የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ በዓለማችን ምንም ለዉጥ ያላሳየች የመጨረሻዋ ሃገር ኤርትራ ናት ሲል ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ማኅበር አስታወቀ። ማኅበሩ በቅርቡ በጀርመን መዲና በርሊን ላይ ይፋ ባደረገዉ ጥናት እንዳሳወቀዉ ፤ ኤርትራ ባለፉት 10 እና 15 ዓመታት በፕሬስ ነፃነት ላይ ምንም አይነት መሻሻልን አላሳየችም።
አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:51
ባለፉት 10 እና 15 ዓመታት ኤርትራ በፕሬስ ነፃነት ምንም መሻሻልአላሳየችም
የፕሬስ ነፃነትን በተመለከተ በዓለማችን ምንም ለዉጥ ያላሳየች የመጨረሻዋ ሃገር ኤርትራ ናት ሲል ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች ማኅበር «Reporters Without Borders» አስታወቀ። ማኅበሩ በቅርቡ በጀርመን መዲና በርሊን ላይ ይፋ ባደረገዉ ጥናት እንዳሳወቀዉ ፤ ኤርትራ ባለፉት 10 እና 15 ዓመታት በፕሬስ ነፃነት ላይ ምንም አይነት መሻሻልን አላሳየችም። አሁንም ለዓመታት የታሰሩት ጋዜጠኞች አልተፈቱም፤ ቤተ-ዘመዶቻቸዉም የታሰሩበትን ቦታ አያዉቁም። ወጣት የሆነዉ አብዛኛዉ የማኅበረሰብ ክፍል በብሔራዊ ዉትድና ተጠምዶአል፤ በ 21 ኛዉ ክፍለ ዘመን የሃሳብ እና የመረጃ መለዋወጫ የሆነዉን የኤሌክትሮኒክስና የኢንተርኔት ተጠቃሚ አይደለም። የዓመቱ የሚከበረዉ የፕሬስ ነፃነት ቀን የፊታችን አርብ በመላዉ ዓለም ታስቦ ይዉላል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ