
በለንደን ማራቶን ኢትዮጵያውያን ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል
በለንደን ማራቶን የወንዶች ምድብ ሞስነት ገረመው፣ ሙሌ ዋሲሁን እና ቶላ ሹሬ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ደረጃን በማያዝ አጠናቀዋል፡፡
ኤሊውድ ኪፕቾጌ ውድድሩን 1ኛ በመሆን ሲያጠናቅቅ 2ኛውን ፈጣን የማራቶን ሰዓትም አስመዝግቧል።
እንግሊዛዊው ሞ ፋራህ ኢትዮጵያውያኑን ተከትሎ 5ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።
በሴቶቹ ምድብ ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ ሮዛ ደረጀ 3ኛ ይዛ አጠናቃለች፡፡
በውድድሩ ኬንያዊቷ ብርጊድ ኮሴጊ አሸናፊ ሆናለች።
ቪቪያን ቼሪዮት 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
SOURCE – EBC