ከማኮነን ተስፋየ ፌስ ቡክ የተወሰደ

ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

ምትኩ ኪቲላ ማን ነው??

Image may contain: 1 person

.
“ይህንን መጣጠፍ የላከልኝ በጊዜው የሠራተኞች ማሕበር መሪ የነበር ዛሬም በስደት በሰሜን አሜሪካ በሕይወት ያለ ወገን የሚያስታውሰውን ያክል ያቀረበው ሲሆን ለምትኩ ኪቲላ ከዘጠነኛ ክፍል ጀምሮ የቅርብ ጓደኛውና በኢሕአፓም ውስጥ በአንድ ህዋስ ውስጥ አብሮ የታገለ ምስክር ነው።”

(ምትኩ ኪቲላ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማሕበር ጠቅላይ ምክር ቤት አባል የነበረ)

ምትኩ ኪቲላ የአንደኛ ደረጃ ትምሕርቱን በወለጋ ክፍለ ሀገር ነቀምት ከተማ አጠናቀቀ። ሰባተኛና ስምንተኛ ክፍል በአዲስ አባባው የልዑል መኮንን ትምሕርት ቤት፤ ከዚያም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በተፈሪ መኮንን የንግድ ሥራ ትምሕርቱን አጠናቋል። በሥራው ዓለምም በንግድ ባንክ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ዋና መሥሪያ ቤት ቁጠባ ክፍል ከ1964 እስከ 1968 ዓ.ም. አገልግሏል። ምትኩ በሥራው ዓለም እያለ ማታ ማታ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምሕርቱን የቀጠለ ሲሆን ሦስት ወንድሞቹን ሰብስቦ ያስተምር የነበርና፤ ቤተሰቦቹንም ይረዳ የነበር ጠንካራ ጓድ ነበር።

ምትኩ የንግድ ባንክ ሥራ በጀመረ አጭር ጊዜ ውስጥ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ዋና መ/ቤት የቁጠባ ክፍል የሠራተኞች ማሕበር ተጠሪ እንዲሆን በሠራተኞች ተመርጦ ማገልገል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የባንኩ ሠራተኞች ማሕበር ጠቅላይ ምክር ቤት አባል ሆኖ በ 1968 ዓ.ም. መጀመሪያ የደርግን ፋሺሽታዊ አገዛዝ በመቃወምና ኢሕአፓ ይጠይቅ የነበረውን የጊዚያዊ ሕዝባዊ መንግሥትን በመደገፍ በጊዜው የኢትዮጵያ ሠራተኞች አጠቃላይ ማሕበር (ኢሠአማ) በጠራው የሥራ ማቆም አድማ ላይ የባንኩ የሠራተኞች ማሕበርም ተሳታፊ በመሆናቸውና፤ የሥራ ማቆም አድማው ካለቀ በኋላ በጊዜው ተሳታፊ በነበሩ የሠራተኞች ማሕበር መሪዎች ላይ በደርግ ነፍሰ ገዳዮች ይወሰድ የነበረውን የግድያ እርምጃዎች አምልጦ የደርግ ሰላዮች እያደኑትም እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ በህቡዕ ሆኖ በኢሕአፓ በተለያዩ እርከኖች ውስጥ ሆኖ ያታገለ ጠንካራ ገድ ነበር።

በጊዜው ኢሠአማ በዚያ የሥራ ማቆም አድማ ሳቢያ መሪዎቹ እነ ማርቆስ ሐጎሥ ታድነው የተረሸኑበት ጊዜም ስለነበር በሕቡዕ በተመሠረተውም ኢላአማ (የኢትዮጵያ ላባደሮች አጠቃላይ ማሕበር) ውስጥም ያገለገለ ሲሆን ፤ደርግ የሚፈልገው መሆኑን የሚያሳይ ፎቶ ተበትኖም በደርግ አፍንጫ ሥር ማደራጀትና ማታገሉን የቀጠለ የቁርጥ ቀን የኢሕአፓ ጀግና ነበር። በጊዜው ከኢሕአፓ ተገንጥለው ወጥተው ለደርግ ይጠቁሙ በነበሩ አንጀኞች ጥቆማ መሠረት ተይዞ በማዕከላዊ ከታሠረ በኋላ የሚወዱት ወገኖች ምግብ ለማቅረብ ወደ ዕሥር ቡቱ ሲሄዱ ያኔ ደርግ ያደርግ እንደነበረው እርምጃ እንደተወሰደበት ተነግረው በደርግ ግፈና አሥተዳደር የተገደለ እንደሆነ ታውቋል።

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዚያን ጊዜ ሕይወታቸውን ካጡ ወገኖች መካከል፦ 1. ከአዲስ አባባ – አበራሽ ወርቁ – ጌታቸው ተከስተ ( በማዕከላዊ አይኑን አውጥተው አሰቀይተው የገደሉት) – ፈቀደ ሽፈራው የማሕበሩ ገንዘብ ያዥ የነበረ (አዲስ አበባ ውስጥ በሕቡዕ ሲያደራጅ የነበረ) – ምትኩ ኪቲላ (ከዚህ በላይ ታሪኩ የተጻፈው) – ፋጡማ ሱሩር 2. ከጅማ – ሽመልስ አባተ 3. ከድሬ ዳዋ የታሠሩና የተገደሉ – ግርማ ብሥራት – መስፍን በቀለ – መክብብ ታደሰ – ጌታቸው መኮንን – ሥዩም ገ/ጻዲቅ – ሙሉጌታ ጋዲሳ – ዮናስ ኢብራሒም

ምትኩ ኪቲላ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!