በለሳ ሰዎችን አሳፍሮ ይጓጓዝ የነበረ አይሱዚ የደረቅ ጭነት ማመላላሻ ተሸከርካሪ ተገልብጦ የ20 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፖሊስ የመንገድ ደህንነት ማረጋገጫ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ኮማንደር ውህብነህ አስናቀ እንደተናገሩት ትናንት ምሽት ሁለት ሰዓት ገደማ አደጋውን ያደረሰው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 -01254 አዲስ አበባ የሆነ የጭነት ተሸከርካሪ ነው፡፡

የጭነት ተሸከርካሪው ከያዘው 25 ኩንታል ጭነት በላይ 40 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ምዕራብ በለሳ ልዩ ስሙ ወራህላ በተባለው ቦታ ሲደርስ መንገድ ስቶ በመገልበጡ አደጋው ደርሷል፡፡

በአደጋው ህይወታቸው ካለፈ 20 ሰዎች በተጨማሪም በ20 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ጎንደር ዩንቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

ተሳፋሪዎቹ የትንሳኤን በዓል ለማክበር ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ይጓዙ የነበሩ ናቸው” ብለዋል፡፡

የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ በማጠራት ላይ ሲሆን ÷ ተሰውሮ የነበረው አሽከርካሪው በህዝቡ ጥቆማ ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተገለጸው፡፡

ህብረተሰቡ ከዚህ መሰል አሰቃቂ አደጋ እራሱን በመጠበቅ በኩል የጭነት ተሸከርካሪን ከመጠቀም በመቆጠብ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ እንዲጓጓዝ ኮማንደር ውብነህ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፡- ኢ ዜ አFiled in:Uncategorized