May 3, 2019

Source: https://fanabc.com

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት ሶስት ቀናት በኢትዮጵያ ሲካሄድ የቆየው የዓለም የፕረስ ቀን በዓል ተጠናቀቀ፡፡

በአፍሪካ ህብረት የመሰብሰቢያ አደራሽ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየውና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችና ጦማሪያን የተሳተፉበት የዓለም የፕረስ ቀን በዓል ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል፡፡

በመድረኩ ላይ በኢትዮጵያ የፕረስ ነፃነት ካለፈው አንድ ዓመት የመንግስት ማሻሻያ በፊትና በኋላ፣ የመገናኛ ብዙሃን በዴሞክራሲ ግንባታና በምርጫ ሂደት ላይ ሊኖራቸው በሚገባው ሚና ዙሪያ እንዲሁም የማህባራዊ ሚዲያዎችና የዲጂታል ቴክኖሎጅ መስፋፋት ለዘርፉ እደገት ያላቸው ምቹ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

በሀገሪቱ ባለፈው አንድ አመት በተደረጉ የመንግሰት አሰራር መሻሻዎች ዘርፉ መነነቃቃት ማሳየቱ በውይይቱ ተነስቷል፡፡

በዚህም ከ260 በላይ ተዘግተው የነበሩ  ድረገጾች መከፈታቸው ለአብነት ተጠቅሷል፡፡

የግልም ሆነ የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን አቅም መጠናከር ፣ ጋዜጠኞች ለሙያ ስነ ምግባርና ለህግ ተገዥ በመሆን የህዝብ ድምጽ ሆነው ማገልገል እንዳለባቸውም ነው የተገለጸው፡፡

የማህባራዊ ሚዲያዎችና የዲጂታል ቴክኖሎጂ መስፋፋት አሁን ላይ በርካታ ጥቅሞች ያሉት ቢሆንም የሚቆጣጠረው አካል ባለመኖሩ የሃሰት መረጃዎችና የጥላቻ ንግግሮች ማሰራጫ እየሆኑ በመምጣታቸው ተጽኗቸው ከፍተኛ መሆኑን ተወያይዮቹ ተናግረዋል፡፡

ለዚሁ ችግር መስፋፋትም የመንግስትም ሆነ የግል ሚዲያዎች ወቅታዊ መረጃዎችን ለአድማጭ ተመልካቾቹ ከማቅረብ አንፃር ያለው ውስንነት፣ ለአንድ ወገን አድሎ ማሳየት ደንበኞች ከመገናኛ ብዙሃን ይለቅ ወደ ማህበራዊ ሚዲያዎች ዝንባሌ እንዲኖራቸው የየራሳቸው ተጽእኖ እንዳላቸው ነው የተገለጸው፡፡

በምርጫ ሂደትም ከማህበራዊ ሚዲዎች ተጽእኖ ለማላቀቅ የምርጫ ቦርድን በቴክኖሎጂ በመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በማዘመን የመረጃ ተደራሽነትን ለማሳለጥ ከወዲሁ መስራት ያስፈልጋል ተብሏል፡፡

በዚህም ዋጋ ከሚያሳጡ መረጃዎች ህብረተሰቡ ራሱን መጠበቅ እደሚቻል ነው ተወያዮቹ ያነሱት።

ለህብረተሰቡ ከወከገንተኝነት የጸዳ ወቅታዊ መረጃዎችን ማደረስ ላይ የመገናኛ ብዙሃኑ ትኩረት አድረገው ሊሰሩ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡

በትዕግስት ስለሺ