April 28, 2019
ሪፖርተር ጋዜጣ

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የመንግሥት ግዥ፣ ንብረት አስተዳደርና ማስወገድ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን፣ የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ፣ የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ኃላፊዎችና ቤተሰቦቻቸው ንብረትና በባንኮች የሚገኝ ገንዘብ ዕግድ ተጣለበት፡፡
የአራቱም ተቋማት ኃላፊዎች ማለትም የመንግሥት ግዥ ንብረት አስተዳደርና ማስወገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ይገዙ ዳባና አራት ቤተሰቦቻቸው፣ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ መንግሥቱ ከበደና ሦስት ቤተሰቦቻቸው፣ የቀድሞ መድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኃላፊ አቶ ኃይለ ሥላሴ ቢሆንና ስድስት ቤተሰቦቻቸው፣ የውኃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ኃላፊ የነበሩት አቶ አታክልት ተካና አራት ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ሌሎችም ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ባለሀብቶች በአጠቃላይ 39 ሰዎች ቋሚ፣ ተንቀሳቃሽና በተለያዩ ባንኮች የተቀመጡ ገንዘቦች ዕግድ ተጥሎባቸዋል፡፡
ሆቤካ ኮንስትራክሽን፣ ጃይንት ኧርዝ ሙቪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ዕቁባይ ዮሐንስ ኮንስትራክሽን፣ ማኅተቤ አርጋቸው ኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አከራይ፣ አብርሃም ኃይሌ ኮንስትራክሽን መሣሪያዎች አከራይ፣ ክፍሌ አብርሃም አጠቃላይ አስመጪና ላኪ ኮንስትራክሽን መሣሪዎች አከራይ ድርጀት፣ ዮናስ ኃይሌ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ አከራይን ጨምሮ በአጠቃላይ 16 ድርጅቶችና ባለቤቶቻቸው ንብረት እንዳይንቀሳቀስ ዕግድ ተጥሎበታል፡፡
የመንግሥት ግዥ ንብረት አስተዳደርና ማስወገድ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ንግድ ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች፣ ከ400,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዥ ጋር በተገናኘ በአጠቃላይ 23,798,376 ብር ጉዳት ማድረሳቸው ተገልጿል፡፡ የመድኃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ ደግሞ የግዥ መመርያን በመተላለፍ የ92,502,316 ብር፣ በውስን ጨረታ የ23,124,196 ዶላርና የ24,833,834 ብር መድኃኒት በመግዛት፣ እንዲሁም ለመድኃኒት መጋዘን ግንባታ በማለት ዕጥፍ ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ በመፈጸም፣ በመንግሥት ላይ ጉዳት