April 30, 2019
ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኝ እና የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ከሚባል የኤርትራ ተቃዋሚ ፓርቲ የደረሰኝ መረጃ: ጋዜጠኛ ኤሊያስ መሠረት

በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን ልዩ ቦታው ማይ ዓይኒ በሚባል የሚታወቀው የኤርትራውያን ስደተኞች ካምፕ ይገኛል። ካምፑ የኤርትራ መንግስትን ጭቆና በመሸሽ የሚመጡ በሺህ የሚቆጠሩ ኤርትራውያን የሚኖሩበት የስደተኞች ካምፕ ነው።
ሰሞኑን አንድ ሀርድ ቶፕ ታርጋ አ:አ የሆነች ከአዲስ አበባ የኤርትራ ኤምባሲ በመነሳት በውስጡ የሻዕብያ ልዩ ሀይሎች በመጫን፣ ከ 6 በላይ የሆነ የትግራይ ፓሊስ የደንብ ልብስ (ተመሳስሎ የተሰራ) እና በተጨበረበሩ ሰነዶች ጭምር በመያዝ አጭበርብሮ ካምፑ ውስጥ በኢሳያስ አፈወርቂ የሚፈለጉ ሰዎችን ይዞ ጠልፎ አስመራ ለመውሰድ ካምፑ ውስጥ ገብተዋል። ይህ ልዩ ሀይል ቡድን የተሰጠው ተልእኮ ተፈላጊው ኤርትራዊው (የሰንዓፈ ተወላጅ ነው) ከካምፑ ጠልፎ ሑሞራ ለሚጠብቀው ER የሆነች ኮብራ መኪና በማስረከብ በኡምን ሓጀር አድርገው ሰውየውን ለመጥለፍ ነው።
ይህንን ቀድድመው ያወቁበት የትግራይ የፀጥታ ሀይሎች ድራማው እስኪሚጠናቀቅ በጥብቅ እየተከታተሉ ለግዜው በካምፑ ሊጠልፍት የሚፈልጉት ኤርትራዊ ስደተኛ ከቦታው ዘወር እንዲል አድርገውታል። ከአዲስ አበባ የተነሳቹ ሀርድ ቶፕ ማይ ዓይኒ የኤርትራውያን ስደተኞች ካምፕ ያለ ምንም ችግር ብትገባም ቅሉ ተፈላጊው ሰውየ ስላልተገኘ ገብተው ሊወጡ ሲሉ በካምፑ በር እጅ ተፈንጅ ተያዙ።ሲፈተሹ የተጨበረበረ የትግራይ የፓሊስ ልብስና ሰነዶች ተገኘ። ወድያውኑ እነሱን ሲጠባበቅ የነበረ የኤርትራ የስለያ በሑሞራ ቡዱንም በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደረገ።
ሲመረመሩ ከስደተኛ ካምፑ ሰውየው በመጥለፍ የትግራይ ፓሊስ መስለው ልብሱን እንዲለብሱትና ሑሞራ ድረስ ወስደው አስረክበው አዲስ አበባ እንዲመለሱ ሚሽን እንደነበራቸው ቃላቸው ሰጥተዋል።
Written by Garead Yinebeb
