April 29, 2019
ለረዢም አማታት ትችቶቼን የተከታተላችሁኝ ሁሉ ፈረንጆች “ቦልድ” የሚሉት “ፈጣጣ” ትችቶችን የምተች ተቺ መሆኔን ታውቃላችሁ። በዚህ ባሕሪየ ብዙ ጠላት አፍርቻለሁ።ደፋር እንጂ አጎብዳጅ አለመሆኔን እጅግ ደስ ይለኛል። በኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ተወዳጁና ተጠቃሚው አጎብዳጁ እና አጭበርባሪው ክፍል እንጂ ደፋር እና ቅን ተወዳጅም ተሞጋሽም እምብዛ አይደለም። ይህንን አውቃለሁ። ታሪካችንም ይህንን ይነግረናል።
አጼ ቴዎድሮስ በደፋርነታቸው ብዙ ጠላት ተገንብቶባቸው መጨረሻ እርሳቸውን/ንጉሡን/ ያጠቁ መስሎአቸው አገሪቷ በወራሪው እንግሊዝ እንድትደፈር ተባባሪዎች ሆነው “እርሳቸውም ቅርሶቻችንም እና የንጉሡን ባለቤት እንዲሁም ልጃቸው ለሕልፈተ ሞት ለመዳረጋቸው” የቴዎድሮስ ጠላቶች ዋነኞቹ ተጠያቂዎች ነበሩ።ንጉሡ ያቀዱት ሰፊ ዕቅድም ባጭሩ ተቀጨ።
በትግሬነቴ ስለ ትግራይ ማሕበረሰብ ያለኝን ትችት ከሌሎቻችሁ የተለየ መሆኔንም ታውቃላችሁ። የትግራይ ሕዝብ እራሱ ነፃ ለማውጣት ሳይፈልግ ‘ታፍኗልናእኛነፃእናውጣው’ እያሉ የሚፏክቱ ምሁራን በጣም በርካታ ናቸው (98%ማለት በሚያስችል)። ለዚያ ሕዝብ ምን እናድረግለት? እያሉ ሕዝቡ ነፃ አውጡኝ ብሎ ሳይጨነቅ ስለ ሕዝቡ የሚጨነቁ ሰዎች ገጥመውኛል። በፖለቲካ ወቅቴ ውስጥ እንዲህ ያለ አስቂኝ ገጠመኝ (አስተሳሰብ) ያስገረመኝ የለም።
በንጽጽሩ እኔም እንደ አጼ ቴዎድሮሰ ጠላቶቼ እኔን ያጠቁ መስሎአቸው የምጽፋቸው ሃገራዊ ትችቶች በየሚዲያው ለሕዝብ እንዳይሰራጩ የተቻላቸውን ያህል ለበርካታ አመታት በማገድ ጥረዋል። አንዳንዶቹም ሲነሽጣቸው ሊንክ ያደረጉትን (ያያዙትን) የድረገጼ ማስፈንጠሪያቸው ሰርዘው ከድረገጻቸው ማስፈንጠሪያ ሊስት (ዝርዝር) በማስወጣት ከድረገጻቸው ያጠፉታል። ከሚያስቁኝ ብቻ ሳይሆንየሰዎችትንሽነት ምን ያህል መሆኑንም ከሚገርመኝ አንዱ ከትግሎቼ ዘመን ገጠሞቼ ያየሁት ክስተት ነው።
ይህ ክስተት ኢትዮጵያውያንን በደምብ የሚገልጽ “የቂመኛ ፤ የድንቁርና እና የግልፍተኛ ባሕሪ” መለያ ነው። ኢሳት የተባለው “ታማኝ በየነ” በበላይነት የሚያስተዳድረው ጣቢያ በቅርቡ በሁለት እውቅ ጋዜጠኞች ማለትም በቴዎድሮስ ጸጋየ (የርዕዮት ሚዲያ አዘጋጅ) እና የኢሳትዋ ጋዜጠኛ ወ/ት ርዕዮት አለሙ ላይ የፈጸመው የመናገር መብት አፈና ጉልህ ማስረጃ ነው። “በታማኝበየነ”! “በታማኝበየነ”! “በታማኝበየነ”!ስተዳደር!
ከዚያ አስታክኮ በጉራጌው ምሁር በዶ/ር በዕድሉ ዋቅጅራ እና እርሱን በሚመስሉ “ጠባብ ብሔረተኞች” በቴድሮስ ጸጋየ ላይ የተሰነዘረው “ዘረኛ ዘለፋ” የሚያሳየን ክስተት “ኢትዮጵያውያን” ከቂም፤ ከዘር እና ከአጎብዳጅነት ባሕሪ ገና ያልወጣን መሆናችንን የሚገልጽልን ክስተት ነው።
ለዚህ ነው እኔም ለረዢም አማታት በዛው በአፈና ብትር እየተቀጠቀጥኩ የዘለቅኩት። ለ27 አመት ያየነው የምሁራን ውድቀት ደጋግሜ፤ ደጋግሜ ስለተቸሁበት ለአንባቢዎቼ አዲስ አይሆንባችሁም። ምሁራኖች እና ድንገት የተከሰቱ የአገሪቱ መሪዎች የሚረባረቡት አፍ መፍቺያቸው ያደረጉት በሞጉእ መውቀጫ “አገሪቱንመውቀጥ” ነው። ወጣቱም በዚያወረርሺኝተበክሎ ‘ታሪኳን ባሕልዋን ፤ ሃይማኖትዋን ማንኳሰስ ነው።
ካንዱ ሃይማኖት ወደ ሌለ ሃይማኖት መገለባበጥ ፤ ታሪክ ለፖለቲካ ፍጆታ ማጣመም ፤ ሰንደቃላማን ማርከስ… የተለመደ ሆኖ በደናቁርት ሥልጣኔ ወረርሺን ተበክሏል።
ዛሬም እንዳለፈው በብልጣብልጡ አብይ አሕመድ “አሳሳች ስብክት” ከድጡ ወደ ማጡ ተጃጅለን ሕዝባችን ባልተጠበቀ የድረሱልን “እሪታ” ውስጥ ከትተነዋል።
አብይ አሕመድ የሚመራው የአናርኮ ፋሺስቱ ስርዐት አወዳሾች እና ጠበቃዎች የስርዓቱ ወንጀሎች እንዳይጋለጡ “በአወዳሽነት” በመተባበር እንቅፋት እየሆኑ እንደሆነ ጥቂትሃገራውያንተቺዎችጥቂትቢሆኑምብርቱማስረጃቸውንይዘውቢከራከሩም በራሱ በአብይ አሕመድም ሆነ በደጋፊ ጋዜጠኞቹ እና ምሁራኖቹ ተባባሪነት እውነት እየታፈነ ይገኛል።
ሃገራውያኖቻችን እየደረሰባቸው ያለው የማስፈራራት ውርጅብኝ ሁሉም ያደመጠው ሃቅ ነው። እስክንድር እና አዲስ አበቤዎችን፤ቴድሮስ ጸጋየን፤ የኢሳትዋ ርዕዮት ዓለሙን….እና አገር ውስጥ በሚኖሩ ሃገራውያን ላይ እየደረሰባቸው ያለው ወከባ ፤ ዘለፋ ፤ እስራት ፤ ዛቻ እና አፈና ማየት የወቅቱ የተለመደ ክስተት ነው። የአናርኮ ፋሺሰቱ ሥርዓት አስተዳዳር ያልተጠበቁ ክፉ ክስተቶችን በደበቃቸው ባሕሪዎቹ ሳያስበው ድንገትእየፈነዱበት ይፋ እየወጡ ነው። በጣም በርካታ ክስተቶችን እያሳየን ነው።
ስለ አዲሱ የአማራ “አፓርታይድ አስተዳደር/ክልል/ መሪው ከታች ስለምጠቅስ አስቀድሜ ይህንን ልበል። ሰዎች ስርዓቱንም ሆነ አድርባይ ምሁራኖችን “በስድብ መግለጽ” ነውር ነው ይሉናል። ስድብ ዝምብሎ አልተፈጠረም። መጽሐፍ ቅዱስም፤ ቁርኣንም ስድብ ይጠቀማሉ። ስድብ የተፈጠረው ለጉዳይ ነው። ጥፋት እየፈጸሙ፤ ተው ተብለው ሳያርሙ መልሰው አንተኑን የሚዘልፉ፤ ሕዝብን እያሳሰቱ አገረቱ በምትዋዥቅበት ምንገድ እንደትሄድ አስተዋጽኦ የሚያደርጉ የአምባገነንደላሎችንለመግጽየተፈጠረየመገለጫመንገድ ነውና በዚህ እንስማማ። ቅዱሳን መጻሕፍትን አንብቡ! የስድብ ተቀባይነቱን ታያለችሁ።
አማራውን በአዲስ መንፈስ እመራለሁ ብሎ ምሎ ተገዝቶ የመጣ አጎብዳጁ “አምባቸው መኮንን” የሰሞኑን አስገራሚ ንግግሩን ሰምታችኋል። እርሱና አቶ ንጉሱ ጥላሁን የተባሉ እነኚህ ሁለት አማራዎች ‘ሕገ ምንግሥቱ አግላይ ነው፤ አንዱ ባለቤት ሌላው እንደ የእንጀራ እናት የሚያይ ሕገ መንግሥት ነው” ፤ እያሉ ሲኮንኑና ሲመጻደቁ ተራማጆች መስለው ‘ጉራቸውን’ ሲነዙ ከርመው ቀስ በቀስ ከምላሳቸው የሚደመጠው አድርባይነትን ስትመለከቱ የሚገርሙ ሰዎች ናቸው።
ልክ እንደ አብይ አሕመድ እነዚህ ሰዎችም የደበቁት ባሕሪያቸው ሳያስቡት ድንገት ከውስጥ ፈንድቶ ሲደመጥ ማንነታቸውን ሲገልጹልን ሰምተናቸዋል። በቅርቡ ዶ/ር አምባቸው መኮነን የተባለው የአማራ “ክልል” ፕረዚዳንት “አዲስ አባባን በሚመለከት” ተጠይቆ የኦሮሞን ልዩጥቅም ለማስጠበቅ እስከመጨረሻ እንታገላለን” ብሎን ቁጭ!
ሙሁራኖቻችን ማሕበረሰብን በአግባቡ መምራት የሚያስችል የትምሕርት ክምችት ቢኖራቸውም፡ ምክንያቱ ባልተፈተሸ ባሕሪያቸው ምክንያት “ለመጣ አዲስ ገዢ” እያጎበደዱ ያልነቃውን ማሕበረሰባችን ከድጡ ወደ ማጡ እየከተቱት የጠየቅነውን ፍትሕ የማንገሥን ጥያቄ እንዲዘገይ ጎታች ሃይል ሆነዋል።
አብይ አሕመድ የተማረ ነው። ስትመለከቱት ግን ከ14 አመቱ ጀምሮ አስካሁን ድረስ ለወያኔ ሥርዓት በማገልገል ያደገ ወጣት ነው። ልዩ የሚያደርገው የዚህ ወጣት መሪ ባሕሪ ግን በራሱ አንደበት የነገረን “የአመራር ብቃት ችሎታ” ሳይሆን “የልመናችሎታ” ከፈጣሪው እንደተሰጠው ነው ሳይሸሽግ የነገረን። ስለሆነም ሰርዓተ አልበኞቹ የሕዝብን ህይወት ሲያናጉ ፤ በሽብር አገሪቷን ሲበጠብጡ ፤ የደቡብ ሕዝባችን እስከ በ80 ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ ከመኒኖሩበት ቦታ በአንድሳምንትውስጥ “ውጡ!” ተብለው ተባርረው እየተደበደቡ እየሞቱ እየተፈናቀሉ እያየ (በ800 ሺሕ የሚቆጠር) ምንም አርምጃ አልወሰደም።
ሁኔታው እንዲቀጥል እና እንዲባባስ የመሆኑ ምክንያት “የአብይ አመራር የብቃት ማነስ” ማሳያ ነው። እርሱ የሚያምነው ሽብርተኞችን አለመቆጣጠር ማለት ትርጉሙ፤-
በግጭትየማያምን፥ቀናእናሽብርተኞችንምእንደሰላማዊዜጎችበእኩልዓይንየሚያይ፥አባብሎለምኖዝምየሚያሰኛቸው፤አምባገነንያልሆነዲሞክራቲክመሪነውያስብለኛል” በሚል እምነት የተቃኘበት ስልቱ ነው። ስለሆነም ባንክ ዘራፊዎች እና አፈናቃዮችን “በተሰጠው የልመና ችሎታ” ለምኖ ለማስታገስ እየጣረ ያለውም ለዚህ ነው።
”ሽብርተኞችን ለምኖ ወደአስመራሄዶ አስመጥቶ ሲያበቃ ሽብርን በከፋ መልኩ በሕዝባችን ህይወት ላይ አፋፋመ። ለማኙ መሪ ‘ሰርዓተ አልበኞችን ማስቆም” አልቻለም። የተካነበት የልመና አስተዳደርም አልሰራም! ከቶውንም እየለመኑ ማስተዳዳር “ቅዠት” እንጂ ከዘመኑ ጋር አይሄድም።አገር በድፍረት እና በሕግ እንጂ በልመና አይቀናም።
መሰራት ያለበትን መስራት፤መደፈር ያለበትን ንግግር በድፈረት ተናግሮ የመሪው አቁዋም ማንነት ማሳወቅ የመሪ ዋና መመሪያው መሆን አለበት።
ሳይሸሽገን ደፍሮ የነገረን ደብቆት የቆየ አንድ ባህሪው ግን ነግሮናል። እርሱም በጦርነት አላምንም ሲለን ቆይቶ “አስክንድር ነጋን ለማሸማቀቅ በሓሰት ወንጅሎ “መፈንቅለመንግሥትሊያርግብኝእየዶለተነው” ብሎ “ግልጽጦርነትአውጅበታል” ይህ ሳይሸሽግ የማንነቱ ባሕሪ ባፈጠጠ መልኩ ሕዝብ ፊት መናገሩ የድፍረቱ ዓይነት ቢያስደነግጠንም “ስሜቱን ሳይሸሽግ ዛቻ መዛቱን ግን አዳራሹ በነበሩ “ማሃይማን ጋዜጠኞች” ተጨብጭቦለት አድናቆት አትርፏል። ታሪክም ለመጪው ትውልድ የሚታወስ ትውስታ “ነክሶ” እንደማይለቅ በመዝገቡ ዘግቦለታል! ይህ ግን ድፈረት ሳይሆን መሪዎች የሸሸጉት ባሕሪያቸው ሳያስቡት በድንገተኛ ቁጣ የሚያፈነዱት ድብቅ ማንነታቸው ያፈለቀው ድፍረት ነው።
ይህ አንድ ነገር አስታውሶኛል። ሊደፈሩ የማይችሉና ዋጋ የሚያስከፍሉ ግን ጠቀሜታ ያላቸው ለአገር ጠቀሜታ ተብሎ በድፍረት ሃቁን የዘረገፉ በቁርጣኛነታቸው የሚታወሱ ጥቂት መሪዎች ታሪክ ዘግቦአቸዋል። ለአገር ሲባል የማይደፈርን ድፍርት ደፍረው ራሳቸውን ለአደጋ የጋረጡ መሪዎች አሉ። በዚህ የምጠቅሰው ምሳሌ ያነበብኩት አንድ መሪ ትዝ አለኝ። የ1956 የመጀመሪያው የቱኒዚያ መሪ!
በ1956 ዓ.ም ነፃ የወጣችው የመጀመሪያው የቱኒዚያ መሪ የነበረው “ሓቢብቡርጊባ” ይባላል። የእስልምና ተከታይ የሆነውን የቱኒዚያን ሕዝብ ያልተጠበቀ “ቦልድ” “ፈጣጣ ውሳኔ” ወስዶ ‘ያደርገዋል ተብሎ ያልተጠበቀ አስገራሚ እርምጃ’ በሕዝቡ ላይ ተቀባይነት አግኝቶ እስከዛሬ ድረስ ሲታወስ ይኖራል።
ምንድ ነው ያደረገው? ከገዛሁት አመት ሆኖኝ አንብቤ ሳልጨርሰው በመጀመር በማስቀመጥ ላይ ያለሁት መጽሐፍ Conflict, Culture, and History (regional Dimensions) የሚል በአምስት ደራሲያን የተጻፈ መጽሐፍ ሳነብብ በእስልምና እምነት ተከታዮች ጭንቅላት ውስጥ የገባበትን አስተሳሰቦችን የመለወጥ ጥበቡ የሚገርም ነበር።
አገሪቷ በቅኝ አገዛዝ ስትማቅቅ ኖራ “ለዘብ ያሉ እስላማዊ ሃይላትን” ያቀፈ፤አክራሪ እስላሞችን የተቃወመ መሪ ነበር። አስገራሚው ውሳኔው ቱኒዚያ ድህነት ስላጠቃት “በሮመዳን ጾም” በቴ/ቪዥን ቀርቦ የብርቱካን ጭማቂ የያዘ ብርጭቆ በመያዝ “ፉት” እያለ ለሰከንዶች ቃል ሳይተነፍስ አፍጥጦ ተመልካቾቹን ያይ ጀመር፤ ወቅቱ “የሮመዳን ጾም” ነበርና የብርቱካን ጭማቂ የመጠጣቱን ትዕይንት ተመልካቾቹ “በድንጋጤ” ተውጠው ይመለከቱት ጀመር።
እንዲህም አለ፦
“ወቅቱሮሞዳንመሆኑንአውቃለሁ።ብዙዎቻችሁስራከመስራትተቆጥባችሁበየመስጊዱምሆነበየቤቶቻችሁአጥልላችሁአርፋችሁተቀምጣችሁአያለሁ።ሆኖምሸሪዓበሮማዳንወቅት ‘አትስሩ’ ‘እረፉ’ አላለም።ሸሪዓሥራንአይቃወምም።የገባንበትንአስፈሪድህነት “በጂሃድ”መመታትእንዳለበትሸሪዓያዝዛል።ሕዝባችንበድህነትእየማቀቀአጋዥአቅምሳይኖሮውድህነትንማሸነፍከቶአይቻለውም።ጂሃድሰይፍአንስቶበጦርነትመሳለፍብቻአይደለም፡ “ስራምጂሃዳዊግዴታነው” ስለዚህምአቅምሊሰጠንየሚችልአጋዥሃይል “ሳንኮንን” የገባንበትንየምጣኔሃብትግንባታተሎካላፋጠንንየባሰውንጭንቅውስጥመግባታችንአይቀሬነው!”
በማለት እዛው ቁጭ ብሎ የሚታየውን የሸሪዓውን እውነታ እንዲመለከቱት አዘናጊውን የአስተሳሰብ ዘይቤን በገንቢ አስተሳሰብ መዝዞ ለመለወጥ ወቅቱ የሚጠይቀውን ፈተና መጋፈጥ ምን ያህል ቆራጥ ድፍርት እንደሚጠይቅ ከሓቢብ ቡርጊባ ታሪክ ሳንብብ በጣም ተመሰጥኩ።
ይህንን በማድረጉ በአክራሪ እስላሞች ምን ያህል አስጨናቂ ፈተና እንደሚደርሰው የውቃል። ሆኖም እውነታውን በድፍረት መጋፈጥ ያንድ መሪ የመርሕ ባሕሪ ነበርና ያንን አድረጓል።
ቡርጊባ ለማለት የፈለገው፤ በጂሃድ ጦርነት ውስጥ “መግደፍ’ ይቻላል። ሳትበላ ከባዱ ጦርነት ላማካሄድ አቅም ያንሳሃል፡ ስለሆነም መግደፍ ይፈቅዳል። ድህነት እና አገር ግናበታም “ሌላው ጂሃድ” (ጦርነት) ስለሆነ አቅም ሊሰጣችሁ የሚችለውን ሁሉ ሳትኮንኑ ሳታርፉ ድህንትን መዋጋት ሸሪዓ ይፈቅዳልና ድህነትን ተዋጉ ማለቱ ነው። ባጠቃላይ ሊደፈር የማይቻለውን አውነታ ደፍሮ በተግባር ማሳየት ካንድ መሪ የሚጠበቅ አስገራሚ ክስተት ነው። ያውም እስላማዊ አገር መሪ ሆኖ!
አብይ ብዙ ጋጠወጦችን አስፋፍቶብናል (አንዳንዶቹ አልፈጠራቸውም አንዳንዶቹ ግን አዲሶች ናቸው)። ለምሳሌ ጋጠወጡና አሸባሪው ኦነግ ለምኖ ሲያስገባው “ሽብር ሲፈጽም” ጠ/ሚኒሰትሩ ‘ተው አቁም!” የማለት ድፍርት አጥቷል። ይባስ ብሎ “የታጠቀ የኦነግ ሃይል የለም” ብሎን ቁጭ ነው ያለው። ሆን ብሎ እነዚህን ሃይላት በድፍረት ማስቆም ከተከታዮቹ ጋር ድጋፍ ያስሰጠኛል ስለሚል በወላዋይ ባሕሪ ድፍርት አጥሮት ሕዝባችንን ለኦነግ ታጣቂዎች አጋልጦ ለመከራ ዳርጓል። አብይ አሕመድ የሚመራው ሰርዓት “አናርኪ” ነው። ምክንያቱም ስርዓተ አልባዎቹ በብዙ ገጠሮች እና ከተሞች ሕዝብን በመንገዳቸው እያስተዳደሩት ነው (እንደ የአልሸባብ ዓይነት አስተዳደር)። የሽብር ቁንጮዎች የምንላቸው የወያኔ መሪዎችን ሊደፍራቸው ቀርቶ ለምኖ ያስገባውን ኦነግ እንኳ ሳይቀር “ተው” ሊለው ድፍርት አጥሮት ልቅ ለቅቆታል። ለዚህም አናርኮ ፋሺስቶችን አሳድጓል። አናርኪ ማለት ደግም ይህንን ትርጉም ይሰጠናል፡
Anarchy is a state of disorder due to absence or nonrecognition of authority. Lawlessness, nihilism, disorder, stateless society… ይላል። አጠቃላይ ትርጉሙ የወረበሎች መንጋ የሚፈነጩበት መንግስት አልባ ክስተት ማለት ነው።
ይህ ከመዋቅሩ በሽብር ያደገ ፤ በሽብር የታነጸ ሕገ መንግሥት እና በወንጀል የተጨማለቁ ሰዎች የሚመሩት ስርዓት ሕግ አልባዎቹን መቆጣጠር ይችላል ወይ? የሚለው ጥያቄ መልሱ አይችልም ነው።
ምክንያቱም በአገሪቱ የደረሰው እና እየደረሰ ያለው ስርዓተ አልባ ክስተት የማስቆም ችሎታም ፍላጎትም ድፍረትም የለውም። ዋናው “ፍላጎት” የለውም የሚለው ነው ለኔ ዋናው መሰረታዊ መልሱ። ምክንያቱም የፋሽስት ኦሮሞ ፓርቲዎች አንዱ ፓርቲ ከሚመሩት አንደኛው ኦነጉ ብ/ጄነራል ከማል ገልቹ “ ኤል ቲ ቪ” በተባለ ቴ/ቪዥን ጣቢያ የሰጠው ቃለ መጠይቅ አብይ የደበቀብንን ምሰጢር አጋልጦ ሃቁን ነግሮናል።
እራሱ ከየኦሮሞ ጸጥታ ሃላፊነት ሰሞኑን መባረሩን አስመልክቶ በቃለ መጠይቁ እራሱ የነገረን ሃቅ “ግድያና የባንክ ዘረፍ” የተደረገው የአብይ አሕመድ ፓርቲ ኦፒዲኦ (አዴፓ) አድርግ እያለ በደብዳቤ እየጻፈ ለሽብርተኞቹ ያስፈጸመው እራሱ መንግሥት ነው ብሎ ምስጢሩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተናግሯል። ይህ ምስክርነት ይፋ ሲሆን ሕግ ቢኖር ኖሮ የሃገሪቱአቃቤሕግእናየፍርድቤቶችጠቅላይፕረዚዳንትተብየዋ ወዲያውኑ “ጉዳዩ” እንዲጣራ ፋይል እንዲከፈት ማድረግ ትችል ነበር። ሌላ ቀርቶ ፓርላማተብየውም ልዩ ስብሰባ አድርጎ ሰውየውን ጠርቶ በፓርላመው ፊት ጥያቄና መልስ ሰጥቶ ሕዝቡ እውነቱን ማግኘት ማደረግ ነበረበት። ግን አናርኮ ፋሺሰት (ፋሺስታዊ ስርዐተ-አልባ) መንግሥት በራሱ ላይ ምርምራ እንዲካሄድ አይፈልግም። (ልጁቀማኛአባቱዳኛ!)
የከማል ገልቹ አስገራሚው ምስክርነቱ ደግሞ የአሸባሪው ኦነግ ታጣቂዎች (ብዙዎቹ የኦዴፓ ታጣቂዎች ናቸው ይላል) በመንግሥት እውቅና ነው የሚንቀሳቀሰው ብሏል። በኦሮሞ አካባቢ ሲፈጽሙት የነበረውን ሽብር ረገብ አድርጎ ወደ ሌሎች አካባቢዎች በማስፋት ወደ “ከሚሴ እና የመሳሰሉ” ሄዶ እዛውም ሽብር እንዲፈጽሙ “ኦዴፓ’ አዝዞት ነው ብሎ ተናገሯል፡ (ኋላ “አብን” የሚባል አማራ ድርጅት ነው ብሎ አስቀድሞ ራሱን በራሱ የመሰከረውን የሚምታታ ወደ አማራው የሚያላከክ ንግግር ቢሰነዝረም)።
በዚም ምንጭ አውነት ከሆነ ለማም ሆነ አብይ የራሳቸውን ኦዴፓ ፓርቲ መቆጣጠር ችሎታ እና አቅም የላቸውም ወይንም ደግሞ ሆን ብለው ሽብሩ እንዲስፋፋ አድርገዋል ማለት ነው። ከሁለቱ አንዱ። ሰውየው አብይሚመራውኦዴፓ የተባለው ድርጅት (አብይ ባያዝዘውም) ኦነግ ባንኮች እንዲዘርፍ የጻፈውደብዳቤአለ‘’ ሲል መስክሯል። አስገራሚው ደግሚ ከሚሴ ውስጥ ያሉት የራሱ የከማል ገልቹ ኦነጋዊ አባሎች ናቸው ሲል ነግሮናል። ለግጭቱ መነሻም ሲነግረን “የኢትዮጵያሰንደቅአላማከተማውስጥይዘውየታዩትኢትዮጵያውያንላይየመንጠቅዘመቻበማድረግይህሰንደቅአላማእንደታሳዩንብለውነውግጭቱየተቀሰቀሰው” ብሎ አስገራሚ እና ግልጽ ጸረ ኢትዮጵያ ጦርነት እንደተካሄደ ተናግሯል። (ከማል ገልቹን “ቤቲ/ቤተልሄም ታፈሰ” የተባለቺው የ ኤል ቲ/ቪ ጋዜጠኛ ብትጠቀው ኖሮ የተሻለ ምስጢር ይወጣ ነበር የሚል ግምት አለኝ። ሆኖም ጋዜጠኛው እንደወትሮው ለስላሳ ስለነበር ብዙም አልገፋውም)::
ለዚህም ነው አብይ ሊደፈር የማይቻለውን ክስተት ለመድፈር እንደ ሓቢብ ቡርጊባ ‘ደፍር ሃሞትም ሆነ ፍላጎት’ የለውም ያልኩት። እራሱ አብይ አሕመድ እንደነገረን ችሎታው “ልመና” ነው። በመለመን ይሳካልኛል ብሎናል። ሥርዓትን በልማና ማስከበር ደግሞ የታየ የታሪክ አጋጣሚ አላነበብንም። መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ ቁርአንም ይህንኑ አያሳዩም። የአብይ ፍልስፍና “አናርኮ ፋሺዝምን” ባስደንጋጭ ፍጥነት ማስፋፋት ነው። እባቡና ጫጩቱ ፤ ገዳይ እና ተገዳይ ወንጀለኛው እና ሰላማዊው እንዳቅማቸውይዋጣላቸው ብሎ ነጠላው አፉ ላይ ከድኖ የጎረምሶችን ትግል ለማየት ሙርኩዝን ተደግፎ እንደሚያይ ሽማግሌ “አህያና ጅብ ተገዳድለው፤ ተፈነቃቅለው ፤ ተቦጫጭቀው” ሲደክማቸው እራሳቸው ይከስማሉ” የሚል ስርዓተ አልባዊ “ታዛቢስርዓት” እንጂ “ሕግ አስከባሪ ስርዓት አይደለም”።
ስለሆነም አዲስ መንግሥታዊ ሕገ መንግሥትም ሆነ አዲስ መሪ መለወጥ የግድ ነው። አንድ አመት ሙሉ ተንጨብጭቦለት ሰላም እንዲያሰፍን ፤ ህይወት እንዲያረጋጋ ዕድል ተሰጥቶት በሚገርም ሁኔታ ‘ከድጡ ወደ ማጡ’ አሸጋግሮናል። ይህም አልሰራም። ሌላ መሪ መፈተሽ የግድ ነው!