April 28, 2019

Image may contain: 1 person, text

አማራ ላይ የሚካሄደውን ክኅደት እንፋረዳለን!
*****
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) በትናንትናው (ሚያዝያ18/ 2011 ዓ/ም) ምሽት ዝግጅቱ በጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና አቅራቢነት አንማው አንተነህ (PHD) የተባለ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርን አቅርቦ የአማራን ሕዝብ ኅልውና የሚክድ ዝግጅት ማቅረቡ ይታወቃል።

ምሁሩ የአማራን ሕዝብ ኅልውና በሚክድ መልኩ «አማራ የሚባል የለም» ከማለት አልፈው «በአማራነት መደራጀት አውሬነት ነው» በማለት የአብንን ስም ጠቅሰው ያልተገባ ነገር ተናግረዋል። በዚህ የተነሳም በአማራ ሕዝብ ላይ የተሰራውን የዘር ማጽዳት እና ዘር ማጥፋት ከመካዳቸው በተጨማሪ ለወንጀለኞች ሽፋን ሰጥተዋል ብለን እናምናለን።

ስለሆነም የአብን የሕግ ክፍል ዝግጅቱ የተላለፈበትን ሚድያ ኢሳትን ጨምሮ፣ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌናን እና ተናጋሪውን አንማው አንተነህን (PHD) በሕግ ፊት ለማቅረብ ክስ እያዘጋጀ ይገኛል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከ27 ዓመታት በፊት ጀምሮ የአማራን ሕዝብ ኅልውና የካዱትን ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያምንም አብን የሚከስ መሆኑን እናሳውቃለን።

አማራ ታሪኩን ያድሳል!
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን)
► መረጃ ፎረም – JOIN US