April 25, 2019
አገራችን ኢትዮጲያ የብዙ ጎሳዎችና ቛንቛዎች አገር ናት። ከ 5000 አመት በላይ ታሪክ እንዳላት ብዙ ማስርጃዎች ያሳያሉ (1) ። በዘመናት የአገራችን ግዛት ሲሰፋና ሲጠብ የኖረ ሲሆን እንድዚሁም ጎሳዎችና ቋንቋዎቹም እንዲሁ ሲሰፍና ሲጠቡ ኖርዋል። አብዛኞቹ በአለም ላይ ያሉ አገራት ድንበር በጦርነት ከዚያም በሚከተለው ወጤትና ስምምነት የሚጸኑ የድንበር ወስኖች ናቸው (2) ። አገራችን ኢትዮጲያም በዚሁ ታሪካዊ ሂደት ያለፍች ስትሆን ኢትዮጲያ ብቻ በጦርነት ወሰኗን የመሰርተች የሚመስላቸው ብዙ የተሳሳቱ ወገኖች አሉ። ነግስታቱ ሲጎብዙ፣ ሃብት ሊያፋሩ፣ሃይማኖት ማስፋፋት ሲፈልጉ ግዛታቸውን ብዙ ግዜ በጦርነት አንዳንዴም በጋብቻ በሚመስረት ዝምድና በመዋሃድ ያገር ድንበርና ህዝብ ያሰፋሉ። ይህ ባውሮፓ ና በጥንታዊ የመካከልኛው እንዲሁም የሩቅ ምስራቅ አገሮች ሁሉ የሆነ ነው።
አሁን የምናውቃትን ዘመናዊ ኢትዮጲያ ከነ ዳር ድንበሯና ወስኗ ለቀሪው ትውልድ ያስርከቡት የዳግማዊ አፄ ሚኒልክ መንግስት ነው። አገራችን ስታንስ በዘመነ-መስፍንት ግዜ ( 18ኛው ክ/ ዘምን ሁለተኛው አጋማሽና 19ኛው ክ/ዘመን የመጀመርያ አጋማሽ) የነበርቸው የተበታትኑ የሰሜን አውራጃዋችን ስታክል፤ ስትስፋ ደግሞ ባፄ አምደ ጽዮን ዘመነ መንግስት (14 ክ/ዘምን መጀምርያ አጋማሽ 1314-1344) የአሁኗን ኤርትራ፣ ጅቡቲ፣ ሱማሌን ሁሉ ያከተተች ግዛት ነበረች። በአኩሱም መንግስት ዘመን (ከ 2-10 ክ/ዘመን) ግዛቱ አንዳንዴም ቀይ ባህርን አልፎ ያሁኗን የመን ይጭምር ነበር (3,4,5)።
በተለይ አምስት የሚሆኑ የታሪክ ክስተቶች የጥንታዊት ኢትዮጲያን ህዝብ ጎሳና ቑንቛ እንዲሁም የግዛት ወሰኑን እጅጉን ሲለዋውጠ ችሏል።
የመጀምርያው ያክሱምን ዘምነ መንግስት የወደቀበት 10ኛው ከፍለ ዘመን ባፈ ታሪክ በዩዲት ዘምን ግዜ ሲሆን 960 ይህም የአክሱም መንበር መንግስትና ስልጣኔ ወድቆ ወደ ዛግዌ ስርወ መንግስት የተለውጥችበት ዘመን ነው። በዚያን ግዜ በምእራብና በሰሜን አሁን ሱዳን የነበረውን አገር ሁሉ ቀርቶ የዛግዊ መንግስት ወደ ሮሃ (ላሊበል) ሲከትም ወደ ዳቡብ ግን ግዛቱን አስፍቷል። የዛግዌ ስረወ-መንግስትም የራሱን ስልጣኔ አሻራ ትቶ አልፎል(4, 6)።
ሁለተኛውግዜ1270 ይኩና አምላክ ከሸዋ ንግስናውን ወደ ኢትዮጲያ ንጉሰ ነግስትነት በአቡነ ተክልሃይማኖት እርዳታ ከዛግዌ ስረው መንግስት (10-13 ክ/ዘምን) ከተርከበ ቦኋላ በተለይም በጀግንንቱ ወደር የሌለው ንጉሰ ነግስት አጼ አምደ ፂዮን የኢትዮጲያን ግዛት እጅግ አስፍቶ ታልቅ ግዛት አድርጓት ነበር። በምስራቅ ያሁኑዋ ጅቡትን፣ እንዲሁም ሱማሌን ሁሉ ያካተተ ሲሆን አብዛኛውን በጦርነት ና በሰላም ስምምነት ያስፋፍው ግዛት ነበር። እጅግ ብልህ ስለ ነበር በያዛቸው ግዛቶች ያገሩን ሰው እየሾመ ሃይማኖታቸውን ስይቀይሩ ባህላቸውን እንደያዙ ለማአከዊው መንግስት እንዲገብሩ ያድርግ ነበር። በዚህም የርሱ ግዛት የታወቁትን ያዳል ሱልጣን፣ የይፋት እንዲሁም ዳውሮ ግዝቶች ሁሉ ያካተቱ ነበር (4,5)።
ሶስተኛው ግዜ16ኛው ክፈለ ዘመን መጀምርያ አጋምሽ አጼ ልብነድንግል ዘመን በተለይም ግራኝ አህመድ (አህመድ ኢባን ኢብራሂም አል ጋዚ) የተደርገው ትልቅ ጦርነት 1527-1543 የቀድሞውን ኢትዮጲያ የህዝብ ቑንቋ፣ ጎሳ ና የ ሃይማኖት አስላልፈ በይብልጥ ለውጦታል። በተደርገው 14 አመት ጦርነት የቀድሞዋ ኢትዮጲያ እጅጉን የተቀይርችበት፣ ሃብቷ የተዘርፈበት፣ ቤተ ክርስትያኖትች የተቃጥሉበት፣ የጽሁፍ ታሪኳ የጠፋብት ሲሆን፤ በሌላም በኩል እስልማና ወደ ስሜን ኢትዮጲያ የተስፋፋበት፤ በተለይም ደግሞ ከጦርነቱ ቦሗል ሁለቱ ሃያላን ማለትም ንጉሱና የሓረሩ አሚር በጦርንቱ ደክመው ደቀው ስልነብር በደቡብ ኢትዮጲያ ይኖሩ የነበሩ ኦሮሞ ወገኖቻችን ወደመሃል አገር እስከ መካከልኛው ሰሜን ኢትዮጲያና እንዲሁም በምስራቅ ኢትዮጲያ አስከ ሓርር ግዛት ባጭር ግዜ የፈለሱብት ታሪካዊ ወቅት ነበር። በዚህም ሳቢያ የኢትዮጲያ ህዝብ፣ ጎሳና ቑንቓ እጅጉን ከበፊቱ ተለውጦል(4,5) ።
አራተኛው ዘመን ከ1769 to 1855 ድረስ የቆየው ዘመነ- መስፋንት ኢትዮጲያ በታሪኳ ሁሉ ያንስችበትና የተለያዩ የአውርጃ መሳፍንቶች ከመሃል መንግስት ተንጥለው የራስቸውን አግዛዝ የመሰርቱብት ግዜ ሲሆን፤ የድቡብ ና ምስርቅ ኢትዮጲያ ሙሉ ለሙሉ የተነጠለብት ግዜ ሲሆን፤ ጎንድር ፣ጎጃም ፣ወሎ፣ ሸዋ ና የትግሬ አግር ( ትግርይና ኤርትራ በክፊል ) በተበታትነ የራስ አገዛዝ ወይም እጅግ ልል በሆነ መአክልዊ መንግስት ስር ነብሩ ። ከ ኦሮሞ ወገን የነብሩ ክርስትያን የየጁ ሰዎች ማእክላዊ ኢትዮጲያን ጎንደር ፋሲለደስ ቤተ-መንግስት ተቀምጠው ይገዙም ነበር ። (በይበልጥ የሚታውቁት እቴጌ መነን እንዲሁም ልጃቸው ትንሹ ራስ አሊን ይጨምራል)። ዓፄ ቲውድሮስ (ዳግማዊ) ተንስተው አንደ አገር አስኪ ያደርጉቸው ድርስ የኢትዮጲያ መአክልዊ መንግስት የተዳከምባት የመስፍንቶች አውራጃ ስብስብ ነበርች። እሳቸውን የተከተሉት ነግስታት በተለይመ አጼ የሐንስ 4ኛ ፌድራል በሚመስል አስትዳድር ንጉስ ተከል ሃይምኖትን በጎጃም፣ ንጉስ ሚኒልክን በሸዋ፣ ንጉስ ሚካኤልን በውሎ አድርገው፤ ሰሜኑን ኢትዮጲያ ራሳቸውን ይዘው የኑጉሶች ሁሉ ንጉስ (ንጉስ ነግስት ሆነው ) አገር አስፈትው ጠብቀው ኖረዋል(3, 4)።
ንጉስ ሚኒሊክ እድገታቸው በሸዋ ቤትመንግስት በአባታቸው ንጉስ ሃይለ መልኮት ሲሆን ቦሗላም በምርኮና እስራት ባፄ ቴድሮስ መቅደላ አንባ ታስረው በነበሩበት ጌዜ የ መኳንንቱ ልጆች ከሚሟራቸው የጦር፣ አገር አስተዳድርና አገዛዝ ባሃልዊ ትምህርት በተጨማሪ በፅህፍም እንዲሁም ባፈ-ታሪክም የቀደሞዋን ገናና የኢትዮጲያን ወሰነን ታሪክ ይማሩ የነብሩ ሲሆን፤ በዚያ የሚያልፍ ተማሪ ሁሉ ስልጣን ቢይዝ ያንን ታላቅ ገናና እገርና ታሪክ ለመመልስ ይመኝ ነብር(3)።
ንጉስ ምንሊክ ካፄ ቴዎድሮስ መቅደላ አንባ በ ሃምሌ 1965 አምለጠው ሸዋ ያባታቸው አገር ከገቡ ቦሃላ የሸዋ ንጉስ ሆኑ። አፄ የሐንስም 4ኛ ሃይለው የኢትዮጲያ ንጉሰ ነግስት ሲሆኑ በሳቸው ስር የሸዋና ደቡብ ኢትዮጲያ ንጉስ ሆኑ።
አምስተኛው ዘመን፡ ንጉስ ሚኒሊክ የቀድሞ “ያባቶቻቸው የሆነውን ግዛት” ለመምለስ ይመኙ ነብረና በወቅቱ የነበረው የሃያላን አውሮፓ አገራት ና የቀኝ ግዛት አሰለልፈ እንዲሁም ካፄ ዮሓንስ የሚደርስባቸውን ተጽኖ ለምቛቋም ግዛታቸውን በጦርነትና በሰላም ያስፋፉ ጀምር። አጼ ምንሊክ ያኔ ይናግሩ የነበሩት አዲስ አገር ልግዛ ወይም ላሰልጠን ሳይሆን ‘ያብቶቼ ግዛት የሆነውን ግዛትና ህዝብ ልመስል’ ብለው ነብር፡፤ እርግጥ ነው ግዛት መስፋፍት ተከትሎ የሚመጣ ሃብት፤ የሰው ሃይል አዲስ ምሬት እንዲሁም ጦርነት የሚያስከትለውን ሰቆቃና ጭግር እንዳለ ሁኖ።
በዚህም ሳቢያ ንጉስ ሚንሊክ ካብሮ አደጎቻቸውና ጋድኞቻቸው ከነበሩ የሸዋ ኦሮሞች ከነ ራስ ጎበና ጋ በመሆን አገር ማስፋቱን ገፉብት። በብልሃታቸው የሚታወቁት ንጉስ (ቦኋል ንጉሰ ነግስት አጼ ምንሊክ ዳግማዊ) ግዛታቸውን ሲያሰፉ ሁለት መንገዶችን ይከተሉ ነበር። አንዱ ‘በሰላም ግባና ገብር’ ሲሆን እምቢ ያለውን ደግሞ በጦር ሃይል ያስግብሩት ግዛቱንም ይወስዱብት ነበር። ይሁን እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ነግስታት የተጠቀሙበትና የፈጸሙት ክስተት ነው። በዚህም መስረት ንጉስ ሚኒሊክ በምስራቅ፣ ደቡብ አና ማአክላዊ ምራብ ኢትዮጲያ ዘምተው በውድቴና ግዴታ የአሁኗን ኢትይዮጲያ መስርተዋል። ከሸዋ በስተ ሰሜን ያለውን አገር ሁሉ አፄ የሐንስ መተማ ላይ ከዱርብሾች ጋ ሲዋጉ በማለፋቸው በወቅቱ በሃይልም በማግባባትም መሳፍንቱን ሁሉ ማሳምን የቻሉት እሳቸው ነብሩና ንጉስ-ነግስት ተቀብለው የሁሉ ኢትዪጲያ ገዠ ሆኑ(3)።
ዳግማዊ ሚንሊክ የያኔውው የሸዋ ንጉስ ሆንው አገር ሲያቀኑ በጦርነትም በፍቅርም ብዞዎችን አስግብትዋል። በሰላም አልገባ ካልቸው ሁሉ ጋ ጦርነት አድርግዋል። በጦርንቱም አብዝኞቹ የሸዋ ኦሮሞና አማረኛ ተናጋሪ የነበሩ ወታዳሮች ሲሆን የሚከተላቸው መሪዎችም ብዞዎቹ የሸዋ ኦሮሞዎችና የሸዋ አማርኛ ተናጋሪዎች ነበሩ(3 4)።
መቼም ጦርንት መልካም ነገር የለውም፡፤ ብዙ የሰው ሞትና መቁሰል እንዲሁም የንብርት ዝርፊያና ጥፋት ያመጣል። በተለይ አልገብርም ባለ መሪና ተከታዮቹ ዘንድ ይሄ ይበርታል። የተማረኩ ወታድሮችም በጥንቱ ዘመን እንድ ባርያ ይቆጥሩም ነብር። በጨልንቆ ፣ አሩሲ እንዲሁም በወላይታ የተደርጉ ጦርነቶች ብዙ ደም ፈሶባቸውል። ከሁለቱም ወገን።
ከነዚህ የቀድሞ ታሪካችን የምንማረው፣ ዛሬ ልንወቃቀስበትና ሌላ የቂም ጦርነት ለማድርግ የምንዘጋጅበት ሳይሆን ከአባቶቻችን የተሻለ ሰው ለመሆን ከነሱ መልካምን የምንማርበት፤ መልካም ያለነበረውን ስራቸውን ኣውቀን ተመሳስይ ዽርጊት እንዳይፈጸም ለማድረግ ነው። ይህን ለማድርገ ደግሞ እውነትኛ ታሪክ ላይ ተመርኩዘን እንጂ በውሸትና በተጋነነ ሁኔታ የሚጻፈውንና የሚሰራጨውን ታሪክ የሚባል ልቦልድ ጭምር ከተቀበልን አይበጀንም።
አንዳንዴ በሚያስትዛዝብ መልክ የሚነግረው የሃሰት ታሪክ ለማንም አይጠቅምም። በዚህ ላይ ደግሞ ተማርን የሚሉ ሰዎች የፕሮፓጋንዳ ፖለቲካ አለማ ለመስራት ብለው ታሪክ አጣመው፣ ትልቅ ውሸት ሲቆልሉ አንድም ለሌላ ጥፋት፣ ሌላውን ሰው ለማነሳሳት ሲሆን በሌላ በኩል ሲታይ ደግሞ እነርሱንም ለትልቅ ትዘብት ይጥላቸዋል፡፤
ሚኒልክ 5 ሚሊዮን ኦሮሞ ጨረሱ የሚባለውለው የሃስት ተርት ከነዚህ የፖልቲካ ፕሮፓጋንዳ መካከል አንዱ ነው። ይህን ፕሮፕጋንዳ አልጂዘራን ጨምሮ ተስታፊ ሁነውብታል (8,9) ። ለመሆኑ ያን የሚያክል ህዝብ የሚኒልክ ጦር የሚጨርሰው የኒኩለር ወይም አቶሚክ ቦንብ ሲኖረው ብቻ ነው። አቶሚክ ቦንብ ደግሞ ለመጀምርያ ጦርነት ላይ የዋለው አሜርካኖች በጃፓን ከተሞቸ ሔሮሽማና ናጋሳኪ ላይ 1945 የጣሉ ግዜ ነው። ያም ሆኖ ሁለቱ ጅምላ ጨራሽ ቦንቦች የሞቱቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 250 ሺ ነበር (7)።
የሚኒሊክ ጦር ሚግ 29፣ F16 ወይስ ሚራዥ ወይም ታይፉን ጂቶች ነበሩት ወይስ ያን ያህል ህዝብ የሚያጠፋው በምን ይሆን? እነዚህ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ሁሉ የተሰሩት ሚኒሊክ ከሞቱ ብዙ አምታት ቦኋለ ነው። ኬሚካል ጭስም እንደዚሁ።
የዛን ግዜ ከ 6 000 ጠምንጃ ባላይ የሌላቸውን አጼ የሓንስን ለመድፈር ያልሞከሩ አጼ ሚኒሊክ የሚኖራቸው የቀድሞ ጠብ መንጅ እጅግ ከዛ ያንሰና አውቶማቲክ እንኳ አይደለም። የዛሬው AK-47 ጠብመንጃ ከዚያን ግዜው 50 ጠምንጃ ቢደመር አይሰትካክለውም። 1870 አፄ ሚኒሊክ ያላቸውን የጥንት ቁመህ ጠብቀኝ ጠመንጃ ሁሉ ተደምሮ 3000 አይሞላም ነበር። እንዴት ተብሎ ነው 5 ሚሊዮን ህዝብ በዚያ የሚጨፈጨፈው? ጥይቱስ ከይትኛው ፋብሪካ ነው የሚመርተው? ጦሩንስ የሚያጓጉዙብት የትኛው መርከብ አውሮፕላን እንዲሁም ከባድ ሚኪና ኖሮ ነው?
ከ30 አምታት በላይ የፈጀው የ ኢትዮጲያና ኤርትራ ጦርነት (1961-1991) ከባድ መሳርይ፣ መድፍ፣ ታንክ ፣ ሚሳይል እንዲሁም የጦር አውሮፕላኖች ሄሊኮፕተሮች ሁሉ ተጨምሮ ከሁለቱም ወገን ያለውቀር ከ 255 000 በታች ነው (8) ። እንዴት ተብሎ ነው የንጉስ ሚኒሊክ ጦርነት አብዛኛውን ግዜ ከአንደ ቀን ያነሰ በሰአታትት ጦርነት ያን ያህል በጦርና ጎራዴ እንዲሁም ሗላ ቀር ጠምንጃ ያን ያህል ህዝብ የሚጨርሰው?
በዚያን ግዜ የነበርውን የኢትዮጲያ ህዝብ ሁሉ ቢደምር እንኳ 6 ሚሊዮን በላይ አይሆንም (11)። ያ ጥፋት ተድርጎ ቢሆንማ እንዴት ተብሎ ባሁን ግዜ የኦሮሞ ህዝብ በቁጥሩ ከሁሉ ኢትዪጲያ ህዝብ ሊበልጥ ቻለ?
ስለ ጦርነት ክፋት ካነሳን ዮዲት በ አክሱም ላይ ያጠፋቸው፣ ግራኝ አህመድ በክርስትይኖች ና ሰሜን ኢትዮጲያ ያጠፋው፣ እንዲሁም በኦሮሞ ፍልስት የጠፋው ህዝብና አገር፣ በዘመን መሳፍንት ሁሉ ጦርነት የጠፋው ሰው፣ አጼ ዮሐንስ ጎጃም ላይ የፈጸሙት አሰቃቂ ጦርንትና እንዲሁም የእሳት ማቃጠል ሁሉ ወደር የማይግኝለት ጥፋቶች ናቸው።
ከታሪካችን በመማር አሁን አለም ከደርሰበት ስልጣኔ ና አኗኗር በመመልከት በጋራ ሊያኖርን የሚችለውን የሰው ልጅ፣ ኢትዮጲያውያን ሁሉ እኩል በህግ ፊት የሚሆነውን ስራኧት ለመምስርት መጣር አለብን። አባቶቻችን ከፈጸሙት ስህተት ተምርን በሌላ በኩል ከቅኝ ግዠዎች አገራችንን ጠብቀው አገር ያወርሱንን አያሰብን በተለይ አሁን የተጀምርወን የለውጥ ጉዞ እንዲሳክ ጠንክርን መስራት አለብን።
ካለፉት 50 አመታት እንኳ መማር አለብን፤ ስንት ወገኖቻቸን በህይወት የምናውቃቸው ተገደሉ፣ተሰደዱ ተፍናቀሉ። ይህ ሁኔታ አሁንም ድርስ እየቀጠለ በተለይ የሃሰት ታሪክ እይተነገረ፣ እይተጋነነ ና እይተዋሸ ስልሚቀርብ ጥልቅ ጥፋት በወገኖቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ እየተፈጸመ ነው።
ሓውልት መስራት ለመማርያና ተመሳሳይ ነገር እንዳይፈፀም ከሆነ መልካም ነው፤ ግን በእውነት ለይ የተመሰረተ መሆን ይኖርበታል። የሃውልት መስራት ውድድር ከሆነ ካላይ ለተጠቀሱት ሌሎችንም ጨምሮ ብዙ ሃውልቶች በሙሉ ኢትዮጲያ መሰራት ሊኖርበት ነው። ሃወልት መስራት ወይስ ከድሮው ታሪካችን በሃቅ ላይ የተመሰርተ መግባብት ደርሰን የወደፊቱን ኢትዮጲያ መምስርት ይሻለናል? ያ ነው ትልቅ ሃውልት ለሁሉም የሚበጅ።
የወያኔ አገዛዝ በተለየ ሁኔታ ላግዛዝ ያመቸው ዘንድ ያለፈውን ታሪካችንን አዛብቶ ፣ ቆርጦ, ቀጥሎ፣ ዋሽቶ እንዲሁም አጋኖ የቀረበውን በጥሬው መቀበል እንደ ገና ለሌላ ፍጀት ነው የሚዳርገን። ይልቅስ ስላልፈው ያልኖርበትን ግዜ ታሪክ እልህ ይዞን ስንዳክር ያሁኑንና የምንኖርበትና የወደፊቱን ለልጆቻችን የሚሆነው ግዜና አገር በመልካም መሰረት ላይ ማቆሙን ዘነጋን።
በመደበኛ እንዲሁም በሶሻል ሚዲይ ተጽኖ ፈጣሪ አክቲቭስቶች፣ እንዲህም የታሪክ ተማራማሪዎች፣ የፖለቲካ ሰዎች ፣ወጣቶች ፣ አስተማሪዎች እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎች በተለይም በስልጣን ላይ ያላችሁ ወገኖች፤ ይህን የሃሰትና የቅጥፍት ፕሮፓጋንዳን በማጋልጥ በትክከለኛውን ልንማርበት በሚችል፣ ሊያግብባን በሚችል መልኩ እንዲቀርብ፤ በተለይ ባለፈ ጊዜ ሳይሆን ባሁኑና ለሚመጥው ግዜ ላይ የተሻለ ስራ እንዲሰራ የዜግነትና የ ሰው መሆን ሃላፊንት ና ግዴታ አለብን።
መረጃዎች
- http://www.ethiopianadventuretours.com/about-ethiopia/ethiopian-history.
- https://www.nationalgeographic.org/encyclopedia/border/
- አጤ ምኒሊክ ከ ጳውሎስ ኞኞ መጸሃፍ 1984 አ ም
- የኢትዮጲያ ታሪክ፣ መጸሃፍ ፤ ትርጉም አለማየው አበበ 2006 አ ም
- The Oromo of Ethiopia, 1500–1850, with special emphasis on the Gibe region. Degree: Ph.D. Date awarded: 1983. Author: Hassen, M. Supervisor(s) Oliver R. A , London
- https://en.wikipedia.org/wiki/Gudit
- https://en.wikipedia.org/wiki/Atomic_bombings_of_Hiroshima_and_Nagasaki
- https://en.wikipedia.org/wiki/Eritrean_War_of_Independence