
ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ የ2019 የዩኒስኮ የሰላም ተሸላሚ ሆኑ
ድርጅቱ ጠቅላይ ሚንስትሩን የሸለመዉ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነፃነትን ለማስፈንና ሰላምን ለማምጣት ባደረጉት አስተዋጽኦ ነዉ።የጠቅላይ ሚንስትሩ ሽልማት ይፋ የሆነዉ በአዲስ አበባ ከተማ የአፍሪቃ ህብረት አዳራሽ እየተከበረ በሚገኘዉ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ላይ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አድሪ አዙላይ አማካኝነት ነዉ።
ሽልማቱ የዩኒስኮ ፊሊኒክስ -ቦኒይ የሰላም ሽልማት በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከጎርጎሮሳዊዉ 1999 ዓ ም ጀምሮ ዓለም ዓቀፍ ግጭቶችን በመፍታት ዉይይትንና ድርድርን በማስቀደም ሰላም እንዲሰፍን አስተዋፅኦ ላደረጉ ከሃያ በላይ ዓለም ዓቀፍ ግለሰቦች መሸለማቸዉን የጠቅላይ ሚንስትር ፅ/ቤት በፌስቡክ ገፁ አስፍሯል።
► መረጃ ፎረም – JOIN US