May 4, 2019


Source: https://fanabc.com-

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 23ኛ ሳምnት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በዛሬው እለት በአዲስ አበባ እና በክልል ስታዲየሞች ቀጥለው ተካሂደዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም የተካሄደው ጨዋታ መከላከያን ከባህር ዳር ከተማ ያገናኘ ሲሆን፥ ጨዋታውም በመከላከያ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የመከላከያን ብቸኛ የማሸነፊያ ጎል ፍቃዱ ዓለሙ በ30ኛው ደቂቃ ከመረብ አሳርፏል።

መቐለ ላይ የተደረገው የደደቢት እና የፋሲል ከነማ ጨዋታን ደግሞ ፋሲል ከነማ በሰፊ የጎል ልዩነት ማሸነፍ ችሏል።

ፋሲል ከነማ ጨዋታውን 5ለ1 በሆነ ውጤት ደደቢትን የረታ ሲሆን፥ የፋሲል ከነማን የማሸነፊያ ጎሎችም አምሳሉ ጥላሁን፣ አብዱራህማን ሙባረክ፣ ሽመክት ጉግሳ፣ ኤፍሬም ዓለሙ እና ሙጂብ ቃሲም ከመረብ አሳርፈዋል።

የደደቢትን ብቸኛ ጎል ደግሞ መድሀኔ ታደሰ ነው ከመረብ ያሳረፈው።

ደቡብ ፖሊስን ከአዳማ ከተማ ያገናኘው ጨዋታ ደግሞ በደቡብ ፖሊስ 2ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በጨዋታው ላይም ሄኖክ አየለ እና ብርሀኑ በቀለ የደቡብ ፖሊስን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል።Filed in:Uncategorized