May 2, 2019

የህግ ጥሰት ፈፅመዋል ከተባሉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል 3ቱ ክስ ተመሰረተባቸው፡፡

በኢደስ አበባና ዙሪያው ከሚገኙ 167 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል 46ቱ የተለያዩ ህጎችን ጥሰው ሲሰሩ መገኘታቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
ከመካከላቸው ሦስቱን ህግ ፊት አቁሚያቸዋለሁ ብሏል፡፡

ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ9 ወር የስራ ክንውን ሪፖርት እንደተመለከትነው በግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ኮሌጆች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጓል፡፡

በፍተሻው መሰረት 46 ያህሉ የተለያዩ የህግ ጥሰቶችን ፈፅመዋል ያለ እውቅና ፈቃድ ተማሪ መዝግበው ሲያስተምሩ የተገኙ 27፣ በርቀት ፈቃድ የመደበኛና በመደበኛ ፈቃድ የርቀት ሲያስተምሩ 4 ተቋማት ተገኝተዋል፡፡

የእውቅና ፈቃድ ሳያድሱ የሚያስተምሩ 6፣ ያልተሰጣቸውን የደረጃ ስያሜ ለምሳሌም ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ሳይሆኑ በስያሜው የሚጠቀሙ 3 የግል የትምህርት ተቋማት ተገኝተዋል ተብሏል፡፤

የህግ ጥሰት ፈፅመዋል ከተባሉት መካከል ክስ ከተመሰረተባቸው ባሻገር 24 ያህሉ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ ተደርጓል፡፡ በሌሎች ላይ ደግሞ ተጨማሪ ማጣራት እየተደረገ ሲሆን እርምጃም ይወሰዳል ተብሏል፡፡

Sheger FM