April 29, 2019
Source: https://fanabc.com

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 21 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) 8ኛው የጣና ፎረም በሳምንቱ መጨረሻ በባህር ዳር ከተማ ይካሄዳል።
ፎረሙ የፖለቲካ ሁኔታ ተለዋዋጭነት በአፍሪካ ቀንድ – የሰላም ጅማሮዎችን ማስቀጠል በሚል መሪ ቃል የፊታችን ቅዳሜና እሁድ የሚካሄድ ይሆናል።
የዘንድሮው የጣና ፎረም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል በቅርቡ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የሚካሄድ ይሆናል።
ከዚህ አንጻርም የአፍሪካ የደህንነት ጉዳዮች በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ባለው የፖለቲካ ተለዋዋጭነትና ሰላምን ለማስፈን መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚመክር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።