April 29, 2019

ክሬሚያ ጥንትንም የሩሲያ ግዛት የነበረች ብትሆንም ክሬሚያን አሳልፎ የሰጠው በወቅቱ የሶቪየትን ኤምፓየር እንዲገዛ በትረ መንግስቱን ስታሊን እጅ ለመረከብ እድል እጁ መዳፉ ውስጥ የገባችለት khushchov ነበር። khushchov ዩክሬን የሩሲያ ግዛት አካል የሆነችበትን ሶስት መቶኛ አመት ምክንያት በማድረግ ክሬሚያን ከሩሲያ ወስዶ ወደ ዩክሬን ለመደባለቅ የፈጀበት አስራ አምስት ደቂቃ ብቻ ሲሆን ሰውየው ይኽን እርምጃ እንዲወስን ያደረገው ሶቪየት ኤምፓየር እንዲህ በቀላሉ ፈርሶ ዩክሬንም ነጻ መንግስት ትሆናለች የሚል ግምት ስላልነበረው ነው። ሆኖም ግን ይኽ ታሪካዊ ውሳኔ የተነሳ ክሬሚያ ክእናት ራሽያ በተለየች አርባ አመት ሳይሚላ ሶቪየት ህብረት ብትንትኑ መውጣቱ የክሬሚያ ነገር በሩሲያ ህልውና ላይ ሌላ ዙር አደጋ ይዞበት መጣ።
፩ ዩክሬን ማለት ሩሲያ ከምእራብ አውሮፓ በኩል ለሚመጣው ማንኛውም ጥቃት እራሷን የምትከላከልበት በፈር ዞን ሲሆን ዩክሬን በኔቶ እጅ ብትገባና የአሜሪካ ሚሳየል ዩክሬን ላይ ቢጠመድ ሞስኮን በሶስት ደቂቃ ውስጥ ለመምታት የሚያስችል አቅም ይሰጣል።
፪ በአመቱ ውስጥ አብዛኻኛውን ወራት በሃይለኛ በረዶ ውስጥ የምታሳልፈው ሩሲያ የኑክሌር ባህር ሰርጓጅና የጦር መርከቦቿን ያለመንም አይነት ተጨማሪ እድሳት ለማቆም የሚያስችልና አመቱን ሙሉ የማያቋርጥ ሙቅ ውሃ ልታገኝ የምትችለው ከጥቁር ባህር ጋር የምትዋሰነው ክሬሚያ በመሆኑ የዚኽች ቦታ በጸረራሺያ ሃይሎች እጅ መግባት የራሺያን የባህር ሃይል ፈተና ውስጥ የሚጨምረው ይሆናል።
በዚህም የተነሳ የዩክሬኑ ያናኮቪች በፋሽቶች መገልበጥን ተከትሎ ቆፍጣናው ፑቲን በወሰደው ፈጣን እርምጃ አንድ ሰዓት ባልሞላ ኦፐሬሽን፣ ክሬሚያን አንድ የጽጌረዳ አበባ ሳይቀነጠስ ወደ እናት እራሽያ ጠቅልሎ ቁጭ አለ።
አማራውን ለማዳከም የቀን ጅቡ ከወሰዳቸው በርካታ እርምጃዎች ውስጥ አንዱ መተከልን ከጎጃም ነጥቆ ቤንሻጉልን መፍጠሩ ነው። ቢሆንም ግን በዚህ ቦታ ከሚኖረው ውስጥ ከዘጠና ስድስት ከመቶ በላይ የሚሆነው አማራና አገው መሆኑ ይታወቃል። ቢሆንም ግን ቀን በሰቀላቸው ከሃዲያን ቆስቌሽነት የተነሳ ዛሬ በመተከል ውስጥ መልኩ ቀላ ያለውን ሁሉ እየተመረጠ ማምቡክና ዳንጉር የተባሉ ቦታወች ላይ እየተገደለ የመዋሉ ነገር ስንጠግበው የዋልነው መርዶ ነው።
መቸም የአማራው ክልል በበኩሉ እንዲህ ዓይነቱን ችግር በፌደሬሽን ምክር ቤት በኩል መፍትሔ ያገኛል ብሎ የሚያንቀላፋ ከሆነ እልቂቱ በከፋ መልኩ በምላትና በስፋት እንደሚቀጥል ጥርጥር የሌለው ከመሆኑም ባሻገር ክልሉ ችግሩን በራሱ ግዜ ፈትቶ ለነዋሪው ሰላም ይፈጥራል ብሎ ማሰብ አይቻልም። ይልቁንም ዛሬ ቤንሻጉል ክልል ማለት በማንኛውም መስፈርት ማንም የፈለገውን የሚያደርግበት ፌይልድ ስቴት የሚሉት አይነት አደጋ ውስጥ የወደቀ መሆኑ ይበልጥ ግልጽ እየሆነ የመጣ ሆኗል። ስለዚህ በዚያ በኩል ያለውን ህዝብ ሰላም ከማስከበር አንጻር፣ ቦታው የአባይ ግድብ ጋር ያለው ግንኙነትና እንዲሁም በዚያ በኩል ክልሉን ለሚዳፈሩ ተንከሲሶች መግቢያ ቀዳዳ ላለመስጠት ጭምር ሲባል አምባቸው መኮንን ቆራጥ ከሆነ መተከልን እንደ ክሬሚያ በጠዋት ተነስቶ ለመሰልቀጥ የሚያግደው ነባራዊ ሆኔታ የሌለ ከመሆኑም በላይ ለነወልቃይትና ራያ የተስፋ ብርሃን መሆን ይችል ነበር። ክፋቱ ግን ሰውየው የስነልቦና እና የእውቀት ልምሻ ያለባቸውን የአዴፓ ኮተታሞች አሳምኖ እና ያለውን ቢሮክራ ተቌቁሞ እንዲህ ያለ ስትራቴጅካል እርምጃ ለመውስድ የሚያስችል አመራር የመስጠት አቅም ያለው አይመስልም።