May 2, 2019
Source: https://mereja.com/tv/watch.php?vid=56f423e48
ማንነትን መሰረት አድርገው የተደራጁ ፓርቲዎችን ለማጥፋት የሚደረገው ሽርጉድ ችግር ያስከትላል – ዶ/ር ደብረፂዮን

የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል በወቅታዊ ክልላዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሰጡት መግለጫ የፌዴራል ስርዓቱና ህገመንግስቱ አሁንም ላይ አደጋ ነው ብለዋል፡፡ ማንነትን መሰረት አድርገው የተደራጁ ፓርቲዎችን ለማጥፋት የሚደረገው ሽርጉድ ችግር ያስከትላል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተደረገው የሰላም ሂደት የፌደራል መንግስት እንጂ የትግራይ መንግስት አልተቀበለውም እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ ነዉ ተባለ፡፡
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተደረገው የሰላም ሂደት የፌደራል መንግስት እንጂ የትግራይ መንግስት አልተቀበለውም እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው አሉ የትግራይ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል፡
ርዕሰመስተዳድሩ ይህንን የተናገሩት በወቅታዊ ክልላዊ እና ሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነዉ፡፡
በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ከኤርትራ ጋር የተጀመረውን ግንኙነት በሚመለከት ህወሓት ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ለኢህአዴግ ሲያቀርበው የነበረ አጀንዳ ነበር ያሉት ዶ/ር ደብረፂዮን ፤ኢህአዴግም ጉዳዩን በትኩረት በማየት ሁለቱም ሃገራት መሪዎች የጀመሩት ግንኙነት ይበልጥ ወደ ህዝብ መውረድ እንዳለበት የክልሉ መንግስት ያምናል ብለዋል፡፡
በመሆኑም በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የተደረገው የሰላም ሂደት የፌደራል መንግስት እንጂ የትግራይ መንግስት አልተቀበለውም እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተቢስ ነው ብለዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በሃገራቱ ግንኙነት ከፌደራል መንግስት የተለየ አቋም የለንም ሲሉም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
እንደውም የትግራይ ህዝብ እና መንግስት ከኤርትራ ህዝብ እና መንግስት ጋር ለማደግ የላቀ ፍላጎት አለው ተብሏል፡፡
የሃገሪቱ ወቅታዊ አቋም በሚመለከትም ዶ/ር ደብረፂዮን የፌዴራል ስርዓቱና ህገመንግስቱ አሁንም አደጋ ነው ብለዋል፡፡
ማንነትን መሰረት አድርገው የተደራጁ ፓርቲዎችን ለማጥፋት የሚደረገው ሽርጉድFiled in:Amharic
Ethiopia: Tigray Region President Debretsion Gebremichael expresses disappointment